Author Archives: Central

በደቡብ ክልል የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ወረቀቶችን በትነው ማደራቸውን አስታወቁ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ለኢሳት በላኩት መረጃ በሐዋሳ ፣ በወላይታ ከተማ ፣ በአርባምንጭ ፣ በኮንሶ ፣ በጅንካ እንዲሁም በአቶ ኃ/ማሪያም ደሰላኝ የትውልድ አከባቢ በሆነው አረካ አካባቢ “ ከአሁን በሁዋላ በወያኔ መታለል ይቁም፣ የታጋይ አርበኞቻችን ደም በከንቱ እንደፈሰሰ አይቀርም፣ በወያኔ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝቡን መብት ለማፈን እና አርበኞችን ትግል ለማደናቀፍ ያለመ ቢሆንም የአርበኞች ...

Read More »

መሬታቸውን የተነጠቁ አርሶአደሮች ካሳ ሳይከፈላቸው ለአመታት መቆየታቸውን ገለጹ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዋሽ ሐራ ገበያ – መቀሌ እየተገነባ ካለው የባቡር መስመር ጋር ተያይዞ አርሶአደሮች ያላ አንዳች የካሳ ክፍያ ለዓመታት መቆየታቸውን ተናገሩ፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳን አቋርጦ ወደ መቀሌ ከተማ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመር በርካታ አርሶአደሮችን ለችግር ዳርጐ መቆየቱን የቀበሌ ነዋሪዎች ለመንግስት ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በባቡር ሃዲዱ ግንባታ ምክንያት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ለሁለት ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳደር ተቃውሞ የተነሳበትን የመንገድ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ገለጸ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ታናሽ ወንድም አቶ ገነቱ ደሳለኝ የሚመራው የአዲስአበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አወዛጋቢውን የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ በአዲሱ ደንብ በሚያዝ ሪከርድ መሠረት በተደጋጋሚ አጥፍተዋል የተባሉ አሽከርካሪዎች ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡ ኤጀንሲው ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን በአዲስዘመን ጋዜጣ መጋቢት 28 ቀን ...

Read More »

ወደ ማላዊ የገቡ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል የተባሉ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ የድንበር ፖሊሶች መያዛቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ለጊዜው መነሻቸው ከየት እንደሆነ ያልታወቀው ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በመኪና ተጭነው በሕገወጥ መንገድ ወደ ካሮንጋ ግዛት ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ሃምሳ ስድስቱም ኢትዮዮጵያዊያን ስደተኞች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና የጭነት መኪናው አሽከርካሪ መኪናውን በመተው ከአካባቢው መሰወረኑን ፓሊስ ...

Read More »

አሜሪካ የሶሪያው መሪ ባሽር አልአሳድ ከስልጣን የሚወገዱበት አማራጭ ይፋ አደረገች

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) አሜሪካ የሶሪያው ፕሬዚደንት ባሽር አልአሳድ ከስልጣን የሚወገዱበት ሁኔታ መታየት ወዳለበት አማራጭ መድረሱን ይፋ አድረገች። በሶሪያ መንግስት ከቀናት  በፊት በንጹሃን ሰዎች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል በተባለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ግድያ ተቃውሞዋን ስታሰማ የሰነበተችው አሜሪካ ፕሬዚደንት አሳድ ስልጣናቸው በሃይል የሚያከትምበት ጊዜ መቃረቡን ለመጀመሪያ ጊዜ ፍንጭ መስጠቷን መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ወታደራዊ ባለስልጣናት በበኩላቸው ...

Read More »

አሜሪካ በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት ሰነዘረች

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) የሶሪያ መንግስት ከቀናት በፊት በንጹሃን የሃገሪቱ ዜጎች ላይ ፈጽሞታል የተባለውን የኬሚካል የጦር መሳሪያ ዕርምጃ ተከትሎ አሜሪካ በተመረጡ የሃገሪቱ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት መውሰዷን ሃሙስ ይፋ አደረገች። የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት ከምስራቅ የሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከወታደራዊ መርከቦች የተወሰደው የሚሳይል ጥቃት በቅርቡ በሰሜናዊ ምዕራብ የሶሪያ ግዛት ጥቃት ለመፈጸም አገልግሎት የሰጠ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ዋነኛ ኢላማ እንደነበር ገልጸዋል። ...

Read More »

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሱዳን ድንበር ዙሪያ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በምትዋሰነት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድንበር ዙሪያ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይል በማሰማራት ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆኗን የመከላከያ ሰራዊት አርብ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ በአካባቢው ወታዳራዊ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን ሲገልጽ መቆየቱም ይታወሳል። ባለፈው ወር መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው የአባይ ግድብ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 13 ታጣቂዎች ገደልኩ ሲል መግለፁ ይታወሳል። ይህንኑ ...

Read More »

በበለጸጉ አገራት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የነበረው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ውድቅ ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) የአለም አቀፍ አረንጓዴ ከባቢ (ግሪን ክላይሜት) በጀት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ባሰበው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ላይ የበለጸጉ ሃገራት  ያቀረቡትን ተቃውሞ ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሊለቀቅ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ ውድቅ ተደረገ። ከ20 የሚበልጡ የተቋሙ የቦርድ አባላት ሃሙስ ለሁለተኛ ቀን በቀጠሉት ውይይት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በነበረው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ላይ ሰፊ ልዩነት ማንጸባረቃቸውን ሮይተርስ ከደቡብ ኮሪያ ዘግቧል። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ስዊዘርላድ፣ ...

Read More »

በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ነጻ የተሰናበቱት ሁለት ጦማሪያን በአዲስ ወንጀል ክስ እንዲከሰሱ የተላለፈው ውሳኔ ውድቅ እንዲደረግ ሲፒጄ ጠየቀ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ነጻ የተሰናበቱት ሁለት ጦማሪያን በአዲስ ወንጀል ክስ እንዲከሰሱ ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ እንዲደረግ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ። የታችኛው ፍርድ ቤት ባለፈው አመት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ጦማሪያን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ይሁንና ከሳሽ አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ...

Read More »

ታዋቂው አርበኛ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ከጠላት የጣሊያን ወራሪ ጦር የተከላከሉት ታዋቂው አርበኛ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ከ15 አመት ለጋ እድሚያቸው ጀምሮ ጫካ በመግባት የጣሊያንን ጦር ያርበደበዱት ጀግናው ሌተናል ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ በአጼ ሃይለ-ስላሴ ዘመን የጦር አዛዥ እስከመሆን ደርሰዋል። በኦሮሚያ ክልል በሸዋ ጊንጪ አቅራቢያ በጅባትና ሜጫ አውራጃ በዳንዲ ወረዳ ዩብዶ በሚባል ቦታ የተወለዱት ሌተናል ጄኔራል ጀጋማ ...

Read More »