Author Archives: Central

ብአዴን ባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለሉንና ዳሸን ቢራ በኪሳራ እየማቀቀ መሆኑን አስታወቀ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን የልማት ድርጅት የሆነው ጥረት ከርፖሬት ሰሞኑን በዋና ስራ አስፈፀሚው አቶ ታደሰ ካሳ በሰጠው መግለጫ ፣ ኮርፖሬቱ በአሁኑ ስዓት በርካታ ፋብሪካዎችን በመያዝ በክልሉ ቀዳሚ መሆኑን እንዲሁም ከኢጣሊያ በኢትዮጵያውያን ለደረሰው ግፍ የደም ካሳ ክፍያ ተብሎ የተገነባውን የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለላቸውን ተናግረዋል። በዳሸን ቢራ ግን ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብናል ብለዋል። ...

Read More »

በመላ ሀገሪቱ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ሚኒስቴሩ አስታወቀ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም ከፍተኛ ገንዘብ ወጭ በማድረጉ በዚህ አመት ለመንግስት ተቋማት የስራ ማስኬያጃ የሚውል ከፍተኛ የበጀት መዋዥቅ እንደገጠመው የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ገለፀ፡፡ በዚህም የተነሳ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የመስክ ስራዎች እየተቋረጡ ነው። የሚንስትሩ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ካህሳይ ባህታ ፣ በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በተካሄዱ ህዝባዊ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ የረሃብ አድማ ከጀመሩ አራት የኅሊና እስረኞች መካከል አንደኛው ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገባ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ተይዘው ከነበሩት 10 የኅሊና እስረኞች ውስጥ ስድስቱ ከተፈቱ ሦስት ሳምንት በኋላ ከትናንት በስቲያ ሰኞ የረሃብ አድማ መጀመራቸው ከተዘገበ በሁዋላ፣ አቶ አባስ አብዱላሂ ራሱን በመሳቱ ሆስፒታል ተወስዶ ‹የህክምና ዕርዳታ ተደርጎለት መመለሱን የዓይን እማኞች ገለጸዋል ፡፡ የአቶ አባስን በጠኔ መውደቅ ተከትሎ የታሳሪ ቤተሰቦች በፖሊስ ...

Read More »

የደቡብ ክልል ወጣቶች “የደህዴን ኢህአዴግ አገዛዝ በቃን” ሲሉ ተናገሩ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህዴን የወጣቶች ሊግ ከመላው የደቡብ ክልል ወጣቶችን አበል ከፍሎ በወልቂጤ ከተማ በማሰባሰብ፣ የክልሉን ሰላምና እና እድገት ለመስበክ ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል። “የመንግስቱ ሚዲያዎች ሁሉ ሀሰተኛ ናቸው፣ መንግስትንም ለማጥፋት የኛ እጅ በቻ በቂ ነው” በማለት አንዳንድ ወጣቶች ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ “ደህዴን ምንም አልሰራም፣ ክልሉን ወደ ኃላ ያስቀረ እና በድህነት ...

Read More »

በወረዳ 6 የታዋቂውን ሊቅ የአለቃ አያሌው መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በርካታ ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ ተጀመረ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 6 ቀበሌ 11የቤት ቁጥር 207 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኘው የታዋቂው የሃይማኖት አባት አለቃ አያሌው ታምሩ መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታውቋል። በጽኑ ታመው አልጋ የያዙት ባለቤታቸው እና ልጆቻቸውን ቤታቸውን በሁለት ቀናት ውስጥ እንዲያፈርሱ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። ከ50 ዓመታት በላይ ጎጆ ቀልሰው የኖሩበትን የሊቀ ሊቃውንት ...

Read More »

121ኛው የአድዋ ድል በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) ኢትዮጵያውያን ከ100 አመት በፊት ወራሪው የኢጣሊያ ጦርን በአድዋ ድል ያደረጉት 121ኛው የአድዋ ድል በአል ሃሙስ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። የበአሉ አከባበር በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ አባት አርበኞች፣ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት መከበሩ ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ አመታዊ በዓል አከባበር ላይ የታደሙ ...

Read More »

13 የቤኒሻንጉል ነጻነት ንቅናቄ (ቤህነን) ታጣቂዎች መገደላቸውን መንገስት ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) በመገንባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ላይ ጥቃትን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ የቤኒሻንጉል ነጻነት ንቅናቄ (ቤህነን) 13 ታጣቂዎች መገደላቸውን መንግስት ገለጸ። በተወስደባቸው ዕርምጃ ከተገደሉት ታጣቂዎች በተጨማሪ ሰባቱ ወደ ጎረቤት ሱዳን ከሸሹ በኋላ ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውንና የንቅናቄው አባላት መነሻቸውን ከኤርትራ እንዳደረጉ የመንግስት ቃል አቀባይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘዲግ አብርሃን ዋቢ በማድረግ አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል። ይሁንና የኤርትራ መንግስት ጥቃት ...

Read More »

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ያደረጉት ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ሲል የሱዳን አማጺ ቡድን አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) ኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን መንግስት ሰሞኑን ያደረጉት ሰምምነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል በሪክ ማቻር የሚመራው አማጺ ቡድን ውስጥ በአባልነት የሚገኝ አንድ አንጃ ገለጸ። የኑዌር ጎሳዎች በአብዛኛው እንደሚወክል የሚነገርለት የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ንቅናቄ ተቃውሞ አንጃ በደቡብ ሱዳን ሰላም በሌለበት ሁኔታ ሁለቱ ሃገራት የደረሱት ስምምነት ተፈጻሚ እንደማይሆን የአንጃው አመራሮች መግለጻቸውን ራዲዮ ታማዙጂ የተሰኘ ጣቢያ ዘግቧል። የአንጃው ምክትል ...

Read More »

በህገወጥ መንገድ ወደ ሞዛምቢክ ገብተዋል የተባሉ 36 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) በህገወጥ መንገድ ወደ ሞዛምቢክ ገብተዋል የተባሉ 36 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን መምሪያ አስታወቀ። ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ግዛት በሆነው የናምፑላ አስተዳደር በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ በሰው ጥቆማ ሊያዙ መቻላቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የግዛቲቱ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ዘካሪያስ ናኩቴ የኢሚግሬሽን የጸጥታ አባላትና የግዛቲቱ ፖሊስ በጋራ በመኖሪያ ቤቱ ላይ ባካሄዱት ከበባ ኢትዮጵያውያኑ በሰላም ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የከፋ የምግብ እጥረት ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል የምግብ እርዳታ ለማግኘት በ24 መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ተሰባስበው በሚገኙ ሰዎች መካከል እየደረሰ ያለው የከፋ የምግብ እጥረትና ጉዳት በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው አህዝ በሶስት እጅ መብለጡ ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። በክልሉ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ የፌዴራልና የክልሉ መንግስት ከ20ሺ የሚበልጡ ነዋሪዎች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲሰባሰቡ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና እርዳታ ...

Read More »