Author Archives: Central

ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ  “ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ” የተባለውን ድርጅት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (ታህሳስ 28 ፥ 2009) “ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ” በሚል በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ህዝባዊ ስብሰባ፣ ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድርጅቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ። በኢትዮጵያ ለለውጥ የሚታገሉ ሃይሎችም ተባብረው እንዲሰሩም በዚሁ መድረክ ተጠይቀዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት “ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ” በኢትዮጵያ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን በዚሁ ህዝባዊ መድረክ አብራርተዋል። ዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ ...

Read More »

በኦሮሚያ በተባረሩት አመራሮች ቦታ የሚሾም እየጠፋ ነው። የክልሉ ፕ/ት ከህወሃት ጋር የሚያጋጫቸውን ንግግር ተናግረዋል።

  ታኅሣሥ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦህዴድ በቅርቡ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ ከሚገኙ ባለስልጣኖች ጋር ግምገማ አካሂዷል። ግምገማው የህወሃትን የበላይነት ይቃወማሉ የተባሉ የተለያዩ አመራሮችን ለማባረር የታቀደ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም በርካታ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተው ደሞዝ ብቻ እየተከፈላቸው ተንሳፈው ይገኛሉ። ለእስር እንዳረጋለን ብለው የፈሩት ደግሞ እየኮበለሉ ወደ ተለያዩ አገራት እየተሰደዱ ነው። ኦህዴድ በስልጣን ባነሳቸው አመራሮች ቦታ አዳዲስ አባላቱን ...

Read More »

በጂንካ የፖለቲካ እስረኞችን ለመወንጀል የፈጠራ ማስረጃዎች  እየተሰበሰቡ ነው

ታኅሣሥ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን የሃመር ወጣቶች በጥር 2007 ዓ.ም የጀመሩትን ተቃውሞና ከመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ጋር የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በዞኑ የሚንቀሳቀሰውን የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት /ኦህዲኅ/  አመራሮች ለመወንጀል የዞኑ ጸጥታና ደህንነት ሹም/ ኃላፊ አቶ አልዓዛር ቶይሳ የተጀመረው የሃሰት ውንጀላና እስራት  እስከዛሬ እንደቀጠለ መሆኑን የድርጅቱ አባላትና የታሳሪዎች ቤተሰቦች አስታወቁ፡፡ አቶ አልኣዛር ባለፈው ዓመት ፣ሚያዚያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት ተባብሶ ቀጥሏል

ታኅሣሥ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ባወጣው ወርሃዊ የዋጋ ጥናት ሪፖርት መሰረት በታህሳስ ወር የታየው የዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7.3% ጭማሪ አሳይቷል። በታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም የምግብ ነክ የዋጋ ንረት 6.5% ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች በበኩላቸው 8.1% ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ይህም በአጠቃላይ የአስራ ሁለት ወራት ተንከባላይ የዋጋ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ምክንያት በማድረግ ወደ 70ሺ አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ወደ 70ሺ አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን አሶሼትድ ፕሬስ የፓርቲ አባላትን ዋቢ ባማድረግ ዘገበ። የክልሉ መንግስት በበኩሉ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው በቅጣት ላይ የነበሩ 10ሺ እስረኞች በይቅርታ እንዲፈቱ መደረጉን ሃሙስ ይፋ አድርጓል። ይሁንና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት አቶ ሙላቱ ገመቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ...

Read More »

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለምስክርነት እንዲቀቡለት የጠየቃቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና ፍ/ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰዋል ተብለው በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ሃሙስ ለምስክርነት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ፍ/ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ። የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዮናታን ተስፋዬ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ አቶ በቀለ ገርባ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች አካላት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡለት መጠየቁን ለመረዳት ተችሏል። ...

Read More »

ከውጭ አገር ከሚገቡ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተከሰተውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተከትሎ ከውጭ ሃገር በሚገቡ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ተጠቃሚዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በበኩሉ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ምክንያት በማድረግ የሃገሪቱ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረበት 8.1 በመቶ ወደ 8.2 በመቶ ማደጉን ሃሙስ አስታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከተለያዩ ሃገራት የሚገቡ መሰረታዊ ...

Read More »

ሲፒጄ በሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ላይ የተላለፈ የእስር ቅጣት አወገዘ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2009) አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲ ፒ ጄ) በሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ላይ የተላለፈውን የእስር ቅጣት አወገዘ። የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሽብርተኛ ወንጀል ተመስርቶባቸው የነበሩት ጋዜጠኞች ካሊድ መሃመድና ዳርሴማ ሶሪ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል በማለት እያንዳንዳቸው በአምስትና በአራት አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት እንዲቀጡ ፍርድ መስጠቱ ይታወሳል። ይሁንና መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ያደረገው ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ ...

Read More »

አበረታች መድሃኒት በሚወስዱ አትሌቶች ላይ የእድሜ ልክ እገዳ ለመጣል የተወሰደው ዕርምጃ አለም አቀፍ ተሞክሮን ያካተተ እንዲሆን አሰልጣኞች ጠየቁ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው በሚገኙ አትሌቶች ላይ የእድሜ ልክ እገዳ ለመጣል የወሰደው ዕርምጃ አለም አቀፍ ተሞክሮን ያካተተ እንዲሆን አሰልጣኞች ጠየቁ። በቅርቡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት ሆኖ የተመረጠው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ የሃገሪቱ አትሌቶች ዕድሜ ልክ ከእስፖርቱ እንዲታገዱ እንደሚደረግ ከቀናት በፊት ለሮይተርስ መግለጹ ይታወሳል። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አትሌቶች ዕርምጃው አበረታች መድሃኒትን ባለማወቅ የሚወስዱ ...

Read More »

በባህርዳር ግራንድ ሆቴል ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2009) ዛሬ ረቡዕ ማምሻውን በባህርዳር ግራንድ ሆቴል የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በጥቃቱ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ባህርዳር ግራንድ ሆቴል ላይ ጥቃቱን ስላደረሱት ወገኖች ማንነት የታወቀ ነገር የለም። ጥቃቱን የፈጸሙት ወገኖች ለምን አላማ እንደፈጸሙትም ግልጽ አልሆነም። ሆኖም አዲሱን የፈረንጆች አመት በማስመልከት ባለፈው ዕሁድ ...

Read More »