Author Archives: Central

በሶማሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃላፊዎች በጦር መሳሪያ ንግድና በሌሎች የሙስና ወንጀሎች ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 25 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰርቶ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ አመራርነት የተቀመጡ ሃላፊዎች በጦር መሳሪያ ንግድና ሌሎች የሙስና ወንጀሎች ውስጥ ተሰማርተው መገኘታቸውን የሃገሪቱ መገኛኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። ለበርካታ አመታት በሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት በሃላፊነት በማገልገል ላይ ያሉ ሃይሌ ገብሬ በዚህ ህገወጥ ድርጊት በመሰማራት ከፍተኛ ንብረት በማካበት ላይ መሆናቸውን ሱና ታይምስ የተሰኘ ጋዜጣ የአመራሩን ፎቶ በማስደገፍ ለንባብ አብቅቷል። በቅፅል ...

Read More »

በሶማሌ ክልል አስተዳደር ድጋፍ ይደረግላቸዋል የተባሉ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ግድያና የንብረት ዘረፋ እየፈጸሙ እንደሆነ ኦፌኮ ገለጸ

ኢሳት (ጥር 24 ፥ 2009) በፌዴራልና በሶማሌ ክልል አስተዳደር ድጋፍ ይደረግላቸዋል የተባሉ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልልና የብሄሩ ተወላጆች ላይ ግድያን ጨምሮ የንብረት ዘረፋና ወረራን እየፈጸሙ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ረቡዕ ይፋ አደረገ። ከሁለት ወር በፊት ጀምሮ በተለይ በክልሉ በምስራቅ ሃረርጌ፣ ባሌና ቦረና ዞኖች ውስጥ መፈጸሙ የጀመረው ይኸው ድርጊት ያለማንም ከልካይ አሁንም ድረስ ተጠናክሮ መቀጠሉን ፓርቲው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ...

Read More »

የኢንተርኔት የስለላ ወንጀል ክስ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኝ የይግባኝ ፍርድ ቤት ሊታይ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 24 ፥ 2009) በኢትዮጵያ መንግስት ላይ በአንድ አሜሪካዊ ዜጋ የተመሰረተ የኢንተርኔት የስለላ ወንጀል ክስ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኝ የይግባኝ ፍርድ ቤት ሊታይ መሆኑ ተገለጸ። ኪዳኔ ቪ የተባሉት አሜሪካዊ የቀረበውን ክስ በውክልና ይዞ የሚገኘው ኤሌክትሮኒክስ ፍሮንቴየር ፋውንዴሽን የተሰኘ ተቋም ክሱ እንዲቀጥል የሚያስችል የመከራከሪያ ውይይት ነገ ሃሙስ ለፍርድ ቤት እንደሚቀርብ አስታውቋል። ጆንስ ዴይ ኤንድ ሮቢንስ ካፕላን የተሰኙ ሁለት የአሜሪካ ...

Read More »

ኢትዮጵያ በዲሞክራዊያዊና በሰብዓዊ መብት አያያዟ ነጻ ያልሆነች አገር ተብላ ተፈረጀች

ኢሳት (ጥር 24 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በአለማችን በሰብዓዊ መብት አያያዛቸውና በዴሞክራሲ ስርዓታቸው ነጻ ያልሆኑ ተብለው ከተፈረጁ 25 ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መፈረጇን መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም ይፋ አደረገ። የ2016 አም አመታዊ ሪፖርቱን ለንባብ ያበቃው ፍሪደም ሃውስ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተለይ ባለፈው የፈረንጆች አመት ከመቼውም ጊዜ የተባባሰ ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች ተቀስቅሶ ...

Read More »

የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ከአለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጅምላ እንዲወጡ ያስተላለፈው ጥሪ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት (ጥር 24 ፥ 2009) የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት ከአለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጅምላ እንዲወጡ ያስተላለፈው ጥሪ ተቃውሞን ቀሰቀሰ። ትላንት ማክሰኞ ለሁለት ቀን ሲያካሄድ የቆየውን የመሪዎች ጉባዔ ያጠናቀቀው ህብረቱ ወደ 34 አካባቢ የሚጠጉ የአፍሪካ የፍርድ ቤቱ አባላት በጅምላ እንዲሰናበቱ መጠየቁን ቢቢሲ ዘግቧል። ይሁንና፣ ናይጀሪያና ሴኔጋል ህብረቱ ያቀረበውን ጥሪ አጥብቀው ኮንነዋል። በርካታ የአፍሪካ ሃገራት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፍትሃዊ ...

