ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ የትምህርት ቤቱ ቤተመጽሃፍ፣ መዝናኛ ክበብና አዳራሾች መስታውቶቻቸው ተሰባብረዋል። ነገ የማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በተቃውሞው ምክንያት ፈተናው አይሰጥም። ትናንት በርካታ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል።
Read More »Author Archives: Central
በአዲስአበባ የመሬት ሊዝ ጨረታ ዋጋ ንረት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ ትላንት ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ይፋ በተደረገው 25ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለአንድ ካሬ ሜትር ቦታ 50 ሺ 250 ብር ከፍተኛ ገንዘብ አንድ ተጫራች አቀረቡ፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 2 ውስጥ ለሚገኝ 208 ካሬሜትር ቦታ ለመግዛት ለአንድ ካሬሜትር ብር 50 ሺ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸውን እንዲመለሱ ተወሰነ
ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ በሕገወጥ መንገድ ወደ ዝንባብዌ ገብተዋል ተብለው በእስር ላይ የነበሩ 34 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን የአገሪቱ ፍርድ ቤት ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ሲል ውሳኔ አስተላልፎአል። በምስራቃዊ ዝንባቢዌ ማሮንዴራ እርሻ ማሳ ውስጥ ከተደበቁበት በፀጥታ ሃይሎች የተያዙት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ አለመያዛቸውን የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ...
Read More »ሂውማን ራይትስ ወች በኢትዮጵያ ጦር የተገደሉ ሶማሊያውያን ጉዳይ እንዲጣራ ጥሪ አቀረበ
ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በግፍ ተገለው ሕይወታቸውን ያጡ 14 ንፁሃን ሰላማዊ ሶማሊያዊያን ዜጎች ግድያ በገለልተኛ አካል ምርመራ ተደርጎበት እንዲጣራ ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ጥሪ አቅርቧል። ባለፈው ዓመት ሃምሌ ወር ላይ በሶማሊያ ባዬ ግዛት ዋርዲሌ ውስጥ የተፈፀመው ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ስድስት ...
Read More »በጎንደር አንድ የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆነ ተሳቢ የጭነት መኪና በቦንብ ተመታ
ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ረቡዕ ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ ከጎንደር ወደ መቀሌ እቃ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማው በ10 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ወለቃ በምትባለዋ መለስተኛ መንደር ላይ ሲደርስ በቦንብ በመመታቱ መኪናው እስከነጭነቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዞ ወድሟል። ምንጮች እንደገለጹት ተሽከርካሪው ሌሊት ጎንደር ላይ እቃዎችን በመጫን ወደ መቀሌ ጉዞ በማድረግ ...
Read More »በአርባምንጭ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ አርሶአደሮች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል
ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሻራ በሚባለው አካባቢ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ አርሶአደሮች ከተማውን ለማስፋት በሚል ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ በመደረጉ፣ ብዙዎች አካባቢውን ጥለው ሲሰደዱ ሌሎች ደግሞ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተዳርገዋል። ለከተማው መስፋፋት በሚል አርሶአደሮች ከፍያ ሳያገኙ መሬታቸውን እንዲለቁ መደረጉን በመቃወም አቤቱታ ቢያሰሙም “ መሬት የመንግስት ነው “ የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። ...
Read More »የህውሃት ድርጅት የሆነው ኢትዮ ችክን በአማራ ክልል ደሮ አርቢዎች ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ የክልሉ መንግስት እንዲያስቆም ተጠየቀ፡፡
ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዋና መስሪያ ቤቱ በመቀሌ ከተማ የሚገኘው ኢትዮ ችክን ከአንዳሳ ደሮ ብዜት ማዕከል የሚፈለፈሉትን ጫጩቶች ወደ ሚፈልገው አካባቢ በመጫን የሚያከፋፍል በመሆኑ ከአሁን በፊት ከማዕከሉ በመረከብ በጫጩት እርባታ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከስድስት ዓመት በፊት በትግራይ መንግስት እና በአረብ ሃገር ባለሃብቶች ቅንጅት የተቋቋመው ኢትዮ ችክን ንብረትነቱ በህውሃት ቁጥጥር ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በሰንደቅ ጋዜጠኛ ላይ የመሰረቱት ክስ ውድቅ ኾነ።
ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በፍሬው አበበ ላይ ክስ የመሰረቱት ዲያቆን ዳን ኤል ክብረት “ አቡነ ማትያስ ፣ ለመንግስት የደህንነት፣ ለቤተክርስቲያን ደግሞ የድህነት ስጋት” በሚል ርዕስ በቤተክርስቲያኒቱ ስላለው ብልሹ አሠራርና ሙስና በግል ድረ ገጹ የጻፈውን ጽሁፍ ጋዜጣው ላይ በማተሙ ነው። በሁኔታው የተበሳጩት አባ ማትያስ በጋዜጠኛው ላይ የወንጀል ክስ ...
Read More »በኩዌት አንድ ኢትዮጵያዊትን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ አገር ዜጎች በስቅላት ተቀጡ
ኢሳት (ጥር 17 ፥ 2009) የኩዌትት መንግስት አንድ ኢትዮጵያዊትን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን ዛሬ ረቡዕ በስቅላት የሞት ቅጣት መፈጸሙን የሃገሪቱ ዜና አገልግሎት ኩና ዘገበ። ከአንድ ኢትዮጵያዊት በተጨማሪ ሁለት የኩዌት፣ ሁለት የግብፅ፣ አንድ የባንግላዴሽ፣ እና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ እንዲሁም ሰዎችን በማገት ድርጊት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ድርጊቱ ሊፈጸምባቸው መቻሉን የኩዌት መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ስሟ ያልተገለጸው ኢትዮጵያዊትና ሌላ ...
Read More »ደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንቷ በቅርቡ በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ሃገሪቱን ከተለያዩ ሃገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተካሄደ እንደሆነ ይፋ አደረገ
ኢሳት (ጥር 17 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን መንግስት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ሳልባ-ኪር በቅርቡ በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ሃገሪቱ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተካሄደ እንደሆነ ይፋ አደረገ። በሁለቱ ሃገራት መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይትም የኢትዮጵያና የግብፅን ግንኙነት ያነሳ አልነበረም ሲሉ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ቃል አቀባይ የሆኑት አቴኔ ዌክ ማስታወቃቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። የደቡቡ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልባ ኪር በቅርቡ በግብፅ ያካሄዱትን ጉብኝት ...
Read More »