Author Archives: Central

በሳውዲ አረቢያ አንድ ኢትዮጵያዊት የሞት ቅጣት ተፈጸመባት

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) በቅርቡ በአንድ የሳውዲ አረቢያ ህጻን ላይ ግድያን ፈጽማለች ተብላ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባት ኢትዮጵያዊት ሰኞ በመቅላት ድርጊት የሞት ቅጣት እንደተፈጸመባት የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ገለጹ። በ20ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያዊት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኒታ የአሰሪዎቿን ታዳጊ ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሏን የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የአገሪቱ ፍ/ቤት በተከሳሿ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔን ቢያስተላልፍም፣ ኢትዮጵያዊቷ ግድያውን በምን ምክንያት እንደፈጸመች የታወቀና ...

Read More »

የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ቀውስ አስመልክቶ ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009) በኦሮሚያና አማራ ክልል እየተከሰተ ባለው ህዝባዊ እምቢተኝነትና እሱን ተከትሎ የመጣው አለመረጋጋት በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ላይ ስጋት መፍጠሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሃላፊ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ገለጹ። ችግሩ በሚፈታበት ሁኔታ ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር መነጋገራቸውንም የአሜሪካን አቋምን በሚተነትነው ርዕሰ አንቀጽ አስፍረዋል። ኒውዮርክ እየተደረገ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት በአሜሪካ ...

Read More »

መንግስት ለውጭ ኩባንያዎች መሬት በሊዝ ኢንቨስትመንት መስጠቱን አቋርጫለሁ ቢልም፣ በኦሮሚያ ክልል ለህንድ ኩባንያ መሬት መስጠቱ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ለውጭ ኩባንያዎች በሊዝ የኢንቨስትመንት መሬት መስጠት ማቋረጡን ቢያሳውቅም፣ አንድ የህንድ የመድሃኒት ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል ከ4ሺ ስኩዌር ሜትር በላይ መሬት ለ45 ዓመት በሊዝ መረከቡን ሰኞ ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለውጭ ኩባንያዎች ሲሰጥ የቆየውን ሰፋፊ የእርሻ መሬት በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራን አስከትሏል በማለት መሬት የመስጠቱ ሂደት ከሶስት ወር በፊት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ማድረጉ ...

Read More »

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ ተማሪዎች የምደባ ቦታን ለመቀየር በት/ሚኒስቴር ባለስልጣናት ክፍያ እንደሚጠየቁ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009) በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ለወራት የዘለቀውን ህዝባዊ ተቃውሞ ዕልባትን አለማግኘቱን ተከትሎ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን ወደ ተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ ተማሪዎች የምደባ ቦታን ለመቀየር በትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጉን ለኢሳት ገለጡ። ይኸው በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በመፈጸም ላይ ይገኛል ያሉት ሙስና ከትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር የቅርብ ግንኙነት ባላቸው ደላሎችና ለዚሁ ተብለው በተቋቋሙ ድረ-ገጾች አማካኝነት መሆኑንም ምንጮች ...

Read More »

በኢትዮጵያ የባለአደራ መንግስት እንዲቋቋም ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009) ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ፣ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ቀውስ ለመሻገር ባለአደራ መንግስት እንዲቋቋም ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ጥሪ አቀረብ። በተለያየ መንገድ ከሃገሪቱ የተዘረፈውን ገንዘብ በተመለከተም የሂሳብና የህግ አዋቂዎች የሚሳተፉበት የምርመራ ስራ እንዲካሄድና የውጭ አማካሪዎችም ሂደቱን እንዲያግዙ የመፍትሄ ሃሳብ አቅርበዋል። ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ይህንን ጥሪ ያደረጉት ዛሬ ሰኞ መስከረም 16 ...

Read More »

በጎንደርና ባህርዳር አድማቸውን የጨረሱ ነዋሪዎች ወደ ስራ ቢመለሱም አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች እየታሸጉ ነው

መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ6 ቀናት በተከታታይ የተደረገው የጎንደር እና የባህርዳር ከተሞች የስራ ማቆም አድማ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ፣ ህዝቡ ከትናንት ጀምሮ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው ገብቷል። የተቃውሞው አስተባባሪዎች ህዝቡ ባሳየው ጽናትና ጀግንነት ኮርተናል ብለዋል። ከባድ ፈተና ቢሆንም፣ ፈተናው በድል ተወጥተናል በቀጣይም ሌሎች የትግል ስልቶችን ተግባራዊ እናድርጋለን በማለት ተናግረዋል። የሁለቱም ከተሞች ህዝብ በአንድነት በመናበብ ያካሄደውን የስራ ...

Read More »

በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተካሄደው ተቃውሞ የተሳካ እንደነበር መምህራን ገለጹ

መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ የተጠቀሙበት የዝምታ ተቃውሞ፣ ገዢው ፓርቲ ያሰበውን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል ስራ እንዳይሰራ አድርጎታል። ‹‹ በዝምታ ተቃውሞን መግለጽ!! ››  በሁሉም የስብሰባ አዳራሾች ተግባራዊ በመሆኑ፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ንዴታቸውን ለመቆጣጠር ያልቻሉበት ሁኔታ መከሰቱን ያወሱት መምህራኑ፣ በመጀመሪያው  ቀን ምንም አይነት አስተያየት ከመድረክ ያልተሰጠ ሲሆን፣ በሁለተኛ ቀን በተደረገው ስብሰባም ...

Read More »

ኢትዮጵያ ውስጥ በገዢው ስርዓት አማካይነት እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ፣ ግድያ፣ የጅምላ እስርና ስቃይ የሚያወግዙ ሰልፍች በተለያዩ ሀገራት ከተሞች እንደቀጠለ ነው።

መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ውስጥ በገዢው ስርዓት አማካይነት እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ፣ ግድያ፣ የጅምላ እስርና ስቃይ የሚያወግዙ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ለሚደረገው ትግል አጋርነትን የሚገልጹ ሰልፍች እንዲሁም በግፍ ለተሰው ወገኖች የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት የማዳረጉ ሂደት አሁንም በተለያዩ ሀገራት ከተሞች እንደቀጠለ ነው። ያሳለፍነው ቅዳሜ በጀርመኖቹ የፍራንክፈርትና የቩርዝቡርግ ከተሞችም ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት የተከሄደ ...

Read More »

በኖርዌይ  በአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ

መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና በጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅነት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱ በአገራችን የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ከመጨረሻው ግብ ለማድረስ የተያዘው የነጻነት ትግል ለውጤት እንዲበቃ  ምን መደረግ አለበት የሚለውን አጀንዳ በመያዝ ሁሉም ለኢትዮጵያ  ፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን፣ ዲሞክራሲያዊና  ሰብአዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት 7 በደርባን የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ መስራቱን አስታወቀ

መስከረም ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የድርጅቱ አባላትና አስተባባሪዎች እንደገለጹት በደርባን፣ ጆሃንስበርግ፣ ፕሪቶሪያና ራስተምበርግ ለድርጅቱ ማጠናከሪያ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ የተያዘ ሲሆን፣ የመጀመሪያው በደርባን ከተማ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቋል። እሁድ መስከረም 15፣ 2009 ዓም በተካሄደው ዝግጅት ላይ ህዝቡ ለድርጅቱ ያሳየው ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት አዘጋጆች፣ በአገራችን እየተፈጸመ ያለው አፈና እና ግድያ እንዲቆም ተሰብሰባው በጉልበትና በገንዘብ ...

Read More »