ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) በወልቃይት አዲ-ረመጽ ከተማ የሚገኘ አንድ ሆቴል የአማርኛ ዘፈን በመከፈሩ የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት የሃይል ዕርምጃ በነዋሪዎች ዘንድ አዲስ ውጥረት መቀስቀሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ረቡዕ ለኢሳት አስታወቁ። የትግራይ ክልል ልዩ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት በዚህ ዕርምጃ የሆቴሉ ባለቤት ልጅ ክፉኛ የድብደባ ድርጊት እንደተፈጸመበትና የከተማዋ ነዋሪዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል። በአዲ-ረመጽ ከተማ የተቀሰቀሰውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ ...
Read More »Author Archives: Central
የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የዋስትና መብት ጥያቄ በፖሊስ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው ተባለ
ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማክሰኞ ፍርድ ቤት መቅረባቸውንና ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ በፖሊስ ተቃውሞ እንደቀረበበት እማኞች ለኢሳት ገለጹ። በኮሚቴ አባሉ ላይ ምርመራን እያካሄደ መሆኑን ለችሎት ያስታወቀው ፖሊስ፣ ኮሎኔል ደመቀን በሽብርተኛ ወንጀል ድርጊት የሚጠረጥራቸው በመሆኑ ያቀረቡት የዋስትና መብት ተቀባይነት እንዳያገኝ ተቃውሞ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ከፖሊስና ከኮሎኔሉ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ ወረዳ ሁለት ወጣቶች በጥይት ተመቱ
መስከረም ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው መስከረም 17 ቀን፣ 2008 ዓም አንድ የመከላከያ አባል የአሽሬ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ሁለት ወንድማማቾችን በጥይት የመታቸው ሲሆን አንደኛው ወጣት ተማሪ ወዲያውኑ ሲሞት ሌላው ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል። ወታደሩ በወጣቶች ላይ የወሰደው እርምጃ ያበሳጨው ሌላ ወታደር ፣ ገዳዩን ወታደር ገድሎ እና አንዲት ሴት ወታደር አቁስሎ መጥፋቱን የአካባቢው ...
Read More »ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰሱ
መስከረም ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጎንደር ፍርድ ቤት የቀረቡት በእግት ላይ የሚገኙት ኮ/ል ደመቀ ዛሬ ፍርድ ቤት በድብቅ መቅረባቸው የታወቀ ሲሆን፣ የሽብርተኝነት ክስ እንደተከፈተባቸው ታውቋል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስተባባሪ የሆኑት ኮ/ል ደመቀ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ለበርካታ አመታት ያገለገሉ መሆናቸውን እየታወቀ እርሳቸውን በሽብርተኝነት መክሰስ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው በማለት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የብአዴን ከፍተኛ ...
Read More »በጉራጌ ዞን የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ጽሁፎች በስፋት እየተለጠፉ ነው።
መስከረም ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወልቂጤ፣ በቸሀ እና በእንድብር ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ በግድግዳዎችና በዛፎች ላይ የተቃውሞ ጽሁፎች ተለጥፈው ይታያሉ። በየከተሞቹ አደባባይ ላይ ተለጥፈው ከሚታዩት ጽሁፎች መካከል ፦”ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም!፣ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ያነሳው ጥያቄ የኛም ጥያቄ ነው! በአማራና በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ድርጊት እኛንም አሞናል! ጉራጌ ከመርካቶ፣ ከአትክልት ተራ፣ከ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል መንዲ ከተማ በመስቀል በዓል ዋዜማ አንድ ወጣት ተማሪ ተገደለ
ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ስር በምትገኘው የመንዲ ከተማ በመስቀል በዓል አካባበር ዋዜማ ሰኞ አንድ ወጣት ተማሪ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደሉን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። ተደጋጋሚ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱባት በቆየችው የመንዲ ከተማ አሁንም ድረስ የጸጥታ ስጋት መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች የከተማዋ ወጣቶች የደመራ በዓል ዝግጅት እያደረጉ ባለበት ወቅት ወጣቱ በአልሞ ተኳሽ መገደሉን ገልጸዋል። በወቅቱ ምንም አይነት ተቃውሞ ...
Read More »በጎንደር የመስቀል በዓል አለመከበሩ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) ከሃምሌ ወር ጀምሮ ህዝባዊ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ በሚገኝበት የጎንደር ከተማ ማክሰኞ ሊከበር የነበረው የመስቀል በዓል አከባበር አለመከበሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። በዕለቱ የዳመራ የችቦ ማብራት ስነስርዓት አለመከናወኑን የተናገሩት እማኞች በርካታ ነዋሪዎች በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ በመሰባሰብ ተቃውሞ አዘል የሆኑ መልዕክቶችን ሲያስተጋቡ እንደነበር ገልጸዋል። የቪዲዮ መረጃን በማስደገፍ መረጃን ለኢሳት ያደረሱ አካላት የዘንድሮው የመስቀል በዓል አከባበር ከመቼውም ጊዜ ...
Read More »የዩኒቨርስቲ የምደባ ዝውውር አስፈጽማለሁ በማለት ገንዘብ ሲሰበስብ የነበረ ድረገጽ ተዘጋ
ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምደባ ዝውውርን ይፈጸማል ሲሉ ያቀረቡትን የሙስና ቅሬታ ተከትሎ ሲያከናውን የቆየና ንብረትነቱ የማን እንደሆነ ያልታወቀ አንድ ድረ-ገፅ ተዘጋ። ለኢሳት መረጃን የሰጡ ምንጮች ከትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ወገኖች የተለያዩ የምዝገባ ዘዴዎችን በመጠቀም ከአንድ ተማሪ እስከ 10 ሺ ብር የሚደርስ ክፍያ ሲቀበሉ መሰንበታቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ዩኒቨ ኮሌጅ የተሰኘ ድረገጽ ...
Read More »በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ የኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች መስቀልን እጅግ በተቀዛቀዘ ስሜት አከበሩ
መስከረም ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ ታላላቅ ከሚባሉት ሃይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የመስቀል በአል በመላ አገሪቱ እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት መከበሩን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ በአሉ ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው በአደባባይ ያልተከበረ ሲሆን፣ አንዳንድ የከተማዋን ታሪክ የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት ጎንደር የመስቀልን በአል በአደባባይ ሳታከብር ስትቀር ከ100 አመት ...
Read More »በኦሮምያና አማራ ክልሎች የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያወግዝ ሰልፍ በሶማሊ ክልል ተካሄደ
መስከረም ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ቅስቀሳና ማስፈራሪያ በተሰናዳ ሰልፍ በኦሮምያ የሚካሄደውን ተቃውሞ ጠባቦች ያዘጋጁት ነው በማለት ሲወገዝ፣ በአማራ ክልል የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ደግሞ የትምክተኞች ነው ተብሎአል። የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ከጧቱ 12 ሰአት ላይ የፌደራልና ልዩ ሃይል አባላት በየሰዎች ግቢ ውስጥ በመግባት ህዝቡን ወደ ስብሰባ እንዲወጣ አድርገዋል። ወደ ስብሰባው የሚሄዱ ሰዎች በእጃቸው ምንም ነገር እንዳይዙ ...
Read More »