ኢሳት (ጥር 29 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ስድስት የአየር ሃይል አባላት ላይ ከሶስት እስከ 10 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት አስተላለፈ። ከሳሽ አቃቤ ህግ በሰኔ 2007 አም ተከሳሾቹ የአየር ሃይልን በመክዳት ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ እንደተያዙ በክሱ ...
Read More »Author Archives: Central
የቅዱስ ላሊበላ አቢያተ-ክርስቲያናት አስተዳደሪ ቆሞስ አባ ወልደተንሳይ አባተ በመንግስት ጣልቃገብነት ከሃገር መሰደዳቸውን ገለጹ
ኢሳት (ጥር 29 ፥ 2009) የታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ አቢያተ-ክርስቲያናት አስተዳደር የነበሩት ቆሞስ አባ ወልደተንሳይ አባተ በመንግስት ጣልቃገብነት ከሃገር መሰደዳቸውን ገለጹ። የላሊበላ አብያተክርስቲያናት ሰበካ ጉባዔ በመንግስት ባለስልጣናትና በብአዴን ካድሬዎች ቁጥጥር ስር መውደቁንም ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ አመልክተዋል። ወልቃይት የትግራይ ነው በሚል ለህዝቡ እንዲያስተምሩ ግፊት ይደረግባቸው እንደነበርም አመልክተዋል። በመጨረሻም ምክንያቱ ባልታወቀና ባልተገለጸ መንገድ በስፍራቸው ሌላ ሰው ተሹሞ መገኘቱን ገልጸዋል። መልአከ ጸሃይ ቆሞስ አባወልደተንሳዬ ...
Read More »በአዲስ አባባ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጄክት የፋይናንስ ችግር ገጠመው
ኢሳት (ጥር 29 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪዎችን የቤት ችግር ይቀርፋሉ ተብለው ግንባታቸው የተጀመረ የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮጄክቶች የፋይናንስ ችግር እንዳጋጠማቸው ተገለጸ። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኮንትራክተሮችና እቃ አቅራቢዎች ለሰሩት ስራ ክፍያ እየተከፈላቸው ባለመሆኑ ችግር ውስጥ እንደሚገኙና ስራቸውንም ማከናወን የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ መሆኑን እንዳስታወቁ ሪፖርተር ጋዜጣ በእሁድ እትሙ ዘግቧል። የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ...
Read More »የግብፅ መንግስት የደቡብ ሱዳን አማጺያን ላይ የአየር ጥቃት አልፈጸምኩም አለ
ኢሳት (ጥር 29 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን አማጺያን በሳምንቱ መገባደጃ በግብፅ አየር ሃይል የአየር ጥቃት ተፈጽሞብናል ያሉትን ቅሬታ የግብፅ መንግስት አስተባበለ። ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር በአለመግባባት ውስጥ የሚገኙት አማጺያን የግብፅ አየር ሃይል ከቀናት በፊት በዩኒቲ ግዛት በሚገኙ ሶስት ስፍራዎች የአየር ጥቃት ተፈጽሞብናል ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ባለፈው ወር በግብፅ ጉብኝት ያደረጉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልባኪር ከግብፅ መንግስት ጋር የተለያዩ ...
Read More »በበለሳ የህወሃት/ኢህአዴግ ሰራዊት በታጋዮች ላይ ያደረገው ከበባ ተሰበረ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አርባያ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የነጻነት ታጋዮችን በአንድነት በማሰባሰብ የትግል ምክክር ለማድረግ የተጠራውን ስብሰባ ለመክበብ ሙከራ ያደረገው የህወሃት/ኢህአዴግ ሰራዊት፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት መበታተኑን ታጋዮች ተናገሩ። በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የነጻነት ታጋይ ቴዎድሮስ እንደገለጸው፣በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በጋራ በሚወጣ የትግል ስትራቴጂ አገዛዙን ለመግጠም ምክክር ለማድረግ በተጠራ ስብሰባ ላይ ህወሃት መራሹ አገዛዝ፣ አስቀድሞ ...
