መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሎምበርግ ባወጣው ዘገባ የፈረንሳይ የልማት ተራድኦ እኤአ በ2011 በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በቆሻሻ ናዳ ያለቁበትን ረጲ የቆሻሻ መድፊያ ወይም በተለምዶ ቆሸን ለመዝጋት ለአዲስ አበባ መስተዳደር 34 ሚሊዮን 600 ሺ ዩሮ መስጠቱን ገልጿል። ገንዘቡ የቆሻሻ መድፊያውን ለመዝጋትና ከአካባቢው ለሚነሱ ዜጎች መልሶ መቋቋሚያ ታስቦ የተለገሰ ነበር። በቆሸ የደረሰው አደጋ ፖለቲካዊ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ የፈረንሳይ ...
Read More »Author Archives: Central
ኩማ ደመቅሳ በጀርመን የሚኖሩ የሃይማኖት አባቶች የዲያስፖራውን ተጽእኖ የሚቀንስ ስራ እንዲሰሩ ጠየቁ
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ባለፈው የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በጀርመን የሚኖሩ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከገዢው ፓርቲ ጋር ቀረቤታ ያላቸውን ነጋዴዎችና ግለሰቦች በመሰብሰብና ከፍ ያለ ግብዣ በማድረግ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ ላይ የሚያደርሱትን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችል ስብከት እና ሌሎችንም ስራዎች እንዲሰሩ አዘዋል። ቅዳሜ ቀን ለሃይማኖት አባቶች ብቻ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ...
Read More »በፊንላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ለቴንፐር ኮሌጅ የተቃውሞ ደብዳቤ ጻፉ
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፊላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የቴንፐር ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ለአቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሊሰጥ የታሰበውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሽልማት በማውገዝ ለዩንቨርሲቲው አስተዳደር ደብዳቤ አስገብቷል። በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን አፈና፣ ድግያ፣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከሚዘውረው የህወሃት ኢህአዴግ ፓርቲ ባለስልጣናት ውስጥ በዋናነት በጠቅላይ ሚንስትርነት የሚመሩት አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝን በቀጣዩ ግንቦት ወር 2017 እ.ኤ.አ. ለመሸለም ማቀዱ ...
Read More »የእንግሊዝ መንግስት ለአንባገነን አገራት መሳሪያ መሸጡን እንዲያቆም ሲሉ የአገሪቱ ዜጎች ጠየቁ
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእንግሊዝ መንግስት ዜጎቻቸውን ለሚጨቁኑ፣ሰብዓዊ መብቶችን ለሚጥሱ አንባገነን መንግስታት መሳሪያ መሸጡን እንዲያቆም ሲሉ ”የመሳሪያ ሽያጩ ፍትሃዊ ይሁን’ የሚል መፈክር ያነገቡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ተይንተ ሕዝብ አካሄደዋል። ጸረ ጦርነት ባነሮችን የያዙት ሰልፈኞች የእንግሊዝ መንግስት አፋኝ ለሆኑት አገራት ኢትዮጵያ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ባሕሬን እና ቬንዙዌላን ለመሳሳሉ አንባገነኖች መሳሪያ በመሸጥ ሰላማዊ ዜጎችን ከማስጨፍጨፍ ሚናውን እንዲታቀም ሲሉ ጠይቀዋል። ...
Read More »በእስራዔል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንዲራ ያወረደው ማስተዋል ጥላሁን በነጻ ተለቀቀ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በእስራዔል ተላቪቭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመግባት ባንዲራ ያወረደውና ምልክቱን ያቃጠለው ኢትዮጵያዊ በፍድ ቤት በነጻ ተለቀቀ። ድርጊቱ ሲፈጸም በኢትዮጵያ የነበሩት አምባሳደር ጸጋዬ በርሄ የደህንነት ስጋት አለብኝ በማለት ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። ሆኖም ተከሳሽ ኢትዮጵያዊ ከኤምባሲው 500 ሜትር እንዲርቅ ውሳኔ ተላልፎበታል። ሃሙስ መጋቢት 14, 2009 በእስራዔል ቴላቪቭ ወደ ሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመግባት ባንዲራውን በማወረድ የኮከብ ...
