ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢ የተካሄደን ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች በኬንያ ሞምባሳ ከተማ የጸጥታና ደህንነት ውይይት በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባት (ኦነግ) ታጣቂዎችን ለመያዝ በሚል በተደጋጋሚ የኬንያን ድንበር እየጣሰች መግባቷ በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት መፍጠሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ባለፈው ወር የኬንያ ድንበር ጥሰው የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስድስት የኬንያ ፖሊሶችን ...
Read More »Author Archives: Central
በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩና ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉ የውጭ ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት እየተደረገ ነው ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) የአሜሪካና የብሪታኒያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉና በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሃሙስ አስታወቁ። የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው እነዚሁ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ፓይለቶች አፍሪካን በሚሸፍን የአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ አዘጋጆች ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አንድ ብሪታኒያዊ ፓይለት ከሱዳን ወደ ጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እንዳለ ደብዛው መጥፋቱን አስታውቆ እንደነበር ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ ናቸው ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት መቀዝቀዝ ማሳየቱን ተከትሎ በርካታ የሃገሪቱ ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘግበ። በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ችግር ዙሪያ ጥናትን የሚያካሄደው ዎክ ፍሪ የተሰኘ ተቋም በበኩሉ ከ400ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን የባርነት አይነት ህይወት ውስጥ እንደሚገኙ በ2016 ረፖርቱ አስፍሯል። በኢትዮጵያ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሴቶች በረሃብ፣ በህመም፣ በድህነትና ተያያዥ በሆኑ ...
Read More »በሱዳን ካርቱም ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) በሱዳን የተከሰተን የሸቀጣሸቀጦች ዋጋ ንረት ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች ሃሙስ በመዲናይቱ ካርቱም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች የተቃውሞ ሰልፍን ለመበተን በወሰዱት ዕርምጃ፣ ግጭት ተቀስቅሶ ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ተማሪዎች የሱዳን መንግስት የሸቀጣቀጦች ዋጋ ንረት እንዲረግብ እርምጃን መውሰድ እንዳለበት መጠየቃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። መንግስት በተለይ ...
Read More »በአማራ ክልል የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ጸረሰላም ሃይሎች የፈጠሩት ነው ሲል የአማራ ክልል ምክር ቤት ገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2008) የአማራ ክልል ምክር ቤት በክልሉ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የመልካም አስተዳደር ችግርና ጸረ-ሰላም ሃይሎች የፈጠሩት ችግር ነው በሚል ከተወያየ በኋላ የካቢኔ ሹም ሽር በማድረግ ተጠናቀቀ። በአቶ አንዳርጋቸው ገዱ ቀርበው በምክር ቤቱ ከጸደቁት 22 የቢሮ ሃላፊዎች 10ሩ ነባር ሃላፊዎች ሲሆኑ፣ 12 ደግሞ አዳዲሶች ናቸው። ከ12ቱ አዳዲስ የቢሮ ሃላፊዎች 6ቱ በአማራ ክልል ዩኒቨስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ ሲሆኑ፣ የብዓዴን አባላት ...
Read More »በተለያዩ የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ውጊያዎች በመካሄድ ላይ ናቸው
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ዛሬ በአብድራፊ አንገረብ ወንዝ አካባቢ ራሳቸውን ባደራጁ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል። ዛሬ ሲካሄድ በዋለው ውጊያ በነጻነት ሃይሎችም ሆነ በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። በሌላ በኩል በወልቃይት ትርካንና ማይነብሪ አካባቢ በአርበኞች ግንቦት7 ወታደሮችና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል መለስተኛ ውጊያ ...
Read More »በጂማ ዩኒቨርስቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ተማሪዎች ሌሊቱን ሲደበደቡ አደሩ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቲቶ ፉርጊሳ የምህንድስና ትምህርት ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች የጀመሩትን ተከታታይ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ወታደሮች ተማሪዎችን ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በማውጣት እስከ ሌሊቱ 11 ሰአት ድረስ እየደበደቡ ከፍተኛ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል። የኮማንድ ፖስትን በመወከል ተማሪውን ዛሬ የሰበሰቡ አካላት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እንደ ተማሪዎቹ ገለጻ የኮማንድ ፖስት ወኪሎች ‹‹ አርፈን ...
Read More »በሃረር በርካታ ዜጎች ሲታሰሩ በባህርዳር ደግሞ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጪው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓም ከሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል ጋር በተገናኘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፣ በሃረር ከተማ ከፍተኛ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፍተሻ ወቅት የክልሉን መታወቂያ ያልያዙ ሰዎች እየተያዙ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ከሌሎች ክልሎች ሄደው በክልሉ ውስጥ በመስራት ላይ ያሉ በርካታ ዜጎች፣ የክልሉን መስተዳድር መታወቂያ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ከመጣችሁበት ክልል ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት ቃጠሎ እና በጥይት ለተገደሉ ታራሚዎች ሞት 38 እስረኞች ተጠያቂ ሆኑ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ነሃሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ሆን ተብሎ የእሳት ቃጠሎ እንዲነሳ በማድረግ ከእሳቱ ለመሸሽ ሲያመልጡ የነበሩ ታራሚዎች በእሳት ቃጠሎ እና በግፍ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው የሚታዉቅ ሲሆን ለዜጎች ሞት ምክንያት ናቸው የተባሉ 38 እስረኞች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛክስ ተመስርቶባቸዋል። እስረኞቹ ሆን ብለው እሳት እንዲነሳ ያደረጉት በድብቅ ...
Read More »አልሸባብን ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺ ወታደሮች ያስፈልጋሉ ተባለ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ አሚሶም ስር የተሰማራው ጦር፣ በአሁኑ ወቅት አልሸባብ ከተቆጣጠራቸው የሶማሊያ ግዛቶች ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺህ ወታደሮች ማሰማራት እንደሚያስፈልጉት አስታውቋል። ጁባ ሸለቆ፣ ሂራን፣ በቆል እና አንዳንድ የተወሰኑ የድንበር ከተሞች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የኅብረቱ ጦር ቃል አቃባይ የሆኑት ኮሎኔል ጆሴፍ ጊበርት እንዳሉት አሁን ካሉ 21 ሽህ ...
Read More »