ኢሳት (ህዳር 2 ፥ 2009) በወህኒ ቤት የሚገኙ የኦፌኮ ም/ፕሬዚደንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተገለጸ። አርብ ህዳር 2 ቀን 2009 ፍ/ቤት መቅረብ ከሚገባቸው 22ቱ ተከሳሾች ውስጥ አምስቱ በችሎት ያልተገኙ ሲሆን፣ ከመካከላቸው አንደኛው የት እንደሚገኙ አላውቅም ሲል አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል። በችሎቱ ሳይገኙ ከቀሩት አምስቱ ተከሳሾች ማለትም ገላና ነገራ፣ ገመቹ ሻንቆ እንዲሁም ደረጀ መርጋ ...
Read More »Author Archives: Central
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ ከ 11ሺ ሰው በላይ መታሰሩ ተገለጸ
ኢሳት (ህዳር 2 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ ከ11,000 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዋጁ አስፈፃሚ መርማሪ ቦርድን በመጥቀስ የስርዓቱ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘግበዋል። ቦርዱ ይፋ እንዳደረገው በስድስት የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማጎሪያ ጣቢያዎች 11 ሺህ 607 ሰዎች በቁጥጥር ስር ቢገኙም ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አካላት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥሩ ከዚህ እጅግ ሊበልጥ እንደሚችል በመግለጽ ላይ ናቸው። ረቡዕ በአውሮፓ ...
Read More »የብሪታኒያ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁኔታ ለማወቅ አለመቻሉን ገለጸ
ኢሳት (ህዳር 2 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃሊቲ ታስረው ከሚገኙት ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡን ሪፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ ተቋም አስታወቀ። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሁለት ሳምንት በፊት በወህኒ ቤት በተፈጠረ አለመግባባት ለህይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ እንደሚገኙ ይኸው ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚከራከረው ድርጅት የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ዋቢ በማድረግ ገልጿል። የብሪታንያ ኮሱላር ቢሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ...
Read More »በወገራ በነጻነት ሃይሎችና በወታደሮች መካከል ያለው ፍጥጫ ቀጥሎአል
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ የነጻነት ሃይሎች ከህዝብ ጋር በመተባበር በመንግሰት ታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሱ በሁዋላ፣ አሁንም ፍጥጫው መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። እነዚህ ራሳቸውን ያደራጁ ሃይሎች እንደገለጹት፣ ከትናንት ጀምሮ ቀሳውስቱ በመካከላቸው ትልቅ መስቀል በማቆም ጦርነቱ እንቆም ቢያደርጉም አሁንም ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዞ ተፋጦ ይገኛል። ወታደራዊ አዛዦች ...
Read More »የኮንሶ ህዝብ መሪዎች እየታደኑ ነው
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ያቀረበውን ጥያቄ በሃይል ለመጨፍለቅ ተደጋጋሚ የአፈና እርምጃ ሲወስድ የቆየው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ተቃውሞውን ያስተባብራሉ ያላቸውን የአካባቢውን የአገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለመያዝ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ብዙዎች ራሳቸውን ለመደበቅ ተገደዋል። አገዛዙ፣ መሪዎቹን በአሸባሪነት የፈረጃቸው ሲሆን፣ በተገኙበት እንዲያዙ አልያም እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠቱን መንጮች ገልጸዋል። ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ ተፈላጊ ሰዎችን ጠቁሙ እየተባሉ ስቃይ እየደረሰባቸው ...
Read More »ጸሃፊ በፈቃዱ ሃይሉ ታሰረ
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ፖለቲካዊ ትችቶችንና መረጃዎችን በመጻፍ የሚታወቀው በፈቃዱ ሃይሉ ህዳር 02/2009 ዓም “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋሀል” ተብሎ በፖሊስ ተጠርቶ በድጋሜ ለእስር ተደርጓል። በ2006 ዓም ዞን ዘጠኝ እየተባሉ ከሚጠሩ ጻሃፊዎች ጋር ታስሮ ከ18 ወራት የእስር ጊዜ በሁዋላ በ20 ሺ ብር ዋስ የተፈታው በፈቃዱ ፣ ከእስር ከወጣ በሁዋላ ውይይት መጽሄት ላይ በዋና አዘጋጅነት የስራ ...
Read More »በአፋር ክልል በዞን ሶስት የኮሌራ በሽታ የነዋሪዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በዞን ሶስት በገዋኔ፣ ቡሪሞዳይቶና አሚባራ ወረዳዎች ውስጥ የተከሰተው ከፍተኛ የኮሌራ ወረርሽኝ ህጻናትንና አዛውንቶችን እየቀጠፈ ነው። እስካሁን ድረስ ለበሽታው በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ የጉዳት መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።
Read More »በደቡብ ክልል በሃመር ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ የፖሊስ አባል ተገደለ፥ በአካባቢው ውጥረት እንደነገሰ ነው
ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009) በደቡብ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ስር በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች በጸጥታ ሃይሎችና በሃመር ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ የፖሊስ አባል መገደሉንና በአካባቢው ውጥረጥ መንገሱን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአልድባ ቀበሌ እና በአካባቢው በሚገኙ አጎራባች ቀበሌዎች በነዋሪዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ከዜና ዝግጅት ክፍላችን ጋር ቃለምልልስን ያደረጉ እማኞች ገልጸዋል። በዞኑ ስር ...
Read More »ከቱሪዝም ዘርፍ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ የ7.4 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት መመዝገቡ ተገለጸ
ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009) ባለፉት ሶስት ወራቶች ብቻ ከቱሪዝም ዘርፍ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ የ7.4 ሚሊዮን ዶላር (150 ሚሊዮን ብር አካባቢ) ጉድለት መመዝገቡን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሃሙስ ይፋ አደረገ። ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ለገቢው መቀነስ ምክንያት መሆኑን የገለጸውን ሚኒስቴር በአመት ሊገኝ ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው ገንዘብ ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ሊያጋጥም እንደሚችል አመልክቷል። በተያዘው በጀት ...
Read More »በኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ላይ የጉዞ እገዳ ቢነሳም፣ ተጨማሪ ክልከላዎች ሊደረጉ ይችላሉ ተባለ
ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ በሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ መነሳቱ ይፋ ቢደረግም፣ በማንኛውም ሰዓት ተጨማሪ ክልከላዎች ተግባራዊ ሊደረጉ እንደሚችል አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ከ 40 ኪሎሜትር በላይ ርቀው መሄድ ከፈለጉ ጉዳዩ ከሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ መውጣቱ ይታወሳል። የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረትና ...
Read More »