Author Archives: Central

በየካቲት ወር የዋጋ ግሽበት ሰባት በመቶ መድረሱ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የተከሰተን የምግብ ዋጋ ንረት ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በየካቲት ወር በአንድ በመቶ በማደግ ሰባት በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ። በየካቲት ወር ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት 7.8 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ ቁጥሩ ካለፈው ወር የ2.8 በመቶ አካባቢ ጭማሪ ማሳየትን ሮይተርስ የኤጀንሲውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ከጫፍ መደረሱን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) በረሃብ አደጋ አጋጥሟት ባለው ደቡብ ሱዳን የዘር ማጥፋት ድርጊት ከጫፍ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረቡዕ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት አስታወቀ። በሃገሪቱ ባለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ለሰባት ወር የፈጅት ጥናት ማካሄዱን የገለጸው ድርጅቱ፣ በደቡብ ሱዳን በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውን ግጭት ምክንያት በማድረግ በፕሬዚደንት ሳልባኪር የሚመራው መንግስት በማንነት ላይ የሚፈጸም ጥቃት እየወሰደ እንደሚገኝ አጋልጧል። የሃገሪቱ ብሄራዊ ...

Read More »

በአማራ ከልል የተለያዩ ወረዳዎች መምህራን የስራ ማቆም አድማ ጀመሩ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ ወረዳዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በምእራብ ጎጃም ዞን በአዴት፣ በሰቀላ ደግሞ መምህራን አድማ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የተወሰኑ መምህራን ታስረዋለ። በምሰራቅ ጎጃም ደብረወርቅ ፣ ሸበል በረንታ ፣ ቡብኝ፣ በቻግኒ እንዲሁም በድቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ የአፈር ዋናት ሁለተኛ ደረጃ መምሀራን የስራ ማቆም አድማው መንሳኤ ለሌሎች የመንግስት ሰራተኞቸ የደሞዝ ...

Read More »

በረሃብ የተጠቁ ኢትዮጰያውያን ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ተመድ አስታወቀ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተመድ የሰባዊ ድጋፍ አስተባባሪ እንዳስታወቀው 6 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በረሃብ ቢጠቁም፣ ምግብ፣ ወሃና መድሃኒት ለማቅረብ አልተቻለም። አለማቀፉ ማህበረሰብ፣ ህዝቡን ለመደገፍ የሚያስፈልገውን 900 ሚሊዮን ዶላር በፍጥነት ካለገስ፣ ከፍተኛ ሰባዊ ቀውስ ይከሰታል ሲል አስጠንቅቋል። በየቀኑ በርካታ ዜጎች እየተጎዱ መሆኑን የጠቀሰው ተመድ፣ በተለይ ልጆችን በፍጥነት መታደግ ካልተቻለ በሁዋላ ላይ ጉዳቱን ለመቀነስ ከባድ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የአዮዲን እጥረት ተከሰተ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዮዲን እጥረት በዋንኛነት የእንቅርት በሽታ የሚያስከትል ከመሆኑም በተጨማሪ የህጻናት የአእምሮ ዕድገት በመጉዳት በዘላቂነት የአምራች ዜጋ እጦትን ያስከትላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ጨው የሚመረትባቸው አካባቢዎች አፋር ክልል ዶቢ እና አፍዴራ ሐይቆች እንዲሁም በሶማሌ ክልል ኢራካል ሐይቆች በሚገኝ ምርት ነው፡፡ ከሚኒስቴሩ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ወር ጊዜውስጥ ብቻ 300 ሺ ኩንታል ...

Read More »

የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ስራውን እንዲያቆም ተጠየቀ፡፡

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተቋራጮች እንደተናገሩት ስራቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ሰርተው ለማጠናቀቅ እንዳይችሉ ችግር እየፈጠረባቸው ያለው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት በመሆኑ ስራውን እንዲያቆም ጠይቀዋል፡፡ ሰሞኑን በክልሉ የግንባታ ባለሙያዎችና በጤና ጥበቃ ቢሮ መካከል በተደረገው የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተናገሩት የተቋራጭ ድርጅት ተወካዮች፣ የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ባለሙያዎች ...

Read More »

በነርሶቸ እንዘላልነት የአንድ ወላድ ህይወት አለፈ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቀጨኔ ልዩ ስሙ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ህዳሴ በሚባል ጤና ጣቢያ ውስጥ ነርሶች ለወላዷ የምጥ መርፌ ከወጉዋት በሁዋላ ፣ ከወላዱዋ ርቀው ሲጫውቱ ቆይተው ሲመለሱ ህይውቱዋ አልፎ ያገኙዋት ሲሆን፣ በዚህ ድርጊት የተብሳጩት የአካባቢው ነዋሪዎቸ የጤና ጣቢያውን በሮችና መሰኮቶች በድንጋይ ሰባብረዋል። ወላዱዋ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ እንደገባችና ምሽት ...

Read More »

የትራምፕ አስተዳደር  ስደተኞችን በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተላለፈው ውሳኔ በድጋሚ ከህግ አካላት ዘንድ ተቃወሞ ገጠመው

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሰኞ ስደተኞችን በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተላለፈውን ውሳኔ በድጋሚ ከህግ አካላት ዘንድ ተቃወሞ ገጠመው። ፕሬዚደንቱ በአዲስ መልክ ያወጡትን ውሳኔ የተቃወሞ አካላት ዕርምጃው አሁንም ቢሆን የሙስሊም ሃገራትን ሆን ብሎ ያነጣጠረ ነው ሲሉ ቅሬታን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በዚሁ አዲስ ውሳኔ መሰረት ስድስት ሃገራት ለሶስት ወር ተግባራዊ የሚሆን የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ...

Read More »

ለአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ተጋልጠው የሚገኙ ሰዎች በገንዘብ እጥረት የተነሳ የምግብ አቅርቦት እንደማያገኙ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ተጋልጠው የሚገኙ በሚለዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በገንዘብ እጥረት የተነሳ በቂ የምግብ አቅርቦት አለማግኘታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ለሃገሪቱ የሚያስፈልገው አለም አቀፍ ድጋፍ በወቅቱ ባለመገኘቱ ምክንያት በደቡብ ክልል የህክምና ባለሙያዎችን ማሰማራት አልተቻለም ያለው ድርጅቱ የድርቁ አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ወር በፊት ድርቁን ለመቋቋም ...

Read More »

በናይጀሪያ አቡጃ የሚገኝ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲዘጋ ለጊዜው ቢወሰንም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአማራጭነት ተጠቃሚ ነው ተባለ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2009) በናይጀሪያ አቡጃ ከተማ የሚገኝ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ለጊዜው እንዲዘጋ ቢወሰንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአማራጭነት የቀረበን አየር ማረሪያ ለመጠቀም ብቸኛ አየር መንገድ ሆኖ መቅረቡን የናይጀሪያ የአቪየሽን ባለስልጣናት አስታወቁ። በአቡጃ ከተማ የሚገኘው የናምዲ አዚክዌ አየር ማረፊያ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ወደ ከተማዋ አለም አቀፍ የበረራ አገልግሎትን የሚሰጡ 25 አየር መንገዶች በአማራጭነት የቀረበውን አየር ማረፊያ በመቃወም በረራ ...

Read More »