Author Archives: Central

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠው

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የነበረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዞ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍቤት ቀርቦ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም ...

Read More »

በባህርዳርና ጎንደር ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ

ኢሳት (መስከረም 12 ፥ 2009) በባህርዳርና ጎንደር ከተሞች በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ሃሙስ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ህያሎች ይፈጸማል ያሉትን ግድያና የጅምላ እስር በማውገዝ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ መጀመሪቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸው ህዝባዊ ተቃውሞ በሁለቱ ከተሞች መቀጠሉን ለመረዳት ተችሏል። የመንግስት ባለስልጣናት የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ስራቸውን እንዲጀምሩ በማስገደድ ላይ ቢሆኑም የንግድ ባለቤቶቹ ስራ ...

Read More »

በጎንደር ከተማ ቃጠሎ ለማስነሳት የሞከረች አንድ ሴት መያዟ ተነገረ

ኢሳት ( መስከረም 12 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ሃሙስ ቀበሌ 14ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የኢሳት ቃጠሎ ለማስነሳት ከትግራይ ክልል መምጣቷ የተነገረ አንዲት ሴት በነዋሪዎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ። ለጊዜው ስሟ ያልታወቀው ተጠርጣሪ በአካባቢው ነዋሪዎች ከተያዘች በኋላ ለጸጥታ ሃይሎች ተላልፋ የተሰጠች ሲሆን ተጠርጣሪዋ በተሽከርካሪ ታጅባ በጎንደር ከተማ ስትዘዋወር የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ ይፋ ተደርጓል። በድርጊቱ ቁጣ የተሰማቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠርጣሪዋን ይዞ ...

Read More »

ጎንደር ቅዳሜ ገበያ ሱቆችን ለማቃጠል የተንቀሳቀሱ አራት ሰዎች ረቡዕ በቁጥጥር ስር ዋሉ፥ ሌሎች ሱቆችን ለማቃጠል 50 ያክል ሰዎች እንደተሰማሩ ተነግሯል

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) በጎንደር ቅዳሜ ገበያ ያልተቃጠሉ ሱቆችን ለማቃጠል ቤንዚን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ሰዎች ረቡዕ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በጎንደር እንደገና ቁጣ ተቀሰቀሰ። ግለሰቦቹ ከትግራይ ክልል መላካቸውንም ለኢሳት መረጃ ያደረሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሱቆቹን ሲያቃጥሉ ሲሉ በነዋሪዎች ከተደረሰባቸው በኋላ በፖሊስ እጅ የገቡት አራቱ ግለሰቦች ወዲያውኑ ለፖሊስ በሰጡት መረጃ ለጥፋት ድርጊት የተላኩት እነሱን ጨምሮ 50 ያህል ሰዎች መሆናቸውንም እንዳስረዱም ...

Read More »

በአማራ ክልል ሊካሄዱ የታሰቡ የኢንዱስትሪ ልማቶችን ለመደገፍ የተመደበ 4.5 ቢሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መተላለፉ በብዓዴን አባላት ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአማራ ክልል ሊካሄዱ የታሰቡ የኢንዱስትሪ ልማቶችን ለመደገፍ ሲሰጥ የነበረ 4.5 ቢሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መተላለፉ በብሄረ-አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብዓዴን) አባላትና ደጋፊ ዘንድ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ። የፓርቲው አመራሮች ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱት ልዩ ጉባዔ ወቅት የዚህ ገንዘብ ዝውውር ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡንና በድርጊቱ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ጠንካራ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተሳታፊ እማኞች ...

Read More »

በውጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ኢህአዴግ ከስልጣን እንዲወርድ፣ የትግራይ ተወላጆች ህዝባዊ ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ጠየቁ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካና የተለያዩ ሃገራት የሆነ የትግራይ ተወላጆች ገዥው የኢህአዴግ መንገስት ከስልጣን እንዲወርድና በሃገሪቱ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም፣ የትግራይ ተወላጆች በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪን አቀረቡ። 36 የሚሆኑ የቀድሞ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አመራሮችንና አባላትን ያካተተ አንድ ቡድን የትግራይ ተወላጆች ያላቸው አስተዋፅዖ እና ሚና እንዲጠናከር ለማድረግ ዘመቻን እያካሄደ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በተለያዩ ...

Read More »

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረገው ምክክርና ስልጠና ከመምህራን ዘንድ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመካሄድ ላይ ያለው ምክክርና ስልጠና ከመምህራን ዘንድ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ታውቋል። መምህራኑ በአወያዮች ከቀረበው አጀንዳ በተጨማሪ ወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች በመወያያነት እንዲነሱ ጥያቄን ቢያቀርቡም ከአወያዮች ተቀባይነት አለማግኘቱን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ መምህራን ገልጸዋል። መምህራኑ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተከትሎም መምህራኑ በመድረኩ ምንም አይነት አስተያየትና ምላሽ ...

Read More »

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ለምክክሩ ቅድመዝግጅት ፈቃደኛ አልነበሩም በሚል ውንጀላ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምክክር ጋር በተያያዘ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ለምክክሩ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ፈቃደኛ አልነበሩም ተብለው ከሃላፊነታቸው ተነሱ። ከቀናት በፊት ለአመታት ካገለገሉበት ሃላፊነት የተነሱን ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ በበኩላቸው፣ የትምህርት ሚኒስቴር ለስንብቱ የሰጣቸው ምክንያት ትክክለኛ አለመሆኑንና ካህገር አቀፍ ስልጠናና ምክክር ተሳታፊ እንደነበሩ ምላሽን ሰጥተዋል። ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ ለስልጠናው ቅድመ ዝግጅት ትብብር ...

Read More »

ኦህዴድ አቶ ሙክታር ከድርንና ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከሃላፊነት አሰናበተ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ለወራት ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሙክታር ከድርንና ምክትል ሊቀመንበሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከሃላፊነት አሰናበተ። በተሰናበቱት የኦህዴድ አመራሮች ምትክ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ...

Read More »

በጎንደር ባህርዳር እና አዲስ ዘመን የተጀመረው ህዝባዊ የስራ ማቆም አድማ ለ3ኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

መስከረም ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገዛዙ ወታደሮች በጉልበት የንግድ ድርጅቶች እንዲከፈቱ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ውለዋል። በአዲስ ዘመን የተሰማሩት የአጋዚ ወታደሮች ሱቆቻቸውን የማይከፍቱትን አስረዋል። በባህርዳር ደግሞ በርካታ ነጋዴዎች ከታሰሩ በሁዋላ ለቤተሰቦቻቸው ስልክ እየደወሉ ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ ለማስገደድ ተሞክሯል። በጎንደር ህዝቡ ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ ለተቸገሩት ነዋሪዎች ምግብ በጋራ ሆኖ እያቀረበ ነው። በከተሞች ታሪክ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ...

Read More »