ኢሳት (ኅዳር 27 ፥ 2009) የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለእስር የተዳረጉበት ምክንያት ግልፅ እንዲደረግ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄን አቀረበ። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴው ሃላፊ የሆኑት ኤሊና ቫሌንሲያኖ በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራሩ ላይ የሚመሰረት ክስ ካለ መንግስት ጉዳዩን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ባለፈው ሳምንት ከአውሮፓ አባላት ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክርን ያካሄዱት ዶ/ር መረራ ጉዲናን ከጉብኝታቸው መልስ ...
Read More »Author Archives: Central
በእስራዔል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ላይ የተፈጸመ የግርዛት ልምምድ ድርጊት ቁጣን ቀሰቀሰ
ኢሳት (ኅዳር 27 ፥ 2009) ሰሞኑን በእስራዔል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ላይ የተፈጸመ የግርዛት ልምምድ ድርጊት በሃገሪቱ የፓርላማ አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ። አንድ ታዋቂ እስራዔላዊ የህክምና ባለሙያ ተማሪዎቹ ያለምንም ዕውቀት የግርዛት የትምህርት ልምምዳቸውን አነስተኛ ገቢ ካላቸው የኢትዮጵያና የሱዳን ማህበረሰብ ህጻናት ላይ እንዲያካሄዱ ሲያደርግ የቆየው ድርጊት በእስራዔል ፐብሊክ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋለጡን መዘገባችን ይታወሳል። ይህንኑ ድርጊት ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ የሚመክር ...
Read More »በሰሜን ጎንደር በሚደረገው ጦርነት የነጻነት ሃይሎች ድል እንደቀናቸው ተናገሩ
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ከህወሃት/ኢህአዴግ ጦር ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ድል እየቀናቸው መሆኑን ለኢሳት ተናግረዋል። በውጊያው በመሳተፍ ላይ ካሉት መካከል አንዱ በሰሞኑ ወጊያ መትረጊስ ሳይቀር መማረኩን እና በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ገልጿል። ወኪላችን የሰሞኑን የውጊያ ውሎ በማስመለከት በላከው ሪፖርት አገዛዙ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ነው። በዳባት ወረዳ በአጅሬ ጃኖራ ከህዳር ...
Read More »የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2009 ዓም በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ለማክበር በተጠራ ዝግጅት ላይ “ተማሪዎች በአሉ እኛን አይወክልም” በማለት ከመሰብሰቢያ አዳራሹ በመውጣት በጩኸት ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲ ግቢ በመግባት 37 ተማሪዎችን ይዘው አስረዋል። የአማራ ክልል ተወላጆች “ ወልቃይት ማንነቱ አማራ ነው” የሚሉና ሌሎችንም አገዛዙን የሚያወግዙ ...
Read More »“ለቁንጽል መፍትሄ ብለን ከዚህ መንግስት ጋር የሚያደራድረን የለም” ሲሉ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ተናገሩ
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ዲማ ነገዎ ይህን የተናገሩት፣ በጀርመን የሙኒክ ከተማ ንቅናቄውን ለህዝብ ለማስተዋወቅና ድጋፍ ለመሳበሰብ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ነው። “ኢህአዴግ አርበኞች ግንቦት7 ትን ካወገዛችሁ ከእናንተ ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ቢላችሁ፣ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ትሆናላችሁ? “ ወይ ተብሎ ለቀረቡላቸው ጥያቄ ፣ ዶ/ር ዲማ ...
Read More »የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች ሃረርን አጨናንቀዋል
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው ህዳር 29 የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት በማድረግ በከተማው የሚታየው የጸጥታ ቁጥጥር የከፋ መሆኑን ገልጿል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ወደከተማ የገቡ ሲሆን፣ ለጸጥታ ስጋት ናቸው የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። ከሃረር ወጣ ብሎ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ከ500 በላይ የሚሆኑ የአማራ እና የሌሎችም አካባቢ ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው 37 ተከሳሾች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸመባቸው ገለጹ
ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009) በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው 37 ተከሳሾች በእርቃናቸው የመገረፍና የተለያዩ የሰብዓዊ ስቃዮች እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ለፍርድ ቤት አቤቱታን አቀረቡ። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ የቀረበውን አዲስ ክስ ለመስማት በተሰየመ ጊዜ ተከሳሾቹ የቀረበባቸው “የእሳት ቃጠሎ አስነስታችኋል” ክስ የውሸት ክስ ነው ሲሉ ለዳኞች መግለጻቸው ታውቋል። አቤቱታቸውን ለችሎቱ ያቀረቡት እነዚሁ ...
Read More »በኢትዮጵያ ኢንተርኔት እንዲዘጋ በመደረጉ የዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራቶች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲዘጋ በመደረጉ በመንግስት ላይ የዘጠን ሚሊዮን ዶላር ወይም የ200 ሚሊዮን ብር አካባቢ ኪሳራ ማስመዝገቡን አንድ አለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ። መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ያደረገው ዘ-ብሩኪንግስ ኢንስቲቲዩቱ በሃገሪቱ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሃምሌ 1 ፥ 2015 አም እስከ ሰኔ 30 2016 አም የኢንተርኔት አገልግሎት በተለያዩ ምክንያቶች ዝግ ተደርጎ መቆየቱን አውስቷል። አገልግሎቱ ተዘግቶ በቆየበት ...
Read More »በድርቅ ጉዳት ደርሶባቸው አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ አካባቢዎች መለየታቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ አምስት አካባቢዎች አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ ሆነው መለየታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ይፋ አደረገ። በርካታ እንስሳት በድርቁ ምክንያት በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው ድርጅቱ የደቡብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ ኦሞ የሰገን እና ጋሞጎፋ አጎራባች ስፍራዎች እንዲሁም የሶማሊ ክልል አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ቅድሚያ ተኮር ተደርገው አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ ተብለው መፈረጃቸውን አመልክቷል። በሃገሪቱ ተከስቶ ...
Read More »ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ድርጅት ጽ/ቤቶች እንዲዘጉ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገለጸች
ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009) ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃገሪቱ የተቃዋሚ ድርጅቶች ጽ/ቤት እንዲዘጉ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ገለጹ። ሰሞኑን ሚስጢራዊ የጦር መሳርያ ግዥን ለመፈጸም የተስማሙት ሁለቱ ሃገራት በሪክ ማቻር የሚመራው የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሲያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ እንዲያበቃ ድርድር ሲያካሄዱ መቆየታቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። በሁለቱ ሃገራት መካከል የተደረሰን ስምምነት ተከትሎ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ...
Read More »