ኢሳት (ታህሳስ 20 ፥ 2009) ከጋምቤላ ከተማ ወደ መታር ከተማ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞበት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። በህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ረቡዕ ጠዋት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ከጋምቤላ ክልል 60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መሆኑ ታውቋል። አውቶቡሱ ከ40 በላይ መንገደኞች አሳፍሮ ነበር ። ማንነታቸው አልታወቀም የተባሉት ታጣቂዎች የተሽከርካሪውን የነዳጅ መያዣ በጥይት በመቱት ጊዜ ...
Read More »Author Archives: Central
በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በጋምቤላ ክልል ስለተፈጸመ የመሬት አሰጣት ችግር ይፋ የተደረገው ጥናት ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ባለሃብቶች ገለጹ
ኢሳት (ታህሳስ 20 ፥ 2009) በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በጋምቤላ ክልል ስለተፈጸመ የመሬት አሰጣት ችግር ይፋ የተደረገው ጥናት ከእውነት የራቀና ሁሉንም ባለሃብቶች ያላሳተፈ ነው ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ቅሬታ ማቀረባቸውን “ሪፖርተር” ዘገበ። በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ እነዚሁ ባለሃብቶች ሰሞኑን የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ባለሃብቱን ያላሳተፈ፣ ከእውነት የራቀ እና የስራ አፈጻጸሙን በጅምላ የተቸ ነው ማለታቸውን በዘገባው ተመልክቷል። በጋምቤላ ክልል በሃጋዊ መንገድ ...
Read More »ዶ/ር መረራ ጉዲና በሽብር ወንጀል ስለመሳተፋቸው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ፖሊስ ገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 20 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በፖሊስ የተጠየቀን የተጨማሪ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሃሙስ ፈቀደ። ምርመራውን እያካሄደ የሚገኘው ፖሊስ ዶ/ር መረራ በሽብር ወንጀል ድርጊት ስለመሳታፋቸው የተለያዩ ምርመራዎችን እያካሄደ መሆኑን ለችሎቱ ማስረዳቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። ቀደም ሲል ፖሊስ ዶር መረራን ያሰራቸው አስቸኳይ አዋጁን ተላልፈዋል በሚል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ምርመራው የሽብር ...
Read More »በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ ወጣቶች በግዳጅ ተመልምለው ወታደራዊ ስልጣና እየወሰዱ ነው
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የትውልድ ቦታ በሆነው በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ በሚገኙ 17 ቀበሌዎች የሚገኙ ወጣቶች፣ በጎንደር በኩል ወራሪ ጠላት መጥቷል በሚል እየተያዙ በግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወጣቶቹ ከሌሊቱ 8 እና 9 ሰአት ላይ እየታፈሱ በግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ በተደረገው 5 ዙር ስልጠና ከ300 ...
Read More »ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ወንጀል ሊከሰሱ ነው።
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር በብራሰልስ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለስብሰባ መጥተው ሲመለሱ ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ፕሮፌሰር መረራ ከሁለት ሳምንታት በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ የተመለሱ ሲሆን፤ መርማሪዎች የኢሜይልና የፌስቡክ አካውንታቸውን አስገድደው በመውሰድ በሽብርተኝነት ሊያስከሣቸው ይችላሉ ብለው የሚያሥቧቸውን መረጃዎች እያሰባሰቡ ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ዞን ያንዣበበው የረሃብ አደጋ አሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ቆላማ የአርብቶ አደር አካባቢዎች በተለይም በሃመር፣ ኛንጋቶምና ዳሰነች እንዲሁም ሳላማጎ ወረዳዎች የረሃብ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ የቆዩ ቢሆንም፣ ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ ረሃብ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የግብርና ባለሙያዎች ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ረሃቡ ቅድመ ግምት በተሰጣቸው ቆላማ ወረዳዎች ሳይወሰን ወደ ወይና ደጋና ደጋ አርሶአደር ...
Read More »በአዲስ አበባ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሊፈርሱ ነው
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ በሚከለሰው ማስተር ፕላን ስም በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ አዲስ ዘመቻ ሊጀመር መሆኑን መስተዳድሩ አስታውቋል።በዚህ ዘመቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለምንም ተተኪ ቤቶች ይፈናቀላሉ። እንዲፈርሱ ትእዛዝ የተላለፈባቸው አካባቢዎች ፈረንሳይ፣ ካራ፣ የካ፣ አባዶ፣ ወሰን፣ ምኒሊክ፣ ኮተቤ፣ ሲኤምሲ፣ ቦሌ እና የካን የሚያዋስነው መስመር፣ መገናኛ፣ አዲስ አበባን ከኦሮሚያ ...
Read More »ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ የደህንነት ሰራተኞች ደሞዝ በብር ተከፈለ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የውጭ ደህንነት ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ ደሞዛቸው በብር እንዲከፈላቸው ተደርጓል። እስካሁን ድረስ ደሞዝ ይከፈለው የነበረው በአሜሪካን ዶላር ቢሆንም፣ በዚህ ወር ግን ዶላር የለም በሚል ምክንያት በብር እንዲከፈለን ተደርጓል ሲሉ ለኢሳት ተናግረዋል። በጎረቤት አገራት በደህንነት መረጃ ማሰባሰብ ስራ ላይ ከተሰማሩት የደህንነት ሰራተኞች መካከል ብዙዎቹ ከብሄራቸው ጋር በተያያዘ ከሚፈጸምባቸው ...
Read More »የደቡብ ኦሞ ዞን ም/ል አስተዳዳሪ አምጸው ጫካ መግባታቸው ተሰማ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደኢህዲን/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬና የዞኑ ም/አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሥጦታው ጋርሾ ከገዢው ፓርቲና መንግስት ጋር የፈጠሩትን ቅራኔ ተከትሎ በትውልድ አካባቢያቸው በና-ጸማይ ወረዳ ውስጥ ወጣቶችን አስከትለው መሸፈታቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሥጦታው ጋርሾ ከዞኑ የደህንነት ቢሮና አስተዳደር ጋር በተፈጠረ ቅራኔ ‹ተገምግመው › በተለያዩ የሙስ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ወህኒ ወርደው ከተፈቱ በኋላ ወደ ትውልድ ...
Read More »የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባል ታሰሩ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳንሻ ይኖሩ የነበሩት የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ግዛው በሬ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲፈጸምባቸው ከቆዩ በሁዋላ ትናንት ማክሰኞ ሶረቃ ከተማ በስራ ላይ እያሉ በትግራይ ክልል የደህንነት አባላት ታፍነው ተወስደዋል። አቶ ግዛው በዳንሻ መኖር ስላልቻሉ ወደ ሰሮቃ ሄደው በግል ስራ ላይ ይተዳደሩ ነበር። ግለሰቡ እስካሁን ድረስ የት ቦታ እንደታሰሩ የታወቀ ...
Read More »