ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) ግብጽ በተያዘው ወር በአዲስ አበባ ከተማ ከሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በፊት ሱዳንን ያሳተፈ የአባይ ግድብ ድርድር እንዲካሄድ ጠየቀች። በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባትን ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል በአባይ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረ ድርድር መቋረጡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለአንድ አመት ያህል በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጀርባ ግብፅ እጇ አለባት ሲሉ ቅሬታን ማቅረባቸው ...
Read More »Author Archives: Central
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶችን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት አመታዊ የመሪዎች ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ወሰነ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ መንግስትና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች መካከል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶችን ተከትሎ ህብረቱ አመታዊ የመሪዎች ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ወሰነ። የህብረቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ በሃገሪቱ ተግባራዊ ሆኖ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመሪዎች ጉባዔ ላይ የደህንነት ስጋት ይኖረዋል ሲሉ ባለፈው ወር ስጋታቸውን ገልጸው እንደነበር አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል። ይሁንና በሁለቱ ወገኖች መካከል ...
Read More »የአለም ጤና ድርጅት የበላይ ጠባቂ ቦርድ ቀጣይ የተቋሙ ሃላፊ ሆነው ለመመረጥ ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱን ለይቶ እንደሚያሳውቅ ገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) የአለም ጤና ድርጅት የበላይ ጠባቂ ቦርድ በተያዘው ወር ቀጣዩ የተቋሙ ሃላፊ ሆነው ለመመረጥ ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱን ለይቶ እንደሚያሳውቅ ገለጸ። የቀድሞ የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ የብሪታኒያ፣ የፓኪስታን፣ እና የሃንጋሪ ተወዳዳሪዎች በቦርዱ ምርጫ የሚካሄድባቸው መሆኑ ታውቋል። ተወዳዳሪዎቹ በቅርቡ ስለድርጅቱ ያላቸው ራዕይ አስመልክቶ ያቀረቡትን ገለጻና የተደረገላቸውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ አምስቱ ተወዳዳሪዎች ...
Read More »የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት ወ/ሮ ፋናዬ ልጃቸውን እንዳይጎበኙ እገዳ እንደተጣለባቸው አስታወቁ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) በእስር ላይ የሚገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት ልጃቸውን እንዳይጎበኙ እገዳ እንደተጣለባቸው አስታወቁ። ይህንኑ እገዳ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እኛ ለሌሎች አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ደብዳቤን የጻፉት ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳቸው ከጉብኘት እገዳው በተጨማሪ የልጃቸውን ጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን በደብዳቤያቸው አስነብበዋል። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጤንነት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣትን ተከትሎ ጋዜጠኛው በቅርቡ ከሚገኝበት የዝዋይ ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው እስረኞች ቁጥር 121 መድረሱ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) ከወራት በፊት በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው እስረኞች ቁጥር 121 መድረሱ ተገለጸ። የፌዴራሉ ከሳሽ አቃቤ ህግ ከአንድ ወር በፊት በእስር ቤቱ ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተያያዘ 38 እስረኞች ክስ እንደመሰረተባቸው ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ ቁጥሩ ወደ 121 ከፍ ማለቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በይፋ ክስ ...
Read More »ሁለት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 19 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተፈረደባቸው
ታኅሣሥ ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የሬዲዮ ቢላል ጋዜጠኞችን ዳርሰማ ሶሪ እና ካሊድ መሁሃመድን ጨምሮ በተለያዩ 19 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የእስር ውሳኔ አሳልፏል። ዳርሰማ ከህመሙ ጋር በተያያዘ 4 አመታት ከአምስት ወራት ሲፈረድበት፣ ካሊድ ደግሞ 5 አመታት ከስድስት ወራት ተፈርዶበታል። በከድር ሙሃመድ የሱፍ መዝገብ በተከሰሱት ቀሪዎቹ ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ በጅምላ የ 5 ...
Read More »በሁለት ጋዜጠኞችና በ18 ተከሳሾች ላይ ከ6 ወር እስከ 5 አመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ማክሰኞ ተላለፈ
ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) በቅርቡ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ሁለት ጋዜጠኞችና 18 ተከሳሾች ከስድስት ወር እስከ አምስት አመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ማክሰኞ ተላለፈባቸው። ተከሳሾቹ ድምጻችን ይሰማ ሲሉ በችሎቱ መፈክር ማሰማታቸውም ተመልክቷል። የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 18ቱ ተከሳሾች የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ከእስር ቤት ለማስወጣት የሽብር ጥቃት ለማድረስ በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ባለፈው ሳምንት የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ማክስኞ ...
Read More »በብራዚል በእስር ቤት በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) በብራዚል በሚገኝ አንድ እስር ቤት በተቀሰቀሰ የእስረኞች የእርስ በዕርስ ግጭት በትንሹ 56 ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። አማዞናስ ተብሎ በሚጠራው የብራዚል ሰሜናዊ ግዛት ስር በሚገኝ አንድ እስር ቤት በተነሳው በዚሁ ግጭት ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ እስረኞች ማምለጣቸውንም ቢቢሲ የእስር ቤቱን ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ለበርካታ ሰዓታት የቆየው ይኸው የእስረኞች ግጭት በሁለት ቡድን በተከፈሉ እስረኞች የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ ...
Read More »ቡሩንዲ በሰላም አስከባሪ ስም በሶማሊያ ያሰማራችውን ጦር ልታስወጣ ነው ተባለ
ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰማርቶ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ልዑክ ስር ሰራዊቷን አሰማርታ የምትገኘው ብሩንዲ የአፍሪካ ህብረት ወታደሮቿ ክፍያ ባለመፈጸሙ በቀጣዩ ወር ከሶማሊያ ጠቅልላ እንደምትወጣ አስታወቀች። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ወደ 5ሺ 432 አካባቢ የሚጠጉ የብሩንዲ የሰላም አስከባሪ አባላት ለአንድ አመት ያህል ምንም ክፍያ ሳይፈጸምላቸው መቆየቱ ተስፋ መቁረጥ እንዳሳደረባቸው ይፋ ማድረጋቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል። በሶማሊያ ተሰማርቶ ለሚገኘው የህብረቱ የሰላም አስከባሪ ...
Read More »አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ከ5 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች አደጋ ላይ መሆናቸው ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አዲስ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ መጋለጣቸውን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አረጋገጠ። ለምግብ ድጋፍ ለተጋለጡ የሃገሪቱ ዜጎች በተያዘው አመት ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በአደጋው በርካታ የቤት እንስሳት በመሞት ላይ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከወራት በፊት ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቱ ...
Read More »