Author Archives: Central

በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የተቀሰቀሰውን የመምህራንን ተቃውሞ እንደሚደግፍ መቀመጫውን በውጭ አገር ያደረገ የኢትዮጵያ መምራን ማህበር አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 30 ፥ 2009) መንግስት ሰሞኑን ያደረገው የደሞዝ ማስተካከያ መምህራንን ያካተተ አይደለም በማለት በምስራቅ ጎጃምና በወሎ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ መምህራት የስራ ማቆም አድማን እንደሚደግፍ መቀመጫውን በውጭ ያደረገው የኢትዮጵያ መምራን ማህበር ለኢሳት አስታወቀ። መምህራኑ ከሁለት ቀን በፊት የስራ ማቆም አድማቸውን በመጀመር ጥያቄን ማቅረብ ቢጀምሩም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ምላሽ ሊሰጧቸው እንዳልቻሉ የማህበሩ ሰብሳቢ ኮሚቴል ሊ/መንበር አቶ ካሳሁን ከበደ ገልጸዋል። ...

Read More »

በኦጋዴን በ72 ሰዓታት ውስጥ ከ300 በላይ ሰዎች ሞቱ

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ውስጥ በተቀሰቀሰ የኮሌራ ወረሽኝ በ72 ሰዓታት ውስጥ ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር እንዳለው ሰዎቹ እስካሁን የመድሃኒት እና የሕክምና እርዳታ አልተደረገላቸውም። ወደ አካቢዎቹ የተሰማራ ድንገተኛ አደጋ መከላከያ የሕክምና ቡድን ባለመኖሩም በበሽታው የሚሞቱ ዜጎች ቁጥራቸው ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። በኦጋዴን በሚገኙ በርካታ ከተሞች እና ...

Read More »

በሰሜን ወሎና በደቡብ ጎንደር መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ ።በተቃውሞው ምክንያት መምህራን እየታሰሩ ነው።

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ ኢሳት ምንጮች መረጃ የሳንቃ ሁለተኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ መምህራን ፣የሀራ ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣የአንፈሁም የስሪንቃ ሁለተኛ ደረጀሰ መምህራን እና የጉባላፍቶ ወረዳ የገጠር መምህራን ስራ አቁመው ውለዋል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሳይማሩ ተመልሰዋል። በተለይ የሳንቃ መንህራን በፖሊስ ተከበው ከግቢው እንዳይወጡ ማስፈራራት ቢደረግባቸውም፤ አንድም መምህር ገብቶ ሊያስተምር አልቻለም። በተመሣሳይ በደቡብ ...

Read More »

የኢህአዴግ ምክር ቤት የሁለት ቀናት ውይይት በሃሰት ሪፖረት ተጠቀቀ፡፡

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ፣ ህዝቡ በአስቸኳይ አዋጁ ስለተረጋጋ ‹‹እየታደሰን እንሰራለን ፤ እየሰራን እንታደሳለን›› የሚል መርህ ይዞ እንደሚቀጥል ገለጸ።የድርጅቱ ምክር ቤት ባወጣው ሪፖርት፣ ተሃድሶው ስኬታማ ነው ቢልም ማዕከላዊ ኮሚቴው ባቀረበው ሃሳብ መሰረት የአስቸኳይ አዋጁ እንደማይነሳ በውይይቱ መግባበት ላይ ደርሷል፡፡ ኢሃዴግ እንደ ጤነኛ ደርጅት እራሱን እያወደሰ በተነጋገረበት በዚህ መድረክ፣ እኛ ለፖለቲካውትኩረት በሰጠነው ቁጥር የበለጠ ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት ወደ ፖለቲካና የህሊና እስረኞችን አማላጅ መላኩ ተነገረ

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ወደ እስር ቤቶች ሽማግሌዎችን የላከው በቅንጅት ጊዜ እንዳደረገው የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይቅርታ ጠይቀው እንዲፈቱ በሚል ነው። በዚህም መሰረት ኢህ አዴግ የተመረጡት ሽማግሌዎች ወደ እስር ቤት በማምራት የአንድነት ፓርቲ አመራሩን አቶ አንዱአለምን አራጌን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና ሌለኛውን የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ ናትናኤል መኮንን በጉዳዩ ዙሪያ እንዳነጋገሯቸው የእስር ቤት ...