Read More »

ባለፈው አመት ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመግባት ከሞከሩ አፍሪካውያን መካከል 5ሺ የሚሆኑ በባህር ላይ መሞታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 24 ፥ 2009) ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 አም ከሊቢያ የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለመግባት ከሞከሩ ከ180ሺ በላይ ስደተኞች መከክል 5ሺ የሚሆኑት መሞታቸው ተገለጸ። በቅርቡ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞችን አሳፍሮ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በማቅናት ላይ የነበረ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር የመስጠም አደጋ አጋጥሞት 180 ሰዎች መሞታቸውን የጣሊያን የባህር ህያል ባለስልጣናት አመልክተዋል። ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በመሰደድ ላይ ያሉ ...

Read More »

በባህርዳር ኬላ ላይ ለሁለተኛ ቀን ከባድ ፍተሻ እየተካሄደ ነው

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊሶች ከትናንት ማክሰኞ ጀምሮ እስካ ዛሬ ድረስ የተጠናከረ ፍተሻ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች የመፈተሽ ተራ እስከሚደርሳቸው ረጃጅም ሰልፎችን ሰርተው ለሰዓታት ቆመው መዋላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ዋናው ፍተሻ የሚካሄደው በመራዊ አቅጣጫ ባለው የአዲስ አበባ ባህርዳር መስመር ላይ ሲሆን፣ ወደ ከተማው የሚገቡና የሚወጡ መኪኖች ጥብቅ ፍተሻ ይደረግባቸዋል። በአካባቢው በርካታ የፌደራል ፖሊሶች ...

Read More »

በአርባምንጭ የሚገኘው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመፍረስ ላይ ነው ተባለ

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት ለአካባቢው ህዝብ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ በቡልጋሪያና በዲሞክራቲክ ጀርመን ድጋፍ በደርግ መንግስት ተጀምሮ ፣ በ1985 ዓም የተመረቀው የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመፈራረስ ላይ ይገኛል። ሰራተኞች እንደሚሉት ፋብሪካው በሶስት ፈረቃ በሚሰራበት ወቀት ለ1500 ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሮ ነበር። ፋብሪካው ስራ እንደጀመረ ወዲያውኑ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አማካኝነት ለህወሃቱ አልሜዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እንዲሸጥ ...

Read More »

በሰሜን ወሎ በጥልቅ ተሃድሶ ስም በተጠራው ስብሰባ ላይ ውዝግብ ተነሳ

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ወሎ ትናንት ጥር 24 2009 ዓም በዞኑ ጽቤቶች የጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ ሰራተኞችና አመራሩ መስማማት ሳይቸሉ ቀርተዋል ። አመራሩ “በሀገሪቲ በዚህ ደረጃ ለሚታየው ውድቀት ተጠያቂው ሲቪል ሰርቪሱ “ ሲል፣ ሰራተኛው ደግሞ ለውድቀቱ ተጠያቄው ሲቪል ሰርቪሱ ሳይሆን አመራሩ ነው “ በማለት ተከራክሯል። ሰራተኛውን ካስገረሙት ሹመቶች መካከል የዞን ማህበራት ሃላፊ ሆና ...

Read More »

የጋምቤላ ፖሊስ ከዚህ በፊት በክልሉ ተፈጽሞ ከነበረው ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አዋልኩ አለ

ኢሳት (ጥር 23 ፥ 2009) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በአንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ተፈጽሞ ከነበረው ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ማክሰኞ አስታወቀ። ከአንድ ወር በፊት በክልሉ ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢ 40 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ በተፈጸመበት ጥቃት አምስት ሰዎች በተከፈተባቸው የተኩስ ዕርምጃ መሞታቸው ይታወሳል። በዚሁ ጥቃት በትንሹ ስምንት ተሳፋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበርም ...

Read More »