Read More »መንግስት ከቆሼ መደርመስ ለተረፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምንም ድጋፍ አላደረገም ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መደርመስ የተረፉት ከ325 በላይ ነዋሪዎች በመንግስት በኩል የተደረገላቸው ምንም አይነት ድጋፍ እንደሌለ ገለጹ። በቆሻሻ ክምር ናዳው እናቱን፣ አባቱን፣ እህቶቹን፣ አያቱን ጨምሮ 7 ቤተሰቦቹን ያጣው ወጣት አስረስ እውነቱ ለኢሳት እንደገለጸው ከአደጋው የተረፉትና በአካባቢው ያሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ በመንግስት ታዘዋል። ይህም ሆኖ አካባቢውን ሲለቁ መንግስት መጠለያም ሆነ መቋቋሚያ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ...
Read More »የዋልድባን ገዳም መፍረስ የተቃወሙት መነኩሴ በመንግስት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተነገረ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በልማት ሰበብ የዋልድባ ገዳም አይፈርስ በሚል ሲቃወሙና ድርጊቱን በመገናኛ ብዙሃን ያጋለጡት የዋልድባው መነኩሴ አባ ገብረየሱስ በመንግስት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተነገረ። የዋልድባው መነኩሴ የመንግስት ስራ በማጋለጣቸው ለረጅም አመታት ከኖሩበት ገዳም እንዲወጡ ተደርጉ ከአምስት አመታት በላይ መቆሚያና መቀመጫ አጥተው ከገዳም ገዳም ሲዞሩ ቆየተዋል አሁን ደግሞ ባለፈው ጥር 2009 አም ሱባዔ ከያዙበት ጎንደር ከሚገኝ አንድ ገዳም በመንግስት ሃይሎች ...
Read More »የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አያያዛቸውን የሚያሳይ መረጃ እንዲያቀርቡ ታዘዙ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ያሉ ሁሉም የግል ባንኮች ካለፈው አመት ሃምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ አሰጣጣቸውን የሚያሳይ መረጃ እንዲያቀርቡ አዘዘ። ሃገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባንኮች የሚያደርጉትን የውጭ ምንዛሪ አሰጣት እና አያያዝ በተመለከተ ሪፖርት እንዲያቀርቡ አዲስ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንኑ መመሪያ በማድረግ ብሄራዊ ባንክ ሁሉም የግል ባንኮች ከሃምሌ ወር ጀምሮ ያካሄዱትን ...
Read More »በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ 700ሺ ህጻናትን ህይወት ሊያሳጣ እንደሚችል ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት እየተባባሰ ባለው የድርቅ አደጋ ወደ 700ሺ የሚጠጉ ህጻናት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችል ወርልድ ቪዥን የተሰኘ የእርዳታ ድርጅት ሰኞ አሳሰበ። በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ የድርቁ አደጋ ወደ ረሃብ በመለወጡ ምክንያት ሰዎች በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው የሰብዓዊ ተቋሙ በኢትዮጵያና ኬንያ ድርቁ እየከፋ መምጣቱን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሶማሌ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ስድስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸው ስጋት እንዳሳደረበት ተመድ ገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በደቡብ ሱዳን ስድስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸው ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ አስታወቀ። የእርዳታ ሰራተኞች የያዘ ተሽከርካሪ ከመዲናይቱ ጁባ ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ወደ ምትገኘው የፒቦር ከተማ በማቅናት ላይ እንዳሉ የደፈጣ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ተወካይ የሆኑት ኡጊን አውሶ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን ከረሃብ ጋር በተገናኘ ሰዎች መሞት እንደጀመሩ ...
Read More »