ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009) በጋና ለ10 አመት ያህል አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሃሰተኛ የአሜሪካ ኤምባሲ መዘጋቱን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። በጋና መዲና አክራ ከአመታት በኋላ የተገኘው ይኸው ሃሰተኛ ኤምባሲ ለበርካታ ሰዎች በህገወጥ መንገድ የተገኙ ህጋዊ ቢዛዎችን እና የተለያዩ ሰነዶችን ሲሸጥ መቆየቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ሃሰተኛ ኤምባሲ የአሜሪካ ሰንደቅ አላማን እንዲሁም የፕሬዜደንት ባራክ ኦባማ ምስልን በህንጻው ላይ ...
Read More »Author Archives: Central
የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነትና የኮሚሽነሮች ምርጫ እጩን አቅርባ የነበረችውን ኢትዮጵያ እራሷን ከምርጫው አገለለች
ኢሳት (ኅዳር 23 ፥ 2009) በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነትና የኮሚሽነሮች ምርጫ ለኮሚሽነርነት እጩን አቅርባ የነበረችውን ኢትዮጵያ እራሷን አገለለች። በሃምሌ ወር በሩዋንዳ ተካሄዶ በነበረው የህብረቱ የመጀመሪያ ዙር የምርጫ ሂደት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ካለው ስምንቱ የኮሚሽኑ ቦታዎች ለአንደኛው ተወዳዳሪን አቅርባ እንደነበር ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኮሚሽነርነት የተወዳደረበትን ቦታ ባይጠቅስም፣ በወቅቱ ለህብረቱ የጸጥታና የደህንነት ኮሚሽነርነት በርካታ ሃገራት ተወዳዳሪዎችን ...
Read More »በጋምቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ያህያ ጃሚህ በተቃዋሚ እጩ ተወዳዳሪ ተሸነፉ
ኢሳት (ኅዳር 23 ፥ 2009) በጋምቢያ በተካሄደ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለ22 አመታት በስልጣን የቆዩት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ያህያ ጃሚህ በተቃዋሚ እጩ ተወዳዳሪ ተሸነፉ። ከ22 አመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ለስልጣን በቅተው የነበሩት የጋምቢያው ፕሬዚደንት ከተፎካካሪያቸው ሰፊ ልዩነት ያለው ድምፅ በማግኘት መሸነፋቸውን የምዕራባዊቷ ሃገር የምርጫ ኮሚሽን ሃላፊ አሊ’ኡ ሞማር ንጃ’ይ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል። በፕሬዚደንታዊ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩት የተቃዋዋሚ ፓርቲ አመራሩ አዳማ ባሮ ...
Read More »በኢትዮጵያ መንግስት የታቀደው “የ11 በመቶ” አድገት አለመሳካቱ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 23 ፥ 2009) በ2008 የኢትዮጵያ በጀት አመት የታቀደው የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አለመሳካቱንና እድገቱ በስምንት በመቶ አካባቢ መመዝገቡን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ይፋ አደረገ። በቅርቡም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ባለው የኢኮኖሚ መዋዠቅ ምክንያት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በስድስት በመቶ ብቻ ሊያድግ እንደሚችል መገለጹ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስና በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ በኢኮኖሚ ዕድገቱ መዋዠቅ ምክንያት መሆኑ ታውቋል። የ2008 በጀት ...
Read More »በደቡብ ምስራቃዊ ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት በመሞታቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አደጋ ውስጥ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ኅዳር 23 ፥ 2009) በደቡብ ምስራቃዊ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከሰተውን አዲስ የድርቅ አደጋ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸውንና ድርጊቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ስጋት ውስጥ እንደከተተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በርካታ አርብቶና አርሶ አደሮች እንስሶቻቸውን በድርቁ እንዳይሞቱ በመስጋት ለሽያጭ እያቀረቡ መሆኑንም የአለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ንብረት የሚቆጥሩትን የእንስሳት ...
Read More »በአማራ ክልል የብአዴን አባላት ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ግምገማ ጀመሩ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩ የብአዴን አባላት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ግምገማ ተጀምሯል። በክልሉ የውሃ ሃብት ውስጥ የሚሰሩ የብአዴን አባላት በአማራ ክልል መሰብሰቢያ አዳራሽ ዓርብ ሕዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተጀመረው ስብሰባ ከተወያዮቹ ከፍተኛ ተቃውሞዎች ቀርበውበታል። ስብሰባውን በዋና አወያይነት የመሩት በአማራ ክልል የምእራብ አማራ የውሃ ...
Read More »የዶ/ር መረራ ጉዲና እስራት እንዳሳሰበው የአሜሪካ መንግስት መግለጫ አወጣ
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር እና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና እስራት እንዳሳሰበው የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቃል አቀባዩ በኩል የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ማርክ ቶነር እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር መረራ ጉዲና ማሰሩን የአሜሪካ መንግስት መንግስት እያሳሰበው መምጣቱን እና ...
Read More »የአማራ ክልል የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ የታሰሩት በፌደራል ደህንነትና አቃቢ ህግ ነው አለ
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው አርብ ጀምሮ በቁጥጥር ስር የሚገኙት የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ልጃለም መሰረት ፣ ደብዳቤ እንዲያስገቡ ተነግሯቸው ለክልሉ መንግስት “ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ ወይም እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ቢያስገቡም፣ የአማራ ክልል መንግስት “ አንተን ያሰረህ የፌደራል ደህንነትና የፌደራል አቃቢ ህግ በመሆኑ ክልሉ አያገባውም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ኢንስፔክተር ልጃለም ለፌደራል ጠ/አቃቢ ህግ ...
Read More »ነጋዴዎች በካሽ ሬጀስትራር ማሽን ለብዝበዛ እየታጋለጡ መሆኑን ገለጹ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በአገሪቱ የኢንትርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉን ተከትሎ የሂሳብ ማሽን (ካሽ ሬጀስትራር) የሚጠቀሙ የመርካቶ ነጋዴዎች ፣ ማሽናቸው ከጥቅም ውጭ በመሆኑ እሱን ለማስተካከል ማሽኖችን ወደ ገዡባቸው ድርጅቶች ሲሄዱ በነፍስ ወከፍ 280 ብር እንደሚጠየቁ ነጋዴዎች ተናግረዋል። “ ችግሩ የእኛ አይደለም፣ ችግሩ የመንግስትና የቴሌ ነው። እኛ ማሸን ግዙ ተብለን ገዛን፣ ቴሌ ደግሞ ኔትወርክ አቋረጠብን፣ ...
Read More »ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ ውስጥ የሆነ የሰላማዊ ሰልፈኛ ቤተሰብ ታሰሩ ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የሕግ ጠበቃና ዳኛ የነበሩት ሽኩሪ ሻፊ በአውስትራሊያ ከሚገኙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የሶማሌ ብሔር ተወላጆች ጋር በመኾን ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ኡመር የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር። አቶ ሽኩሪ ሻፊ በሜልቦርን ከተማ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፉ ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ሦስት ወንድሞቻቸውን ...
Read More »