ኢሳት (ህዳር 13 ፥ 2009) የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በሃገሪቱ ፕሬዜዳንት ጃኮብ ዙማ ላይ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበን የሙስና ቅሬታ ለመመርመር መወሰኑ ተገለጸ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከበርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ተቃውሞ እየቀረበባቸው የሚገኙት ዙማ ስልጣናቸውን በመጠቀም የመንግስት ሃብትን እንደመዘበሩ የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ሃይሎችና ሌሎች የሲቪክ ተቋማት ቅሬታን እያቀረቡ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ከእነዚሁ አካላት የቀረበን የሙስና ቅሬታ ለመመርመር የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ውሳኔ ላይ የደረሰ ...
Read More »Author Archives: Central
የወልቃይት ማንነት ጥያቄ በሃገሪቱ ለተከሰቱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች መነሻ በመሆኑ ባስቸኳይ ይፈታ ዘንድ የምክር ቤት አባላት ጠየቁ
ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ምክር ቤት በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ የተገኙ የልዩ ልዩ ወረዳ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ባነሱት ጥያቄ የድንበር መካለሉ ጉዳይ ለበርካታ የሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኖ እያለ ምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት ጉዳዩ ወደ የሚመለከተው አካል ተላልፏል መባሉ እንዳልተዋጠላቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በክልሉ ለተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ መንስዔ የመንግስት የመዘናጋት ውጤት እንደሆነ ...
Read More »በቤንሻንግል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መሬታቸውን ያለ ከሳ እየተቀሙ መሆኑን ገለጹ
ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው በክልሉ ተወልደው ያደረጉ የአማራ ተወላጆች እንደገለጹት ቀደም ብሎ በነበረው መንግስት በሰፈራ ፕሮግራም አማካኝነት አሁን ቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ሄደው እንዲሰፍሩ ከተደረገና ልጆችን ወልደው፣ ቤት ንብረት አፍርተው ለአመታት ከኖሩ በሁዋላ፣ የአገዛዙ ሹሞች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጫና እየፈጠሩባቸው ነው። ነዋሪዎቹ ልማት ላይ ያልዋሉ ቦታዎችን ገንዘባቸውን፣ ...
Read More »በኢትዮጵያ በምርት መሰብሰቢያ ወቅት የዋጋ ንረት መከሰቱን የዓለም ምግብ ድርጅት ወርሃዊ ጥናት አስታወቀ
ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየዓመቱ እየባሰበት የመጣው የኢትዮጵያ የዋጋ አለመረጋጋት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የማእከላዊ ስታስቲክ ጽፈት ቤትን ዋቢ በማድረግ የዓለም የምግብ ድርጅት በወርሃዊ የጥናት ሪፖርቱ አመላክቷል። ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ 5.6% የነበረው የምግብ ፍጆታ በሕዳር ወር ወደ 3.4% ከፍ በማለት ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአገሪቱ ውስጥ የዋጋ ንረት ማስከተሉን የደንበኞች የዋጋ አመላካች Consumer Price Index ...
Read More »ዶክተር አብርሃም ይሳቅ በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የመጀመሪያው ቤተእስራኤላዊ ኮሎኔል ሆነው ተሾሙ
ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ19 ዓመታቸው ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተጓዙት ኮሎኔል ይስሃቅ፣ በወታደራዊ ሕክምና አገልግሎት በዶክተርነት ሲገለግሉ መቆየታቸው ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
Read More »ኬንያ በሰላም አስከባሪ ሃይል ስር በሶማሊያ ያሰማራችውን ጦሯን እንደምታስወጣ ገለጸች
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰማርቶ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይል ውስጥ ወታደሮቿን አሰማርታ የምትገኘው ኬንያ ከሃገሪቱ ለቃ እንደምትወጣ ይፋ አደረገች። ሃገሪቱ ሶማሊያ የሚገኘውን ጦሯን በማስወጣት ስትወስን ሶስተኛ ሃገር ስትሆን፣ ዩጋንዳና፣ ቡሩንዲ በቅርቡ ተመሳሳይ ውሳኔን ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካታኖ፣ የኬንያ የሰላም አስከባሪ ሃይል ከአንድ አመት በኋላ ከሶማሊያ ለቆ መውጣት እንደሚጀምር ለመገናኛ ...
Read More »በኮሎምበስ ኦሃዮ ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚሁ በአሜሪካ የኦሃዮ ግዛት ኮሎምበስ ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን ገቢው ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዕሁድ አካሄዱ። የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በተካሄደው በዚሁ ዝግጅት በኮሎምበስ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢሳትን በተለያየ ጊዜ ለመደገፍ ፍላጎትን ማሳየታቸውን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለዜና ዝግጅት ክፍላችን አስረድተዋል። በዕለቱ ኢሳትን ለመደገፍ በተከናወነ ስነ-ስርዓት ከ27ሺ ዶላር በላይ ገቢ መሰባሰቡን ...
Read More »በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ እየተዛመተ ያለው የድርቅ አደጋ እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ ወደ አጎራባች ዞኖች በመዛመት ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድጋሚ ገለጸ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኙ የባሌ፣ ጉጂ፣ እና ቦረና ዞኖች በአዲስ መልክ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በአካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ እንደከተቱ ድርጅቱ አስታውቋል። ከደቡባዊ ምስራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች ...
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡት በሎጂስቲክ ችግር ምክንያትና ለስልታዊ ዕርምጃ ነው ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁልፍ ከተባሉ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡት በሎጂስቲክ ችግር ምክንያትና ለስልታዊ ዕርምጃ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ተወልደ ሙሉጌታ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል የኢትዮጵያ ወታደሮች ለቀው የወጡ ስፍራዎችን መያዙ ለመንግስት ስጋት የለውም ሲሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የሶማሊያ ባለስልጣናት እና የተለያዩ አካላት በሃገሪቱ የሚገኙ ...
Read More »አትላስ አፍሪካን ኢንዱስትሪስ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ገንዘብ ያለ አግባብ አግዶብኛል በማለት ቅሬታን ያቀረበ አንድ አለም አቀፍ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱን ይፋ አደረገ። አትላስ አፍሪካን ኢንዱስትሪስ የተሰኘው ይኸው ኩባንያ ለራያ ቢራ አፍሪካ የቢራ ምርት ማሸጊያ ጠርሙሶችን ለማምረት ስምምነት አድርጎ የሽርክና ስራ ሲሰራ መቆየቱን አውስቷል። ይሁንና ኩባንያው የሽክርና ስራው በጀመረ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ገቢዎች ...
Read More »