Read More »አውስኮድ እንደ ህብር ስኳር ሁሉ በሜቴክ መዘረፉን ሰራተኞች ተናገሩ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰራተኞች እንደገለጹት የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት /አውስኮድ/ከ2002 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ የጣና በለስን የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ለመስራት ከፌዴራል መንግሥት የ6 ቢልየን ብር የግንባታ ስራ ውል ተሠጥቶት ሠራተኞች በሁለት ፈረቃ ቀንና ሌሊት በማሰራት የቦይ ሥራ ስርቶ አስረክቧል። የሸንኮራ አገዳው ዝግጁ እንዲሆን ቢደረግም፣ ፋብሪካውን እገነባለሁ ብሎ ኮንትራት የወሰደው በሜ/ር ጄኔራል ክንፈ ...
Read More »በአርባምንጭ ከተማ የስፖርት ሜዳ ላይ የተቃውሞ ወረቀት ተበተነ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት በአርባምንጭ ከተማ ኳስ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ሜዳ የገቡ ሰዎች የአርባ ምንጭ ወጣቶች ለመከላከያ ሰራዊት እንዳይመለመሉ የሚመክር እንዲሁም ወጣቶች ለመብታቸው እንዲነሱ የሚጠይቅ ወረቀት ተበትኖ ማግኘታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። በራሪ ወረቀቱ “የአገር መከላከያ ሰራዊት ምልመላ ለአገር ድንበር ጥበቃ ወይስ እናትና አባትን መግደያ?” የሚል ርእስ ያለው ሲሆን፣ መላው የአገራችን ህዝቦች በወያኔ ኢህአዴግ የከፋፍሎ መግዛት ...
Read More »የሸጎሌ ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ማግኘት ካቆሙ 3 ወራት እንዳለፋቸው ተናገሩ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ ሸጎሌ ኪዳነ ምህረት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ዉሃ ከተቋረጠ ሶስት ወራት ማለፉን ተናገሩ። ወትሮም ቢሆን በ15 ቀናት ዉስጥ አንድ ሌሊት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ የሚለቀቀው ውሃ ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። በአካባቢው የሚኖሩ ህጻናትና አቅመ ደካሞች ከውሃ ጋር በተያያዘ ለሚመጡ በሽታዎች ...
Read More »ኮማንደር ዋኘው አዘዘው መንግስትን በመክዳት ወንጀል ተከሰሰ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰሜን ጎንደር ዞን የጸረሽምቅ ግብረሃይል አዛዥ የሆነው ኮማንደር ዋኘው አዘዘው ከወራት እስር በሁዋላ መንግስትን በመክዳት ወንጀል መከሰሱ ታውቋል። ኮማንደር ዋኘው በጎንደር በነበረው ህዝባዊ አመጽ ፓርቲውንና መንግስትን በመክዳት ከህዝብ ጋር በመሆን በመንግስት ላይ የተነሳውን አመጽ ለማስቆም ባለመቻሉ፣ መንግስትንና ፓርቲውን ከድቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል። በተለያዩ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ...
Read More »ለመለስ ዜናዊ ፓርክ በተመደበው በጀት ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈጸመ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ መስተዳድር የጉለሌ እጽዋት ማእከል በሚል ሲጠራ የነበረውና በቅርቡ የመለስ ዜናዊ ፓርክ ተብሎ የተሰየመው እንጦጦ ላይ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት የታጠረው ጥብቅ የደን ተቋም በያዝነው አመት 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ሂሳብ ፣ ለኦዲት ምቹ ያልሆነ ነው በሚል ባክኖ መቅረቱን ምንጮች ገልጸዋል። ለፓርኩ ዝግጅት የወጣ ወጪ ቢኖርም አብዛኛው ወጪ ህጋዊ ደረሰኝ ...
Read More »