Author Archives: Central

ዶናልድ ትራምፕ በደቡብ ሱዳን ያለውን ግጭት እልባት ለመስጠት ወደ ጁባ አንድ ልዑክ ሊልኩ ነው

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በደቡብ ሱዳን ያለው ግጭት እልባት በሚያገኝበት ዙሪያ ላይ የሚመክር ልዑካን በተያዘው ሳምንት ወደ ጁባ እንደሚልኩ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ማክሰኞ ገለጹ። የአሜሪካ የልዑካን ቡድን ከፕሬዚደንት ሳል-ባኪር ጋር ከሚያደርገው ውይይት ጎን ለጎን የተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ምክክር እንደሚያካሄዱ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ...

Read More »

ሩሲያ ለግብፅ 50 ተዋጊ አውሮፕላኖች ለማቅረብ ስምምነቷን ገለጸች

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) ሩሲያ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለግብፅ 50 ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለማቅረብ ከሃገሪቱ ጋር ስምምነት መድረሷን የሩሲያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ማክሰኞ ይፋ አደረጉ። የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አልሲሲ በቅርቡ ባደረጉት ውይይት ተዋጊ ጀቶች እንዲቀርቡ ስምምነት ተደርሶ እንደነበር አህራም የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ይሁንና  የግብጽ ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር ተደርሷል የተባለውን ስምምነት መቼ እንደተደረሰና በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር ...

Read More »

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተፈናቀሉት የኦሮሞ አርሶአደሮች ውስጥ 70 በመቶው ከመፈናቀላቸው በፊት ከነበረው በባሰ የኑሮ ጉስቁልና ውስጥ እንደሚገኙ ታወቀ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የአዲስ አበባ መስተዳድር ባስጠናው ጥናት በአዲስ አበባና ዙሪያ ከተሞች ከተፈናቀሉ የኦሮሞ አርሶደሮች መካከል በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባሉት 6 በመቶ ብቻ ሲሆኑ፣ 70 በመቶ ያህሉ ግን ከመፈናቀላቸው በፊት ከነበራቸው የኑሮ ደረጃ ባሽቆለቆለ ኑሮ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። በኦሮምያ ለተነሳው ተቃውሞ መነሻ ከነበሩት ምክንያቶች መካከል ...

Read More »

በጎንደር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን “እናንሳው አናንሳው” በሚል የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሙከራ ቢደርገም የህዝቡ መልስ ባለስልጣኖችን አስደንግጧል

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ የጎንደር ቀበሌዎች በተካሄዱ የህዝብ ስብሰባዎች፣ የአገዛዙ ካድሬዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት በኩል የህዝቡ አስተያየት ምንድነው በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ህዝቡ ግን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በጽሁፍ ፣ “ እናንትን አንቀበላችሁም፣ አናውቃችሁም፣ ከህዝብ ውጭ ሆናችሁዋል” የሚል መልስ በብዛት መስጠቱ ካድሬዎችን አስደንግጧል። አንዳንድ ሰዎች “ አዋጁን ስታውጁ እኛን አላማከራችሁንም፣ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በረሃብ ለተጠቁ ኢትዮጵያኖች 8.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አፋጣኝ እርዳታ ለገሰ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እርዳታው በምስራቅ እና ደቡባዊ ኢትዮጵያ በድርቅ ተጎጂ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ይውላል ተብሏል። ከ 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ውስጥ 785 ሽህ የሚሆኑት ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን ተመድ በሪፖርቱ ጠቅሷል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አስተባባሪ ኮሚቴ ሃላፊ ስቴፋን ኦብሪን ፣ በድርቁ ምክንያት በተለይ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰማአታት ሃውልት ላይ የህወሃት አርማ መተከሉ ትችት አስከተለ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊያን የሚታሰቡበት የካቲት 12 ቀን በተቀዛቀዘ ሁኔታ እንዲከበር ከመደረጉም በላይ በሃውልቱ መታሰቢያ ላይ የህወሃት አርማ እንዲውለበለብ መደረጉ የከተማዋን ነዋሪዎች በእጅጉ አበሳጭቷል። በድርጊቱ የተበሳጩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ “ድርጊቱ ነውር ነው” በማለት አስተያየታቸውን እየሰጡ ሲሆን፣ “ህወሃት ሆን ብሎ የጀግኖችን ሰማአታት ቀን ከራሱ ታጋዮች ጋር እኩል ለማድረግ ያደረገው ...

Read More »

ለደቡብ ሱዳን ሰላም መስፈን ከጎረቤት አገራት ውጭ ያሉ አገሮች ሙከራ ማድረግ እንዳለባቸው የአሜሪካው አምባሳደር ተናገሩ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ ልዑክ የሆኑት አምባሳደር ዶናል ቡዝ በለንደን ሻተም ሃውስ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአካባቢው አገራት የራሳችውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት እያወሳሰቡት ነው ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አገራት በሂደቱ ላይ በቀጥታ ተጽእኖ የሚያደርጉ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ የውይይቱን አቅጣጫ ሁሉ እስከማስቀየር ይደርሳሉ ። አንዳንዶች ሸምጋይ ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያ ለጸጥታ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ምርመራ እንዲደረግበት ተጠየቀ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያ የጸጥታና የዲፕሎማቲክ አባላት ስልጠና እንዲያገኙ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ምርመራ እንዲካሄድበት የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ። የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር እንዲፈቱ ዘመቻን እያካሄዱ ባለበት ወቅት የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ በመስጠት ላይ ያለው ይኸው ድጋፍ “አሳፋሪ” ነው ሲል ሪፕሪቭ የተሰኘ ተቋም ተቃውሞን አቅርቧል። ከተለያዩ አለም አቀፍ አካላት የቀረበን ጥያቄ ...

Read More »

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ ኢትዮጵያውያን መካከል 500 ሲታሰሩ 65ቱ በግርፋት እንዲቀጡ ተወሰነ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ የሃገሪቱ መንግስት በመኖሪያ ፈቃድ ላይ የጨምረውን ክፍያ እንዲያሻሽል ጥያቄ ካቀረቡ ኢትዮጵያውያን መካከል 500 አካባቢ የሚሆኑት መታሰራቸውን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 65ቱ ኢትዮጵያውያን እያንዳንዳቸው ህዝብ  በተሰበሰበት 40 ጅራፍ እንዲቀጡም ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል 65ቱ በ40 ግርፋት እንዲቀጡ በመዲናይቱ ካርቱም የሚገኝ ፍርድ ቤት ብይን መስጠቱን ራዲያ ዳባንጋ የተሰኘ ...

Read More »

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ ኢትዮጵያውያን መካከል 500 ሲታሰሩ 65ቱ በግርፋት እንዲቀጡ ተወሰነ

ኢሳት (የካቲት 13 ፥ 2009) በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ የሃገሪቱ መንግስት በመኖሪያ ፈቃድ ላይ የጨምረውን ክፍያ እንዲያሻሽል ጥያቄ ካቀረቡ ኢትዮጵያውያን መካከል 500 አካባቢ የሚሆኑት መታሰራቸውን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 65ቱ ኢትዮጵያውያን እያንዳንዳቸው ህዝብ  በተሰበሰበት 40 ጅራፍ እንዲቀጡም ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል 65ቱ በ40 ግርፋት እንዲቀጡ በመዲናይቱ ካርቱም የሚገኝ ፍርድ ቤት ብይን መስጠቱን ራዲያ ዳባንጋ የተሰኘ ...

Read More »