Author Archives: Central

የመንግስት ሃይሎች በሰገን ልዩ ዞን ጎማይዴ ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ከመኖሪያ ከቀያቸው እያፈናቀሉ ነው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009) በደቡብ ክልል ስር በሚገኘው የሰገን ልዩ ዞን ጎማይዴ ወረዳ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ለዘመናት በኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ከቀያቸው የማፈናቀል እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን እማኞች ሃሙስ ለኢሳት አስታውቁ። ሰሞኑን የጸጥታ ህያሎች የመኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ ያደረጉትን ድርጊት ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በዞኑ ስር የሚገኙት ...

Read More »

በጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ ግጭት አስነሳ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009) በሰሜን ጎንደር ዞን ስር በሚገኙት የአምባ ጊዮርጊስና በለሳ አርባይ ከተሞች ነዋሪዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተሞከረው እንቅስቃሴ ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ሃሙስ ለኢሳት ገለጹ። ከረቡዕ ጀምሮ በከተሞቹ የተቀሰቀስው ግጭት ዕልባት አለማግኘቱን የተናገሩት ነዋሪዎች ሃሙስ ለሁለተኛ ቀን ለሰዓታት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ማምሸቱን እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ...

Read More »

በእብናት ወረዳ በተደረገው ተቃውሞ አንድ ወጣት ተገደለ

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእብናት ወረዳ ህዝብ ከመስከረም 1 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ የጀመረውን የስራ ማቆም አድማ ቀጥሎበታል። ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወታደሮች የከተማው ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ህዝቡ ማንኛውንም መስዋትነት እንከፍላለን እንጅ ከእንግዲህ በዚህ አገዛዝ ስር አንቀጥልም ማለቱን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ ወታደሮችን ከእየቦታው አሰባስቦ ወደ እብናት ከተማ እያስገባ ነው። ...

Read More »

በህዝብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ አልሰጥም ያለ መኮንን  ከህወሃት ደህንነቶች ጋር ተዋግቶ ህይወቱ አለፈ

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መቶ አለቃ ደጀን ሞቅያለው በሰላም አስከባሪነት ከተሰማራበት ሶማሊያ ወደ ወልቃይት ጠገዴ አካባቢ እንዲዛወር ከተደረገ በሁዋላ፣ በህዝብ ላይ እሱ የሚመራቸው ወታደሮች ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስዱ ማዘዙን ተከትሎ፣ የህወሃት ደህንነቶች ሊይዙት ሲሞክሩ ተታኩሶ ህይወቱ አልፏል። “ወታደር ድንበር ሊያሰጥብቅ እንጅ ህዝብ ሊገድል ተልእኮ አልተሰጠውም” የሚል ጠንካራ አቋም የነበረው የስማዳ ተወላጁ መቶ አለቃ ደጀን፣ በአካባቢው ...

Read More »

የኮንሶ ነዋሪዎች ወደተለያዩ አካባቢዎች እየተሰደዱ ነው

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እልቂት እየደረሰ እንደሆነ የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች፣ ከአጋዚ ወታደሮች እና ከፌደራል ፖሊሶች የሚደርስባቸው ጥቃት ለማምለጥ ወደ ተልተሌና አጎራባች ወረዳዎች እየተሰደዱ ነው። በርካታ ታዋቂ ሰዎች ተይዘው አርባምንጭ እስር ቤት መግባታቸውም ታውቋል። አራስ ሴቶች ሳይቀር በወታደሮች እየተገደሉ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ወደ አካባቢው በመግባት ...

Read More »

አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በከፍተኛ ችግርና በህመም ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ዓመታት በፊት በኖርዌይ በተደረገ ተደጋጋሚ  የማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር አንደኛ የወጣውና የአሸናፊነት ገመዱን ሲበጥስ ሁለት እጆቹን ወደ ላይ በማጣመር የተቃውሞ ምልክት ያሳየው አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በክፍተኛ ችግርና በህመም ላይ እንደሚገኝ ገለጸ። በኖርዌይ በስደት የሚገኘው አትሌት ሙሉጌታ ለሁለት ጊዜ በተደረገ የማራቶን ውድድር ነበር ሁለት ጊዜ የኢሳትን ቲሸርት ለብሶ በመሮጥ ያሸነፈው። ...

Read More »

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ዕርምጃ እንድትወስድ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በአለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ድጋፍ ከፍተኛ እያገኘ እንደሚገኝ ተገለጸ

  ኢሳት (መስከረም 4 ፥ 2008) የአሜሪካን ምክር ቤት አባላት ሃገሪቱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ እርምጃን እንድትወስድ በማስተዋወቅ ላይ ያሉት የውሳኔ ሃሳብ በበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ድጋፍ በማግኘት ላይ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ። ይኸው በአሜሪካ የምክር ቤት አባላት ዘንድ እየተዋወቀ የሚገኘው የውሳኔ ሃሳብ የአሜሪካን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማውገዝ ለሃገሪቱ በሚሰጡ የተለያዩ ድጋፎች ላይ የማስተካከያ እርምጃ ...

Read More »

በኢትዮጵያ መከፈት የነበረበት መደበኛ ትምህርት እንዲራዘም ተደረገ

ኢሳት (መስከረም 4 ፥ 2008) በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ዕልባት አለማግኘቱን ተከትሎ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በተያዘው ሳምንት መጀመር የነበረበት የ2009 ዓም የትምህርት ፕሮግራም እንዲራዘም ተደረገ። የትምህርት ሂደቱ በተያዘው ሳምንት ሰኞ መጀመር የነበረበት ቢሆንም የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች ከመስቀል በዓል አከባበር በኋላ እንዲከፍቱ ምክክር በማድረግ ላይ መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ...

Read More »

በኮንሶ በርካታ ዜጎች ተገደሉ : አካባቢው የጦርነት ቀጣና ሆኗል ተባለ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰራዊት እና የደቡብ ክልል የልዩ ሃይል አባላት በኮንሶ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ባለው ጥቃት በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ25 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ይሆናል ይላሉ። ከተገደሉት መካከል አንድ አራስ ሴት በጥይት ተደብድባ ስትገደል፣ ህጻኑ በወታደሮች ተወስዷል በማለት የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። ትናንት ብቻ ...

Read More »

በባህርዳር እና እብናት የተጀመረውን የስራ ማቆም አድማን ተከትሎ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና በሰሜን ጎንደሯ እብናት ትናንት መስከረም 3 /2009 ዓም  ነጋዴዎች የጀመሩትን የስራ ማቆም አድማ ዛሬም በከፊል የቀጠሉ ሲሆን፣ በዚህ የተበሳጩት የአገዛዙ ካድሬዎች በርካታ የንግድ ድርጅቶችን ለመጨረሻ ጊዜ እያሉ በማሸግ ላይ ናቸው። አዲሱን ዓመት በትካዜ የተቀበለው የባህር ዳር ህዝብ የታሰሩት ልጆቹ እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም መልስ ሊያገኝ አልቻለም። የ25 ዓመታት የአፈና አገዛዝ ...

Read More »