Author Archives: Central

በኳታር የሚኖሩ ህገወጥ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች አገሪቷ በጀመረችው የህገ-ወጥ ስራተኞችን የማስወጣት ዘመቻ ሊወጡ መሆኑን ተነገረ

ኢሳት (ጥቅምት 27 ፥ 2009) በኳታር የሚኖሩ ከሁለት ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ሃገሪቱ በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገችው የህገ-ወጥ ስራተኞችን የማስወጣት ዘመቻ ከኳታር ሊወጡ መሆኑን ተነገረ። የኳታር መንግስት በቅርቡ ያወጣው አዲስ ህግ በቀጣዩ ወር የሚተገበር በመሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሃገራት ህገወጥ የተባሉ ሰራተኞች ህጋዊ እምርጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል የኳታር የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ይኖራሉ የተባሉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች በተሰጠው የሶስት ...

Read More »

የውጭ ሃገር ባንኮች በብድር ማቅረብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 27 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማገዝ ወደ ሃገሪቱ የገቡ የውጭ ሃገር ባንኮች በብድር ማቅረብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተገለጸ። የደቡብ አፍሪካ፣ የቱርክ፣ የኬንያና፣ የአውሮፓ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማገዝ ይችሉ ዘንድ በቅርቡ በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ይታወሳል። ስታንዳርድ የተሰኘ የደቡብ አፍሪካ ባንክ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እያካሄደ ያለውን ስራ ለመደገፍ የ100 ሚሊዮን ዶላር ...

Read More »

በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለመቆየት ወይም ለቆ ለመውጣት በሚሉ አማራጮ ላይ እየመከሩ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአውሮፓ ኩባንያዎች በሃገሪቱ ለመቆየት ወይም ለቆ ለመውጣት የሚሉ አማራጮ ላይ እየመከሩ መሆኑ ተገለጠ። ኩባንያዎቹ በተለያዩ የክልል  ከተሞች ያለው ፖለቲካዊ ውጥረትና በቅርቡ በአንዳንድ ኩባንያዎች ላይ የተቃጣው ጥቃት በኢንቨስትመንት ስራዎቻቸው አማራጮችን እንዲመለከቱ እንዳስገደዳቸው ዘጋርዲያን ጋዜጣ ረቡዕ ዘግቧል። መቀመመጫውን በኔዘርላንድ ያደረገው የአፍሪካ ጁስ ሃላፊ የሆኑት አያን ዴሪ ባለፈው ወር በፋብሪካቸው ላይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናይጀሪያውያን ፓይለቶችን አሰልጥኖ ለመቅጠር እቅድ መያዙን አስታወቀ

ኢሳት (ጥቅምት 26 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተለያዩ የበረራ መስመሮች ናይጀሪያውያን ፓይለቶችን ለማሰልጠንና ለመቅጠር እቅድ መያዙን አስታወቀ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ የውጭ ሃገር ዜጎችን በተለያዩ የበረራ ዘርፎች እያሰማራ የሚገኘው አየር መንገዱ ለሃገር ውስጥ ተማሪዎችና ባለሙያዎች ቅድሚያን አልሰጠም በሚል ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወሳል። 70ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር በናይጀሪያ ሌጎስ ከተማ ዝግጅት የአየር መንገዱ ተወካዮች ናይጀሪያዊያን ፓይለቶችን ለማሰልጠንና ለመቅጠር አዲስ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ከሶማሊያ ለቀው ለመውታጣቸው አለም አቀፍ ማህበረሰብ ተጠያቂ አደረገች

ኢሳት (ጥቅምት 26 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በሶማሊያ ተሰማርተው የሚገኙ ወታድሮቿ ከቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው ለመውጣታቸው የአለም አቀፍ ማህበረሰብን ተጠያቂ አደረገች። በተያዘው የጥቅምት ወር ብቻ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶስት ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡ ሲሆን፣ የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ሶስቱን ስፍራዎች ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የአለም አቀፍ ማህበረሰብ መስጠት የነበረበትን ድጋፍ ባለመስጠቱ ምክንያት ክፍተት መፍጠሩንና ታጣቂ ...

Read More »

ወታደራዊ ምዝገባ ለማካሄድ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰራዊቱ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም እየጠፋ በመምጣቱ የሃይል መሳሳት ያጋጠመው አገዛዙ፣ ወጣቶችን ወደ ውትድርና ስልጠና ለመውስድ አዲስ ማስታወቂያ እያስነገረ ቢሆንም፣ ጥሪው ተቀባይነት አላገኘለትም። በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ወጣቶች እንዲመዘገቡ የሚያሳስቡ ማስታወቂያዎች እንየተነገሩ ነው። ቀደም ብሎ በግልጽ ይወጣ የነበረው የወታደር የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት ማጣቱ በሚዲያ ከተዘገበ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም እንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞና ተቃውሞውን ተከትሎ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በእያመቱ ከ3 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ ገቢ የሚያስገኘውን የቱሪዝም እንዱስትሪ ክፉኛ እንደጎዳው ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል። ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ችግር የሌለባቸው በመሆኑ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚችሉ ቢናገርም፣ የውጭ አገር የአስጎብኝ ድርጅቶች አማካሪዎች ግን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ...

Read More »

በሃረሬ ክልል ካደሬዎች ሰዎች ቤት በድንገት እየገቡ “ኢሳትን ታያላችሁ ወይ?” እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ወኪላችን እንደገለጸው ባለፈው ሳምንት ህዝቡ ዲሽ እንዲያወርድ ማስጠንቀቂያ ከቀረበለት በሁዋላ፣ ካድሬዎች በድንገት ወደ ግለሰቦች ቤት ዘው ብለው በመግባት “ እንዴት ነው ኢሳትን ታያላችሁ?” እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው።አብዛኛው ህዝብ ኢሳትን ለማየት ሌሎች አማራጮችን እየተጠቀመ ነው። ኢሳትን ከማየት ሙሉ በሙሉ የሚከለክለን ነገር የለም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ኢሳትን ለማየት ለሚዲያ ፍጆታ የማይውሉ ...

Read More »

የቪዥን ኢትዮጵያ ወይም ራዕይ ኢትዮጵያ  ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የሽግግር ካውንስል እንዲቋቋም ጥሪ አቀረቡ።

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ይህን ጥሪ ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት  በዋሽንግተን ዲሲ ቪዥን ኢትዮጵያ -ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ-ኢሳት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው  ኮንፈረንስ መጠናቀቁን ተከትሎ ባወጡት ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ  የሚቋቋመው የሽግግር ካውንስል አዲስ ሪፐብሊክና አዲስ የአንድነት መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ሰላማዊና የተረጋጋ የሽግግር ሁኔታ እንዲፈጠር ነገሮችን የሚያመቻች ነው። ካውንስሉ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ጦር ይዞዋቸው የነበሩትን ከተሞች አልሸባብ ተቆጣጠራቸው

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በያዝነው ዓመት በታይግሎ አውራጃ በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እና የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች በተደጋጋሚ ጊዜያት ከአልሸባብ ጋር ከባድ ውጊያዎችን አድርገዋል። ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የምትገኘው ስትራቴጂካዊውን የታይግሎ ወረዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እና የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች ለአልሸባብ በመተው ወደ  ሁዱር እና ቦቆል ሸሽተዋል። በያዝነው ወር ብቻ ...

Read More »