Author Archives: Central

ጎንደርና ባህርዳር እንደገና አድማ መቱ

መስከረም ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በህወሃት አገዛዝ ላይ የሚካሄደው የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ዛሬም እንደወትሮው በስራ ማቆም አድማ ቀጥሎ ውሎአል። ሁለቱ ታሪካዊ ከተሞች በአንድ ቀን የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ፣ የክልሉ ህዝብ ከእንግዲህ የህወሃትን አገዛዝ ተመልሶ ማየት እንደማይፈልግ ማሳያ ነው ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ወገኖች። አብዛኛው ህዝብ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ገቢ የሚተዳደር ቢሆንም፣ የጎንደር እና ...

Read More »

በኮንሶ ከ12ሺ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

ኢሳት (መስከረም 6 ፥ 2008) ሰሞኑን በደቡብ ክልል በሚገኘው የሰገን ህዝቦች ዞን ኮንሶ ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ወደ 12ሺ የሚጠጉ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግስት አርብ አስታወቀ። የዞን ነዋሪዎች ሃሙስ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎኦች በኮንሶ ብሄረሰብ የተነሳውን አስተዳደራዊ ጥያቄ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ በአካባቢው ሆን ተብሎ ግጭትን እንዲቀሰቅስ መደረጉን ገልጸዋል። በዚሁ የጸጥታ ሃይሎች ድርጊት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውንና ለዘመናት በስፍራው ...

Read More »

ህወሃት በኦሮሞና በአማራ ብሄሮች ላይ ሆን ብሎ የማግለል እርምጃ ሲወሰድ መቆየቱን አቶ ጁነዲ ሳዶ ገለጹ

ኢሳት (መስከረም 6 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓት ውስጥ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ቁልፍ የሆኑ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ይዞታዎችን ለመቆጣጠር በኦሮሞና አማራ ብሄር ላይ ሆን ተብሎ የታቀደ ስልታዊ የማግለል እርምጃ ሲወሰድ መቆየቱን በስደት ላይ የሚገኙት የቀድሞ ሚኒስትር አቶ ጁነዲ ሳዶ ገለጡ። ህወሃት ሲፈፅም በቆየው በዚሁ ስልታዊ ድርጊት በርካታ የኦሮሞና የአማራ የጦር ሰራዊት አባላትና ጀኔራሎች ለእስር መዳረጋቸውንና ከሃገር የኮበለሉ መኖራቸውን ሚኒስትሩ ...

Read More »

በአንባጊዮጊስ በወታደሮችና በህዝቡ መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ አምባጊዮርጊስ ከተማ አቀርቢያ በምትገኘው አይባ ኪዳነምህረት መሳሪያቸውን ላለማስጠነቅ ትግል የጀመሩት አርሶአደሮች ፣ ከወታደሮች ጋር ተፋልመው በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል። አንዳንድ ወገኖች የሟች ወታደሮችን ቁጥር በአስራዎች ይቆጠራል ይላሉ።  ኢሳት  የሟች ወታደሮች ትክክለኛ አሀዝ ለማወቅ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ትናንት ምሽትና ዛሬ ጠዋት በርካታ ወታደሮች ወደ ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸው ...

Read More »

በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ ላይ የደረሰው ቃጠሎ ሆን ተብሎ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ሃሙስ ምሽት በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ በሚባለው አካባቢ የተነሳው ቃጠሎ በርካታ ንግድ ድርጅቶች አውድሟል። ነጋዴዎች ቃጠሎው ሆን ተብሎ መነሳቱን እና እሳቱን ለማጥፋት ህዝቡ ወደ አካባቢው ሲጠጋ መከልከላቸውን እንዲሁም የእሳት አደጋ መኪና ዘግይቶ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በቃጠለው ሰለወደመው የንብረት መጠን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

Read More »

