Author Archives: Central

በአማራ እና በሌሎችም ክልሎች እስራቱና ድብደባው በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ኮማንድ ፖስት በሚል ባቋቋመው የአፈና መዋቅሩ የአማራ ክልል ወጣቶችንና የመንግስት ሰራተኞችን ኢላማ  በማድረግ ከፍተኘ ስቃይ እየፈጸመ ነው። ህወሃት የበቀል ጅራፉን በክልሉ ዜጎች ላይ አሳርፎአል የሚሉት ነዋሪዎች፣ ድርጊቱ ወደ አልተፈለገ ደም መፋሰስ ሊያመራ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው። ባለፉት አራት ቀናት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው በገፍ ወደ እስር ...

Read More »

በእነዋሬ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ከአካባቢያቸው  ከሚዘረፈው  ማዕድን ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን ከእነዋሪ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የወረዳዋ ሃብት ከሆኑ ተራራዎች ለሲሚንቶ አገልግሎት ሊውል የሚችል ማዕድን በየቀኑ እየተጫነ መጓጓዙ አግባብ አለመሆኑን በእነዋሬ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በየቀኑ የሚመላለሱት ከባድ የጭነት ተሸከርካሪዎች የከተማዋን መንገድ በማፈራረስ ላይ መሆናቸውንም የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው  የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ሊሆን የሚገባው የአካባቢው ማህበረሰብ መሆን ሲገባው ...

Read More »

የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጸሃፊ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ለሚታየው ችግር አስቸካይ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠየቁ

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ሕብረት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኒኮላ ዛና ዲላሚኒ ዙማ በኢትዮጵያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ አስመልክቶ ሁሉን ያሳተፈ አስቸኳይ የሆነ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርብዋል። ዋና ጸሃፊዋ ሁሉንም ያሳተፈ ድርድር ማድረግ ለአገሪቷ የመጨረሻ አስተማማኝ እና ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ያስገኝላታል ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች እና ...

Read More »

የቀበና ችግኝ ጣቢያ ቦታ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤት መስሪያ ተሰጠ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ10 ሺ ካሬ መሬት በላይ ስፋት ያለው የቀበና ችግኝ ጣቢያ ተነስቶ ፣ ቦታው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን መኖሪያ ቤት መስሪያ ተሰጥቷል። ግንባታው የሚካሄደው በመንግስት ወጪ ሲሆን፣ ወ/ሮ አዜብ ቦታውን በስማቸው አዙረዋል።የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ቦታውን ለቤተመንግስት ሰዎች እንዲያስረክብ የተጠየቀበት፣እንዲሁም የከንቲባ ጽ/ቤት ለቦሌ ክፍለ ከተማ መስተዳደር የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች እና ሌሎችም ...

Read More »

በርካታ የጎንደር እስር ቤቶች በእስረኞች ተጨናንቀዋል ተባለ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮማንድ ፖስት እያለ ራሱን የሚጠራው የህወሃት/ኢህአዴግ የአፈና መስመር ዛሬ በጎንደርና ባህርዳር እንዲሁም በዙሪያ ከተሞች ከፍተኛ አፈሳ ሲያካሄድ ውሎአል። በጎንደር ቀበሌ 2፣ 4 እንዲሁም 14 በርካታ ሰዎች ኢሳትን ታያላችሁ በሚል መታሰራቸውን ተከትሎ እስር ቤት በእሰረኞች ተጨናንቀው ታይተዋል።ፖሊሶች ጣራ ለጣራ እየወጡ ዲሽ ሲነቅሉ መዋላቸውም ታውቋል። በዳባትም እንዲሁ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በባህርዳር ...

Read More »

የአቶ አንዳርጋቸው የደኅንነት ሁኔታ እንዳሰጋው ሪፕሪቭ አስታወቀ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ታግተው የተወሰዱት የነፃነት ታጋዩ የአቶ አንዳርጋቸው የደኅንነት ሁኔታ እንዳሰጋው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው የህግ ባለሙያዎች ስብስብ አስታውቋል።የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ የሞት ቅጣት ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኘው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚገኝና  የደኅንነቱ ሁኔታ ...

Read More »

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርና ደህንነት ግልፅ እንዲደረግ ተጠየቀ

ኢሳት (ጥቅምት 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርና የደህንነት ሁኔታ ግልጽ እንዲደረገ ተጠየቀ። አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተካሄደ ባለው የእስር ዘመቻ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትን ጨምሮ በርካታ መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ እስር ቤት መለወጣቸውን ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ይሁንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊነት የሚከታተለው ኮማንድ ፖስት ለእስር የተዳረጉ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥርና የደህንነት ...

Read More »

የካናዳ ፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ግፊትን እንዲደርግ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፓርላማ አባላቱ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቀረበ

  ኢሳት (ጥቅምት 25 ፥ 2009) የካናዳ ፓርላማ አባላት የሃገራቸው መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ግፊትን እንዲያደርግ በቅርቡ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በሃገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፓርላማ አባላቱ ጋር ለመወያየት ጥያቄን አቀረበ። አሌክሳንደር ኖቴል የተባሉ የካናዳ የፓርላማ አባላት በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን መግለጻቸው ይታወሳል። የፓርላማ አባሉ በፓርላማ ያቀረቡት ንግግር መነጋገሪያ እየሆነ መምጣቱን ለኢሳት የገለጹት ምንጮች ድርጊቱን ...

Read More »

ሪፕሪቭ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ መግለጫ አወጣ

ኢሳት (ጥቅምት 25 ፥ 2009) የብሪታኒያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ “ለህይወቴ” ስጋት አድሮብኛል ሲሉ መግለጻቸውን ይፋ እንዳደረጉ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው የሃገሪቱ የሰብዓዊ መግብት ተሟጋች ተቋም ገለጠ። ሪፕሪቭ የተሰኘው ይኸው ተቋም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለፈው ሳምንት ያቀረቡት ስጋት ለቤተሰቦቻቸው በባለስልጣናት በኩል እንዲደርሳቸው መደረጉን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይገኙበታል የተባለው እስር ቤት ውስጥ ሁከት ተፈጥቶ እንደነበር ያስታወቁት ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ዎች ይፋ ባደረጋቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ጋር ለመወያየት እንደሚፈልግ ገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 25 ፥ 2009) የአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሂዩማን ራይትስ ዎች በቅርቡ ይፋ ባደረጋቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ጋር በማንኛውም ስፍራ በአካል በመገኛኘት ለመወያየት እንደሚፈልግ አርብ ገለጠ። ድርጅቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸውን ሪፖርቶችን ተከትሎ የቀድሞ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኢስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰፊ ምላሽን በመስጠት ተፈጽሟል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና ሂውማን ራይትስ ...

Read More »