Author Archives: Central

ለኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተላከውና በአገዛዙ ላይ የቦንብ ናዳውን የሚያወርደው የመምህራን ግምገማ ሪፖርት ኢሳት እጅ ገባ

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጥር ብአዴን/ማዕ.ኮ/2131ሪ በቀን 23/05/2009 ዓ/ም ለኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት እንዲደርስ የተጠቃለለው የጥልቅ ትሃድሶ የመምህራን መድረክ ማጠቃላያ ሪፓርት ኢሳት እጅ ገብቷል፡፡ ይህ በኢሜል የተላከው ሰነድ እንደሚያሳያው ከ8 ሺ በላይ መምህራን በዞን ደረጃ ቀጠና ተለይቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በአምስት ዋና ዋና ምድቦች አርዕሰተ ጉዳዮች እየተመራ የተካሄደ ሲሆን ኢህአዴግ አደጋ ውስጥ መግባቱን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ መምህራን ስለድህነት፣ ...

Read More »

በትግራይና አማራ ድንበር አካባቢ የተነሳውን ግጭት እንዲያዩ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንደኛው በድጋሜ ታፈኑ

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ አወዛጋቢ ከሆኑት ቦታዎች መካከል አንዱ የሆነውንና የትግራይ ክልል የእኔ ነው በማለት ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚጠይቀውን ግጨው እየተባለ የሚጠራውን ቦታ ሁኔታ ለማየት ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አቶ ዋኘው ደሳለኝ ጥር 26 ቀን 2009 ዓም ማክሰኚት ላይ በድጋሜ በህወሃት የደህንነት አባላት ታፍነው ተወስደዋል። ግለሰቡ ያሉበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም። ኢህአዴግ ...

Read More »

በምስራቅ አፍሪካ የርሃብ አደጋው እንደ አዲስ ማገርሸቱን ተከትሎ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል ሲል የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት አስጠነቀቀ።

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀጠናው በተከሰተው አዲሱ ድርቅ ምክንያት ቁጥራቸው 11.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለከፍተኛ የርሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ አፋጣኝ የረድኤት እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እና የድርቁ ደረጃ በርሃብ መለኪያ Integrated Phase Classification (IPC) ከሶስት ነጥብ በላይ መሆኑን አስታውቋል። በሶማሊያ 2.9 ሚሊዮን፣ በኬንያ 2.7 ...

Read More »

በኢትዮጵያ በአንድ አመት ውስጥ ከአራት ሺ በላይ ዜጎች በተሽከርካሪ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የትራንስፖርት ሚንስቴር ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ።

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ውስጥ 2008 ዓ.ም ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ባጋጠመ ከተሽከርካሪ ጋር ተዛማጅ በሆኑ በደረሱ አደጋዎች በድምሩ 4 ሽህ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የትራፊክ አደጋ ከዓመት ወደ ዓመት እየተባባሰ መምጣቱን እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጥቂት ...

Read More »

የአባይ ድልድይ በመዘጋቱ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የተገነባው የጎጃም ጎንደር አባይ ድልድይ ከዛሬ ጠዋት 4:00 ሰዓት ጀምሮ በቆርቆሮ ተዘግቶ አገልገሎት መስጠት አቁሟል ፡፡ ከጎንደር እና ከጎጃም የሚመጡ መሻገር የግድ የሆነባቸው ተሽከርካሪዎች በሶስት ረድፍ ተሰልፈው በአማራ ልዩ ኃይል ፈቃድ አልፎ አልፎ በድልድዩ አንድ መስመር ብቻ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ እየተደረገ ሲሆን፣ ህዝቡ በከፍተኛ ምሬት በእግሩ እየተጓዘ ነው። በእድሜ የገፉ ...

Read More »

በአፋር ክልል ሰፍረው የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሁለት አርብቶ አደሮች የፈጸሙት ግድያ ውጥረት ቀሰቀሰ

ኢሳት (ጥር 30 ፥ 2009) በአፋር ክልል ልዩ ስሙ ዞን ሶስት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ስፍራው የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከቀናት በፊት በሁለት አርብቶ አደሮች ላይ የፈጸሙት ግድያ በአካባቢው ውጥረት መቀስቀሱ ተገለጸ። በዚሁ አካባቢ ወልጅ አልባ የሰፍሩ ወደ ስድስት ሺ አካባቢ ተቀናሽ ወታደሮች ከአርብቶ አደሮች ጋር አለመግባባት ውስጥ በመሆናቸው ተደጋጋሚ ግጭቶች በመከሰት ላይ መሆናቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሃላፊ የሆኑት አቶ ...

Read More »

በባንክና ፋይናንስ ተቋማት ተሰማርተው የነበሩ የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን  አክሲዮኖች ለጨረታ መቅረባቸው ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 30 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የአክሲዮን ድርሻ እንዳይኖራቸው ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ ባንኮች በትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ስር የነበሩ አክሲዮኖች ለጨረታ አቀረቡ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ አክሲዮን የነበራቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ የያዙትን አክሲዮን እንዲመልሱ ማሳሰቢያን አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል። የጊዜ ገደቡን መጠናቀቅ ተከትሎም አዋሽ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሌሎች ሃገራት ያልተከፈለው ገንዘብ በስራው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ገለጸ

ኢሳት (ጥር 30 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናጀሪያ ግብፅና ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ያልተከፈለው ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ በስራው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን የድርጅቱ ሃላፊዎች ገለጹ። አየር መንገዱ ለነዚህ ሃገራት በተለያዩ ጊዜያት የአየር ትኬትና ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች ሲሰጥ ቢቆይም ለአገልግሎቱ ክፍያ ሳይፈጸምለት በርካታ ጊዜያት መቆጠሩን ሮይተርስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። ...

Read More »

የዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲቫል በዋሽንግተን ሲያትል ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 30 ፥ 2009) በየአመቱ በሰሜን አሜሪካ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረው የዘንድሮው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል የፊታችን ሃምሌ በዚሁ በአሜሪካ ዋሽንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ እንደሚካሄድ መወሰኑን አዘጋጆች አስታወቁ። ለ34ኛ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማሰባሰብ የሚካሄደው ይኸው አመታዊ በዓል በፈረንጆቹ ከሃምሌ 2 እስከ 8 2017 ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል። የባለፈው አመት ዝግጅት በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ የዘንድሮውን ...

Read More »

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ በተከሰተው ግጭት የመንግስት አካላት እንደተሳተፉበት ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 29 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልል ከሶማሌ ክልል ጋር በሚዋሰንበት ድንበር በቅርቡ ለሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው ግጭት የመንግስት አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ገለጸ። የኦሮሚያ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በፌዴራልና በሶማሌ ክልል አስተዳደር ድጋፍ የሚደረግላቸው የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ግድያና ዘረፋን እየፈጸሙ ናቸው ሲል ባለፈው ሳምንት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በአካባቢው በመንግስት ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው ዕርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ...

Read More »