መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ክልል አቀፍ የእምቦጭ አረም አስወጋጅ ዩኒት አስተባባሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ወ/ሮ በፍታ ጥሩነህ ሰሞኑን ለመንግስት ሚዲያዎች እንደተናገሩት የአረሙ ስጋት በጣም ሠፊ በመሆኑ ተስፋ የተጣለበት ይህ ትልቅ ግድብ በእንቦጭ አረም ሊጠቃ እንደሚችል ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡ ዩኒት አስተባባሪዋ ስለመጤ አረሙ ሲያስረዱ የውሀን ተፈጥሯዊትነት በማዛባት እንዲደርቅ የሚያደርገው ...
Read More »Author Archives: Central
አንድ የአሜሪካ የፓርላማ አባል ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ጠየቁ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሎራዶ 6th ዲስትሪክት ተወካይ የሆኑት ማይክ ኮፍማን ለአገራቸው ምክር ቤት የውጭ እርዳታ አስተባባሪ ክፍል በጻፉት ደብዳቤ የኢህአዴግ መንግስት የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እስኪቆም ድረስ በመጪው አመት ሊሰጥ የታሰበው የእርዳታ ገንዘብ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል። “ዛሬ ይህንን ደብዳቤ እንድጽፍ ያደረገኝ እኔን የመረጡኝ አብዛኛዎቹ ኢትዮ-አሜሪካዊያንን ባቀረቡልኝ ጥያቄ መሰረት ነው። “ ያሉት የፓርላማ አባሉ፣ በስልጣን ላይ ...
Read More »በድንበር አካባቢ ያለው ጸጥታ አለመረጋጋቱን ሚኒስትሩ አስታወቁ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሚቀጥሉት አራት ወራት እንዲራዘም ለተወካዮች ምክርቤት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀዳላቸው የወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) ዋና ጸሃፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገው ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ጸረ ሰላም ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ በአማራ ክልል በትግራይና አማራ ፣ በኦሮምያ እና በሶማሊ እንዲሁም በቤንሻንጉልና በአማራ ድንበሮች አካባቢ ጦርነቶች እየተደረጉ ...
Read More »ባህርዳር ውስጥ በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ላይ አንድን ወጣት ገጭቶ የገደለው ባለስልጣን ከተለቀቀ በሁዋላ መልሶ ታሰረ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃይለኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሲያሸከረክር የነበረው የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ ተሻገር በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ወይም “ዜብራ ክሮስ” ላይ ጋሻው የተባለውን ወጣት ገጭቶ ከገደለው በሁዋላ፣ በእለቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወሰድም በማግስቱ የተለቀቀ ሲሆን፣ ኢሳት ዜናውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ግን ተመልሶ እንዲታሰር መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል። ድርጊቱ የከተማው ህዝብ ...
Read More »ከውጭ አገራት በተለያዩ መንገዶች የገባ 50 ቢሊዮን ብር ባንክ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የውጭ አገር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለኢትዮጵያውያን ለልማት እያሉ በብሄራዊ ባንክ በኩል ከሚያስተላልፉት ገንዘብ ውስጥ 50 ቢሊዮን ብር ጥቅም ላይ ሳይውል ተቀምጦ እንደሚገኝ የብሄራዊ ባንክ ምንጮቻችን ገልጸዋል። የውጭ አገር ዜጎች ለልማት እያሉ የሚያስገቡት ገንዘብ፣ በድርጅቶቹ ደካማ እቅድ አፈጻጸም ወይም በሌሎች ምክንያቶች ጥቅም ላይ ሳይውል ተከማችቶ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች፣ የባንኩ ሃላፊዎችና ...
Read More »በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ወርልድ ቪዥን ገለጸ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አለመጣሉን ተከትሎ በተፈጠረ ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን ወርልድ ቪዥን አስታውቋል። የአየር ትንበያዎች በመጪዎቹ ወራቶች ካሁኑ በከፋ ሁኔታ የዝናብ እጥረቱ ተባባሶ እንደሚቀጥልና ከቀድሞው 45 በመቶ ከመቶ በታች የሆነ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል ያመለክታሉ። ከምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ...
Read More »ረሃብና ጦርነትን የሸሹ በሽዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያዊያን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየፈለሱ ነው።
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግር በመጓዝ ሕጻናትን የያዙ እናቶች፣ ነፍሰጡሮች እና አቅመ ደካማ ሶማሊያዊያን አገራቸውን እና መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኘው ዳሎ አዶ መጠለያ ጣቢያ እየጎረፉ ነው። ሶማሊያውያን በርሃብ የተጎዱ ልጆቻቸውን ማጥባት የተሳናቸው ሲሆን፣ አገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት ረሃብ እና ጦርነትን ሸሽተው መሆኑን ተናግረዋል።
Read More »በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአራት ወር እንዲራዘም ተደረገ
ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ሊውል ባለመቻሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ። የአዋጁን አፈጻጸም ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሃሙስ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመጠቀም የሚፈልጉ እና ጸረ-ሰላም ሲል የገለጻቸው አካላት እየተንቀሳቀሱ ነው ሲል አስታውቋል። በበራሪ ወረቀቶች የተለያዩ ፅሁፎች አሁንም ድረስ በመበተን ላይ እንደሚገኙ ኮማንድ ...
Read More »ከቆሼ አደጋ የተረፉ ነዋሪዎች ህጋዊ አይደላችሁም ተብለው ከጊዜያዊ መጠለያ እንዲወጡ መደረጋቸውን አስታወቁ
ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ አደጋ የተረፉና በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ የተደረጉ ነዋሪዎች ህጋዊ ነዋሪዎች አይደላችሁም ተብለው ከመጠለያ እንዲወጡ መደረጋቸውን አስታወቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በጊዜያዊ መጠለያ እንዲገቡ የተደርጉ ሰዎች በአደጋው ተጎጂ እንደነበሩና እንዳልነበሩ የመለየት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ሃሙስ ገልጿል። ይሁንና በጊዜያዊ መጠለያው የሚገኙ በርካታ ሰዎች ከአደጋው ተርፈው በመጠለያ እንዲገቡ ቢደረግም ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያራዘመው ህዝባዊ ተቃውሞው ሊቀጣጠል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2009) መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም የወሰነው ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበትና ተግባራዊ የተደረገ ማሻሻያ ባለመኖሩ እንደሆነ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘግቧል። የዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑትና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊትና በአዋጁ መውጣት ወቅት ለእስር ተዳርገው የነበራት አቶ ስዩም ተሾመ ህዝቡ ተቃውሞን የሚገልፅበት መንገድ ባለመኖሩ አዋጅ ከተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀጥል እንደሚችል ከጋዜጣው ...
Read More »