ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ሳምንታት የድርጅቱ ታጣቂዎች በቃፍታ ሁመራ፣ አዲ ጎሹና አርማጭሆ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ ቃኝ ወታደሮች ጋር ተከታታይ የተኩስ ልውውጦችን አድርገዋል።በተኩስ ለውውጡ ከመንግስት በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ ቢሆንም፣ ከነጻነት ሃይሎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ድርጅቱ ምርመራ እያደረ መሆኑን ገልጿል። “የንቅናቄው ሃይሎች አንዳንድ ቦታዎችን ...
Read More »Author Archives: Central
በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የተጠራው ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ የመንግሥት ሠራተኞችን ለይተው ‹‹በወቅታዊ ጉዳዮች›› ላይ ለማወያየት የተጠራው ስብሰባ ሠራተኛው በስብሰባው ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይሳካ መቅረቱን የከተማው ሠረተኞች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሰኞ ህዳር 12/2009 ዓ.ም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ ገበታው ሲገባ የቢሮ ኃላፊዎች የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑትን ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ እየተባባሰ ቢመጣም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እርዳታ ለማከፋፈል ሳንካ ፈጥሯል ተባለ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አጥኚ ቡድን ከ ኢትዮጵያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የድርቅ አደጋ ያንዣበባቸውን አካባቢዎች ለይተው አውጥተዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ አርብቶ አደሮች ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። ለጉዳተኞቹ እርዳታዎችን ለማሰራጨት አስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው እና መንገዶች ዝግ መደረጋቸው የሰዎችን ሕይወት ለመታደክ ከፍተኛ ሳንካ ፈጥሯል። ...
Read More »የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ የታፈሱት ወጣቶች ይፋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ታስረዋል
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ ከተለያዩ የሃገሪቱ ስፍራዎች ታፍሰው የታሰሩት እስረኞች ገሚሶቹ በአዋሽ አርባ፣ በኦሮሚያ ፖሊስና በቀድሞው ህጻናት አምባ አሁን አላጌ የግብርና ኮሌጅ በመባል በሚጠራው ስፍራ እንደሆነ ታውቋል። መንግስት አዋጁን ለማስከበር በሚል ከ20ሺ እስከ 30ሺ ይደርሳል ተብሎ የሚገመቱ ታሳሪዎችን ቤተሰብና ዘመድ ሊያውቀው በማይችልበት ስፍራ ወስዶ ማሰሩ በታሳሪዎቹ ላይ የስነ ልቦና ጫና ...
Read More »በሶማሊያዋ ኪስማዩ ከተማ 3 የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በቦንብ ተገደሉ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊዋ የሶማሊያ ወደብ ከተማ ኪሲማዩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ጦር የሆኑት ሶስት የኢትዮጵያ መከላከያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቅዳሜ እለት በቦንብ ፍንዳታ ተገድለዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ከኪሲማዩ ከተማ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትከኘው ከማእድን ማውጫዋ ቡሉ ጋዱድ መንደር በወታደራዊ ኮንቮይ መኪና ተጭነው ሲመጡ ጥቃቱ እንደደረሰባቸው የአካባቢው ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆነ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አሜሪካ ጥሪ አደረገች
ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009) አሜሪካ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን አስተዋጽዖ አድርገዋል በተባሉ አካላት ላይ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ማዕቀቦችን እንዲጥል ጥረት እያደረገች መሆኗን ገለጠች። ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የደቡብ ሱዳን መንግስትና በሪክ ማቻር የሚመራው የአማጺ ቡድን ስምምነት እንዲደርሱ ቢደረጉም ሁለቱ ወገኖች ዳግም ወደ ግጭት መግባታቸው ይታወቃል። በደቡብ ሱዳን መንግስትና በአማጺ ቡድኑ መካከል በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰውን ግጭትና ...
Read More »በኢንተርኔት ላይ የተጣለው እገዳ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን ወደማይችሉበት ደረጃ እየወሰዳቸው መሆኑን የተመድ ወኪሎች ገለጹ
ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009) መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የተባበሩት መንግስታት ወኪል ድርጅቶች መንግስት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የጣለው እገዳ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን ወደማይችሉበት ደረጃ እየወሰዳቸው መሆኑን ገለጡ። በተለይ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እረዳታ በተጋለጡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦትን ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ያሉ ተቋማት አለም አቀፍ ግንኙነት ለማድረግ እና ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ የተመድ የዜና አውታር የሆነው ኢሪን አርብ ዘግቧል። የኢንተርኔት አገልግሎት ...
Read More »ከውጭ ንግድ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ተመዘገበ
ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009) በተያዘው አመት ሩብ አመት ከውጭ ንግድ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት መመዝገቡን የንግድ ሚኒስቴር አርብ አስታወቀ። በሩብ አመቱ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለማግኘት እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ከውጭ ንግዱ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ወደ 640 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ብቻ መሆኑ ታውቋል። የምርት ጥራት ጉድለት እንዲሁም በአቅራቢዎችና በላኪዎች እጅ የሚገኝ የግብርናና ...
Read More »የኢትዮጵያ የግብርና እድገት ከሶስት በመቶ በላይ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ባለፈው አመት የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ የግብርና እድገት ከሶስት በመቶ በላይ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ። በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የውጭ ሃገርና አለም አቀፍ ተወካዮች ጋር ውይይትን ያካሄዱ የመንግስት ባለስልጣናት ባለፈው አመት በኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ዙሪያ ከፍተኛ ችግር ማጋጠሙን አረጋግጠዋል። ባለፉት 10 አመታት ስምንት በመቶ ሲያድግ ነበር የተባለው የግብርና ዕድገቱ ወደ ...
Read More »ከሶማሊያ የወጡ የኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቁጥር 12ሺ በላይ እንደሚሆን ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009) በቅርቡ ከሶማሊያ ቁልፍ ከተባሉ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡ የኢትዮጽያ ወታደሮች ቁጥር ወደ 12ሺ አካባቢ እንደሚደርስ አፍሪካ ኮንፊደሻል የተሰኘና በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ዘገባን የሚያቀርብ መጽሄት ዘገበ። የኢትዮጵያ ወታደሮች ባኮ፣ ሂራን እና ጋልጋዱድ ከሚባሉ የማዕከላዊና ደቡባዊ የሶማሊያ ግዛቶች ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል። በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ዘገባን ያቀረበው መጽሄቱ ከሶስቱ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎችና የማዘዣ ጣቢያዎች ለቀው ...
Read More »