Author Archives: Central

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳል-ባኪር ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ሃሙስ አዲስ አበባ ገቡ

ኢሳት (የካቲት 16 ፥ 2009) በግብፅ ጉብኝትን በማድረጋቸው ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተዋል የተባሉት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳል-ባኪር ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ሃሙስ አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለጸ። ፕሬዚደንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በሚሻሻልበትና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ መጠበቁን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። ፕሬዚደንት ኪር በቅርቡ በግብፅ ...

Read More »

ተመድ በሶማሌ ክልል ያለውን የድርቅ አደጋ ለመታደግ የመደበውን የገንዘብ ድጋፍ ተከትሎ መንግስት የእርዳታ አቅርቦት ወደስፍራው እንዲጓጓዝ ማድረጉን አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 16 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሌ ክልል በመባባስ ላይ ያለውን የከፋ የድርቅ አደጋ ለመታደግ የመደበውን የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ተከትሎ መንግስት ከመጠባቂያ ምግብ ክምችት የእርዳታ አቅርቦት ወደ ስፍራው እንዲጓጓዝ ማድረጉን አስታወቀ። በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ ያለው ይኸው የድርቅ አደጋ የሰው ህይወት ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩንም የእርዳታ ተቋማት ገልጸዋል። በሶማሌ ክልል የሚገኙ ዘጠኝ ዞኖች ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና የሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተባቸው

የካቲት ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ጃዋር ሙሃመድ፣ ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሌሉበት የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል። በአውሮፓ ኅብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ቤልጅየም በመገኘት ንግግር አድርገው ሲመለሱ ህዳር 21 ቀን 2009 ዓ.ም ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር ከመኖሪያ ...

Read More »

በንፋስ ስልክ ክፍለከተማ ስር የሚገኙ ነዋሪዎች ግራ መጋባታቸውን ገለጹ

የካቲት ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ክፍለከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ንብረታቸውን በ7 ቀናት ውስጥ አንስተው መሬቱን እንዲያስረክቡ ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ደብዳቤ እንደተሰጣቸው እና በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ንብረታቸውን የማያነሱ ከሆነ አስተዳድሩ እርምጃ እንደሚወስድ እንደተነገራቸው ለኢሳት ገልጸዋል። በከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች በግለሰቦች ቤት እየሄዱ ቤታቸውን አፍርሰው እንዲወጡ ሲያስጠነቅቁና ደብዳቤም በግድግዳዎች ...

Read More »

መከላከያን ጥለው የሚጠፉ ወታደሮችን የማሳደድ ዘመቻ ተጀመረ

የካቲት ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘረኝነትን በመጥላት እንዲሁም በህዝብ ላይ የሚወሰደውን የግፍ እርምጃ በመቃወም ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊቱን እየጣሉ የሚጠፉ ወታደሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፣ በሚጠፉት ወታደሮች ቦታ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመቅጠር የሚደረገው ጥረት አልተሳካም። ይህን ተከትሎም የሚጠፉ ወታደሮችን በማሳደድ በግድ እንዲቆዩ የማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በአንዳንድ አካባቢዎች ወታደሮች ላለመያዝ በሚያደርጉት ራስን ...

Read More »

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ720 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ስታዲየም እያስገነባ ነው

የካቲት ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለቀጣዩ ዓመት የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ተረኛ አዘጋጅነት የተመረጠው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ720 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት በሰመራ ከተማ 30 ሺ ሕዝብ የሚይዝ ዘመናዊ ስታዲየም እያስገነባ ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት በከፍተኛ ድርቅ ከተጠቁ ክልሎች ቀዳሚ የሆነው የአፋር ክልል ፣ አሁንም ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ በድርቁ እየተጎዳ ባለበት ሰአት የሚያስገነባውን ስታዲየም ...

Read More »

ህወሃት በዱባይ አገር በሚገኘው እጅግ ዘመናዊ አለማቀፍ ሆቴል ውስጥ የምስረታ በአሉን ሊያከብር ነው

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት ኩባንያ ሙሉ ድጋፍ እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትብብር ህወሃት የተመሰረተበትን 42ኛ አመት የልደት በአል በአለማችን እጅግ ዘመናዊና ውድ በሚባለው ቡርጂ አል አራብ ጁሚራህ ሆቴል ውስጥ ከአርብ እስከ እሁድ እንደሚያከብር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በልዩ ትእዛዝ በተዘጋጁ አምስት አውሮፕላኖች የህወሃት መስራች አባላትና ባለስልጣኖች እንዲሁም ወጣት የህወሃት ደህንነቶች፣ ባለሃብቶችና ጠንካራ አባላት ...

Read More »

በደቡብ ክልል ወደ 20 ሺ የደህዴን አባላት መባረራቸው ተገለጸ

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የክልሎችን የተሃድሶ ሪፖርት በሰማበት ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከ18 ሺ 250 የበታች አመራሮችን እንዲሁም 1920 ከፍተኛ፣ መካከለኛና ጀማሪ አመራሮች መባረራቸውን ተናግረዋል። በእነዚህ ሰዎች ቦታ ላይ 2 ሺ 359 አዳዲስ አመራሮች መተካታቸውን ገልጸዋል። አቶ ደሴ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አመራሮችን አባረናል ቢሉም ፣ ያባረሯቸውና የተኳቸው ...

Read More »

የብአዴን መሪዎች የጎንደርን ህዝብ በማባበል ስራ ላይ ቢጠመዱም አልተሳካለቸውም

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህዝባዊ አመፁ ከተቀሰቀሰ እና አስቸኳይ አዋጅ ከታወጀ በኃላ ባሉት አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ፣ የመከላከያ ሹማምንት ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎችም የኢህአዴግ አመራሮች በጎንደር እየተገኙ እራሳቸውን እየሰደቡ፣ ችግሮችን ለመፍታት ሲምሉ እና ሲገዘቱ ቆይተዋል። ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን አራተኛ መድረክ፣ ...

Read More »

ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው የታሰሩ 63 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለኢህአዴግ መንግስት ተላልፈው ተሰጡ

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሳለፍነው ሳምንት ሱዳን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት በሰላማዊ መንገድ ሕጋዊ መብቶቻቸውን የጠየቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ በኤንባሲው ፈቃጅነት በሱዳን የጻጥታ ኃይሎች ድብደባ፣ የጅምላ እስራት፣ አካላዊ ጥቃቶች መፈጸሙ እና አንድ ስደተኛም በስለት ተወግተው መገደላቸው ይታወቃል:: በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው በተጨናነቀ በእስር ቤት ታጉረው የተለያዩ ሰቆቃ ሲፈፀምባቸው ከነበሩት ስደተኞች ...

Read More »