Author Archives: Central

መምህራን በእያመቱ በሚጠራው የገዢው ፓርቲ ስብሰባ መሰላቸታቸውን ገለጹ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ በመላ አገሪቱ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማብረድ በሚል ትምህርት የሚጀመርበትን ጊዜ በማራዘም መምህራንን ለ2 ሳምንት የሚቆይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ በዛሬው ስብሰባ መምህራን በእያመቱ በሚደረገው አንድ አይነት ውይይት መሰላቸታቸውን ገልጸዋል። “መምህራኑ ከትምህርት ጋር ባልተያያዘ ጉዳይ ለምን እንሰበሰባለን?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ግዴታ መሆኑ ተነግሯቸዋል። መምህራኑ የጧቱን ዝግጅት ተካፍለው የከሰአቱን አብዛኞቹ አለመሳተፋቸውን መምህራን ...

Read More »

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ  ለ5ኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ የሆኑት የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ በዛሬው እለት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በአካል ሳይቀርቡ ለአምስተኛ ጊዜ ለመስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን የሰላም አስከባሪ የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ  በመኖሪያ ቤታቸው ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለም አቀፍ ትኩረት እያገኘ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009) ባለፉት በርካታ ወራት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአሜሪካ መንግስት ምክር ቤት ትኩረት እያገኘ እንደሆነ አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ ምክር ቤት ተወካይ ተናገሩ። የኮሎራዶ ሴናተር የሆኑት ኮንግሬስ ማን ማይክ ኮፍማን ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ፣ ኢትዮ-አሜሪካውያን በየግዛታቸው ለሚገኙ የኮንግሬስ ለወኪሎቻቸው በመደወል የኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል። አሜሪካ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያላት አቅም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009) የአለም ባንክ ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያላት አቅም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንና ሃገሪቱ ከ189 የአለማችን ሃገራትይ መካከል በ148ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱን ይፋ አደረገ። በአለም የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ዙሪያ ሪፖርቱን ያወጣው የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርገው የሚገኙ የውጭ ኢንቨስትመንት ደንቦችና ጥበቃዎች ከሌሎች ሃገራት ሲነጻጸሩ ደካማ ሆነው መገኘታቸውን ገልጿል። የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ህጎቻቸው ላይ የማሻሻያ እርምጃ ...

Read More »

የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰደ ያለው ከመጠን ያለፈ ዕርምጃ እንዳሳሰበው ገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናትን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ አመራሮችና ሰላማዊ ሰፈኞች ላይ እየወሰደ ያለው ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ አሳስቦት እንደሚገኝ ማክሰኞች በድጋሚ ገለጠ። በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ በብሪታኒያ የተሰባሰቡ የኮሚሽኑ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የጅምላ እስራት እያካሄዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ሃላፊ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴን በኢትዮጵያ የተለያዩ ...

Read More »

በቂሊንጦ አደጋ የተረፉ እስረኞችን ለመጠየቅ ገደብ መጣሉ ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009) በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰውን የእስት ቃጠሎ አደጋ ተከትሎ ከአደጋው የተረፉ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ያቀኑ ጠያቂዎች በእስር ቤቱ አስተዳደር እገዳ መጣሉን ለኢሳት አስታውቁ። የእስረኛ ቤተሰቦች የቤተሰብ አባሎቻቸውን ለመጠየቅ ወደ እስር ቤቱ ቢሄዱም የያዙትን ነገር ብቻ አቀብለው ያለምንም ንግግር እንዲመለሱ መደረጉን ከዜና ክፍላችን ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉ ቤተሰቦች ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ እስር ቤት ላይ ደርሶ ...

Read More »

በኮንሶ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወታደሮች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጸሙ

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከኮንሶ የዞን አስተዳደር ጋር በተያያዘ  ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ሲንከባለል የቆየው ጥያቄ፣ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት እያመራ ሲሆን፣ ግጭቱ ዛሬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፎአል። የቆሰሉና ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንድ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰው እንደገለጹት ዛሬ ብቻ ሁለት መንደሮች እንዲቃጠሉ መደረጉንና ተጨማሪ አደጋ ይደርሳል ብለው ...

Read More »

በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁሉቱ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ውጥረቱ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፣ በባህርዳር አንዳንድ አካባቢዎች የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ውለዋል። በሆለታ ሙገር አካባቢም ሱቆችና መዝነኛ ቦታዎች ተዘግተዋል። የዳንኮቴ የስሚንቶ ፋብሪካ መኪኖች እንደማይነቀሳቀሱም የአይን እማኞች ገልጸዋል። በባህርዳር የስራ ማቆም አድማውን ለማካሄድ የተበተነው ወረቅት በህዝቡ ዘንድ ብዥታን ፈጥሮ ውሎአል። በተወሰኑ ቀበሌዎች የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው አርፍደዋል። አስተባበሪ ሃይሉ ...

Read More »

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ (ቢጂአይ) በህወሃት አባላት ቁጥጥር ስር መሆኑን ሰራተኞች ገልጹ

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገራችን ከሚታዎቁ አንጋፋ የቢራ ፋብሪካዎች አንዱና ቀደምት በሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ የህወሃት ባለስልጣናት የፋብሪካውን ቁልፍ ቦታዎች በአባላቱ በመቆጣጠር ከፍተኛ ምዝበራ እያካሄደቡት መሆኑን የውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል። ከሰማኒያ ዓመታት በፊት የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በሃያ ሺህ ካሬ ሜትር ሰፍሮ የሚገኝ ሲሆን ከሶስት ሽህ በላይ ሰራተኞች አሉት። ድርጅቱ  ከመንግስት ወደ ግል ከተዛወረበት ጊዜ አንስቶ  በፈረንሳዊ ባለሃብትነት የሚተዳደር ቢሆንም በፋብሪካው ውስጥ በከፍተኛ አመራር ላይ የተቀመጡት የህውሃት አባላት ከሚፈጽሙት የገንዘብ ዝርፊያ በተጨማሪ፣ ለድርጅቱ ገጽታ ግንባታ እየተጠቀሙበት መሆኑን  ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱን ከሚመሩት የህወሃት ሰዎች መካከል የማስታወቂያ ክፍል ሃላፊው አቶ ኢሳያስ  አደራ አንዱ ሲሆኑ፣  ግለሰቡ ወደ ድርጅቱ ከገቡ በኋላ በማስታወቂያ ክፍል ኃላፊነት በመስራት ላይ ናቸው። ግለሰቡ ...

Read More »

በድርቅ የተጠቁ 9.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሁንም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በስድስት ክሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ጋር ተዳምሮ በ9.7 ሚሊዮን ሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን እያደረሰ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ ዕልባት አለማግኘቱን ያወሳው ድርጅቱ የኮሌራና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ድርቁን በመከላከሉ ስራ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት ...

Read More »