Read More »

የአማራ ክልል ጋዜጠኞች በአገዛዙ ላይ ተቃወሞአቸውን አሰሙ

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ካቢኔ አወቃቀር በዘር ማንዘር የተዋሀደ እና እውቀትን እና ትምህርትን ያላገናዘበ ባለመሆኑ ክልላችን ላይ ችግር ደቅኗል ያሉት ጋዜጠኞች፣ ብአዴንን ለአማራ ህዝብ ያልሆነ አሻንጉሊት ነው ብለውታል፡፡ ጋዜጠኞች ከየካቲት 24 2009 ጀምሮ ለመጭው ቀናት በሚቀጥለው ውይይታቸው እየተካሄደ ያለው “ጥልቅ ተሃድሶ ሳይሆን ጠቅ ትሃድሶ ነው” ብለውታል፡፡ “እንደ አማራ የሚያስብ ድርጅት በሌለበት አማራ በተገለለበት ...

Read More »

የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ ባለመደረጉ መምህራንና ሰራተኞች ተቃውሞ አቀረቡ፥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመምህራን አድማ ተጀምሯል።

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) መምህራንን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ተደርጓል የተባለውን የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ አልተደረገልንም ሲሉ ተቃውሞ አቀረቡ። በአንዳንድ አካባቢዎች የመምህራን አድማ ተጀምሯል። በተለይ በጎጃምና በጎንደር አንዳንድ መምህራን አድማ አስነስታችኋል በሚል እየታሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። አድማው ከደሞዝ ማስተካከያ የተያያዘ ነው ቢባልም፣ አጠቃላይ የነጻነት ጥያቄን ያዘለ መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በጎጃም በተለያዩ ወረዳዎች ማለትም ዱርቤቴ፣ ቁንዝላ፣ ይስማላ፣ እና አሹዳ ...

Read More »

በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በዘለቀው ግጭት ሚና የነበራቸው ሰዎች ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከአራት ወር በላይ በክልሉና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች የዘለቀው ግጭት መፍትሄ እንዲያገኝ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ። በሁለቱ ክልሎች የድንበር አካባቢ ያለው ግጭት ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑን ያወሳው ምክር ቤቱ፣ ከሁለቱም ክልሎች ችግሮቹ ተባብሰው እንዲቀጥሉ ሚና የነበራቸው የመንግስት መዋቅር አካላት ለህግ ኣንዲቀርቡም ጥሪን አቅርቧል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ...

Read More »

ሂልተን ሆቴል በጨረታ እንዲሸጥ ተወሰነ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አለም አቀፍ ሆቴል የሆነውን ሂልተን አዲስ ሲያስተዳድር የቆየው መንግስት ሆቴሉ በጨረታ እንዲሸጥ ወሰነ። በአጼ ሃይለ-ስላሴ መንግስት ዘመን ስራውን የጀመረው ሆቴል ለጨረታ እንዲቀርብ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ከሂልተን አዲስ የቦርድ ዳይሬክተሮች ጋር ሰሞኑን ምክክር ማካሄዱንና ለጨረታው ሽያጭ ዝግጅት እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠቱን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1969 አም ስራውን የጀመረውን ይህንኑ ሆቴል ለማስተዳደር መንግስት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የነበሩ ወደ 9 ሺ የሚጠጉ ቤተ-እስራዔላውያን ወደ እስራዔል እንዲጓጓዙ ተጠየቀ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2009) የእስራዔል የፓርላማ አባላት የሃገሪቱ መንግስት በጎንደርና አዲስ አበባ ከተሞች የሚገኙ ወደ ዘጠኝ ሺ አካባቢ ቤተ-እስራዔላዊያን በአስቸኳይ ወደ እስራዔል እንዲጓጓዝ አሳሰቡ። ሰሞኑን በኢትዮጵያ በመገኘት የቤተ-እስራዔላውያን ሁኔታ የተመለከቱ አራት የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት በጎንደርና አዲስ አበባ ከተሞች ያዩት ሁኔታ እጅግ አስደንጋጭ መሆኑን እንደገለጹ ጀሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ የፓርላማ አባላቱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በእስራዔል ...

Read More »