ገዢው ፓርቲ በሶማሊያ እና በኦሮሞ ብሄሮች መሃከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲል የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር አስታወቀ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁ ዜጎች የኦሮሚያ እና አማራ ብሔረሰቦችን ጨምሮ በተለያዩ የአገርቱ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የኦጋዴን ነጻነት ግንባር አስታውሷል። በዜጎች መሃከል የእርስበርስ እልቂት እንዲፈጠር ሆን ተብሎ በገዥው ፓርቲ እየተሰራ ሲሆን፣  በተለይ በሶማሊያና ኦሮሞ ብሔረሰቦች መሃከል ግጭት በመፍጠር ሰላማዊ ዜጎች ተገለዋል፣ ተሰደዋል፣ በግፍ ታስረዋል። በሶማሊያና ...

Read More »

በሸዋ ሮቢት በድብደባ የተገደለው ወጣት አስከሬን ለቤተሰቦቹ ተሰጠ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው ተቃውሞ ላይ ተሳትፈሃል በሚል የተያዘው ፍጹም የተባለው ወጣት ሸዋ ሮቢት እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ተፈጽሞበት ህይወቱ ካለፈ በሁዋላ አስከሬኑን ወደ ቂሊንጦ በማምጣት በእሳት እንደተቃጠለ ተደርጎ ለቤተሰቦቹ መሰጠቱን ምንጮች ገልጸዋል። የፍጹም የቀብር ስነስርዓት ትናንት በቦሌ ሚካኤል ተፈጽሟል።

Read More »

በአዲስ አበባ የተጀመረው የመምህራን ውይይት ከፍተኛ ተቃውሞ የታየበት እንደነበር ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009) በአዲስ አበበ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ት/ቤቶች ከረቡዕ ጀምሮ መካሄድ የጀመረው የመምህራን ውይይይት ከአስተማሪዎች በኩል ተቃውሞ እንዳጋጠመው መምህራት ለኢሳት አስታወቁ። ለዚህ ሃገር አቀፍ ውይይት እንዲሳተፉ ጥሪ የቀረበላቸው መምህራን መንግስት ወዳቀረበው የመወያያ አጀንዳ ከመገባቱ በፊት መምህራንን የቅድመ ሁኔታ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተሳታፊ መምህራን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። ረቡዕ የተጀመረው ይኸው የመምህራን ...

Read More »

በቂሊንጦ እስር ቤት በእሳትና በጥይት የተገደሉ ዜጎች ያለማስረጃ ለቤተሰብ እየተሰጡ ነው

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009) በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት ደርስ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ እስረኞች ያለምንም ማስረጃ ለቤተሰብ እንዲሰጥ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የማንነት ጥያቄን አስነስታችኋል ተብለው ባለፈው አመት ለእስር ተዳርገው ከነበሩት የሰሚን ጎንደር ዞን ትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪዎች መካከል በቂሊንጦ እስር ቤት ህይወታቸው ያለፈው አቶ ይላቅ አቸነፍ አስከሬን ለቤተሰብ ተሰጥቶ የቀብር ስነስርዓት መፈጸሙን ለኢሳት ...

Read More »

የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ አገራት ወደአለመረጋጋትና ሁከት ሊገቡ እንደሚችሉ አሜሪካ አሳሰበች

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009) የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ የአለማችን ሃገራት ለችግሩ ዕልባትን የማይሰጡ ከሆነ ወደ ዘላቂ አለመረጋጋትና ሁከት ሊገቡ እንደሚችሉ አሜሪካ ሃሙስ አሳሰበች። ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በስላማዊ ሰልፎች ላይ ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ እንደተጠቀመ የገለጸችው ሃገሪቱ ጭቋኝና አፋኝ የሆኑ ሃገራት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ከዜጎቻቸው ጠንካራ ተቃውሞ እየቀረበባቸው መሆኑን አስታወቀች። ሃሙስ በአለም ዙሪያ የተከበረውን የአለም አቀፉን የዴሞክራሲ ቀን አስመልክቶ ...

Read More »