ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶባቸው ከተተከሉት ራዳሮች መካከል በአፋር ክልል ዱብቲ አካባቢ የተተከለው ራዳር ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ እንዲነቀል ተደርጓል። እርምጃው ለምን እንደተወሰደ ባይታወቅም፣ ዘገባው በኢሳት ከተላለፈ በሁዋላ እንዲነሳ መደረጉ ምናልባትም ከመረጃው ከመውጣት ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የርቀት መቆጣጠሪያ ...
Read More »Author Archives: Central
የፉጋ ማህበረሰብ እየተባሉ የሚጠሩት ለመጥፋት ተቃርበዋል ተባለ
ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል በአላባ ልዩ ዞን የሚገኝው የፉጋ ማህበረሰብ ከፍተኛ ለሆነ መገለል እና መድሎ ተጋላጭ በመሆኑ እና ምንም አይነት ፤ የትምህርት ፣ የጤና ተደራሽነት በማጣቱ ወደ ማህበረሰባዊ በቀል እና ጥላቻ የወለደው አመፅ ሊያመሩ እንደሚችሉ የፌደሬሽን ምክርቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ባስጠናው ጥናት ኢህአዴግ እስካሁን ድረስ አገዛዙን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ ማህበረሰቡ “የተካደ የተናቀ እና ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ ስኮት በርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ዜጎች ጋር በጋራ በመቆም ራሳቸውን ለመከላከል እየሞከሩ ነው።
ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደርባን በ76 ኪ/ሜትር ላይ በምትገኘዋ ስኮት በርግ ከተማ በምትገኝ መንደር ውስጥ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 4 ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፣ 8ቱ ደግሞ ቆስለዋል። 11 ሱቆቻቸውም ተዘርፈውባቸዋል። 1 የደቡብ አፍሪካ ፖሊስም ተገድሏል። አምስት ዘራፊዎችና ነፍሰ ገዳዮች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ ፣ የዋስ መብታቸውን ለማስጠበቅ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ድርጊቱን ለማውገዝና ፍትህ እንዲሰጣቸው ...
Read More »ቤተ እስራኤላዊያን የሚደርስባቸውን ዘረኝነት በመቃወም ብሄራዊ ወታደራዊ አገልግሎትን ተቃወሙ
ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ ቤተእስራኤላዊያን በተቋም ደረጃ በእስራኤል ውስጥ የሚደርስባቸውን ዘረኝነትና መገለል በመቃወም ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም ሲሉ ተቃውሞ አደርገዋል። ቤተእስራኤላውያኑ በእስራኤል መንግስት መስሪያቤቶች በወታደራዊ እና ፖሊስ ተቋማት ውስጥ መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል። እነዚህ 300 ኢትዮእስራኤላዊ አይሁዶች በወታደራዊ አገልግሎት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩ ናቸው።
Read More »የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለ12 አመቱ ታዳጊ ኢትዮጵያዊ አውስትራሊያዊ ደብዳቤ መልስ ሰጠ።
ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ12 አመቱ ታዳጊ ኢዮስያስ መላኩ በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያ፣ አፈናና እስራት የአውስትራሊያ መንግስት እንዲያወግዝ እንዲሁም በአገዛዙ ላይ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቅ በድምጽ የተቀረጸ መልእክት ለአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ማልኮም ተርንበል ካስተላለፈ በሁዋላ፣ የጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ደብዳቤውን ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁሊየ ቢሾፕ ማስተላለፉን የሚመለከት ምላሽ ተልኮለታል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ...
Read More »የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደተዘጋ ነው
ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ቀናት በፊት የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ላለመሄድ በመወሰናቸው ዛሬ አርብ፣ ትምህርት ቤቱ ተዘግቶ ውሎአል። ባለፈው ረቡዕ በተደረገው ተቃውሞ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች ከፍተኛ ደብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ዛሬ ትምህርት ይጀምራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀርቷል። ከአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ...
Read More »አርበኛ መቶ አለቃ ደጀኔ በተኩስ ልውውጥ መሃል መሰዋቱ ታወቀ
ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታህሳስ 12 ቀን 2009 ዓም በነጻነት ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል ቋራ ላይ ተደርጎ በነበረው ከባድ ውጊያ ከመንግስት በኩል ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ወታደሮች ሲገደሉ፣ ከነጻነት ሃይሎች መካካል ደግሞ መቶ አለቃ ደጀኔ መንግስቱ መስዋት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አርበኞቹ እንደሚሉት መቶ አለቃ ደጀኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣውን ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ አስመልሳለሁ በሚል ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ
ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥር ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ የሃመር ወጣቶች ‹‹ከዱር አራዊት በታች መታየት የለብንም›› በማለት የጀመሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በአስቸኳይ አዋጅ ስም ጥያቄውን ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ህዝቡን ለበለጠ አለመረጋጋት መዳረጉን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። “ተቃውሞው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰራተኞች ፣ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የመነሻ ሃሳብ እንዲቀርብላቸው ጠየቁ
ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ ስርዓቱን አደጋ ውስጥ መጣሉን የተረዳው ኢህአዴግ፣ መነጠኛ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እንዲቀርብለት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል ትእዛዝ አስተላልፏል። ጥናቱ በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ እንዲቀርብ ያዛል። ክልሎቹን ህገመንግስቱን ለማሻሻል የሚያስችል አቅም ያላቸው አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አመራሮች ምርጫ አካሂደው እንዲያሳውቁ ታዘዋል። የሚሻሻሉት ህጎች የትኞቹ እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ...
Read More »አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ
ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) ኢትዮጵያዊው የኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ። አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በ72 አመት ዕድሜው ከዚህ አለም በሞት የተለየው በስደት በሚኖርበት ካናዳ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ነው። የኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በ1972 በሞስኮ በተደረገው ውድድር በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትሮች ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ ያስገኘ ድንቅ አትሌት ነበር። ማርሽ ቀያሪው በሚል የሚታወቀው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ...
Read More »