Author Archives: Central

በሶማሌ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ በየዕለቱ ከ500 የሚበልጡ ሰዎች ለህመም እየተዳረጉ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 9 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ በየዕለቱ ከ500 የሚበልጡ ሰዎች ለህመም በመዳረግ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የተባበሩት መንግስታት እና የእርዳታ ድርጅቶች በበሽታው ወረርሽኝ ሰዎች በመሞት ላይ መሆኑን ቢያረጋግጡም መንግስት የሟቾች ቁጥርን ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁንና የበሽታ ወረርሽኙ በመባባስ ላይ መሆኑን ተከትሎ በወረርሽኙ በተጠቁ በርካታ ወረዳዎች በየዕለቱ ከ500 የሚበልጡ ሰዎች በበሽታው እየተያዙ መሆኑ ተመልክቷል። ...

Read More »

የውጭ ምንዛሬ እጥረት በመባባሱ ፋብሪካዎች ስራቸውን እንዲያቆሙ እያደረጋቸው ነው

ሚያዝያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና አማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ፋብሪካዎች ድርጅቶቻቸውን እስከመዝጋት እየደረሱ ነው። የአገሪቱን የፋይናስ ስርዓት በተገቢው መንገድ ይመራል ተብሎ የተቋቋመው ብሄራዊ ባንክ ለንግድ ባንክ ከግል ባንኮች በተለየ የሚሰጠው የዶላር አቅርቦች የግል ባንኮች ለደንበኞቻቸው በቂ የውጭ ምንዛሬ እንዳያቀርቡ በማድረጉ ባንኮቹ የህለውና አደጋ ተደቅኖባቸዋል። አቶ ...

Read More »

የዓለም የምግብ ድርጅት እና የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያ ለድርቅ ጉዳተኞች እርዳታ ለገሱ

ሚያዝያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሳኡዲ አረቢያ መንግስት እና የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) በጋራ ኢትዮጵያ ውስጥ አፋጣኝ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የርሃብ ተጠቂዎች የሚውል ረድኤት እርዳታ ለግሰዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ክልል በድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ርሃብ ተጋላጭ ለሆኑ የ127 ሽህ 666 ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ የሚያስችል ለድንገተኛ አገልግሎት የሚውል እርዳታ ሰጥተዋል። የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በንጉስ ሳልማን የእርዳታ ማእከል አማካኝነት ...

Read More »

ታንዛኒያ ውስጥ 66 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ

ሚያዝያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ እለት ሕጋዊ የመግቢያ ሰነድ ሳይዙ ወደ ታንዛኒያ የገቡ 66 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን የታንዛኒያ የድንበር ፖሊስ አስታውቋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በተጨናነቀ ሁኔት ተጭነው ሲገቡ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳሂር ኪዳቫሻሪ ተናግረዋል። ኮማንደር ዳሂር ”ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞች የጫነውን መኪና በፓትሮል ተከታትለን መንገድ በመዝጋት ኢሶንጄ ከተማ መቃረቢያ ላይ ይዘናቸዋል። ...

Read More »

በቢሾፍቱ ከተማ የአህያ ቄራ መዘጋቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 9 ፥ 2009) በቢሾፍቱ ከተማ የአህያ ስጋን እያዘጋጀ ለውጭ ሃገር ገበያ የሚያቀርበው ቄራ ከህዝቡ በተነሳ ተቃውሞና ጫና መዘጋቱ ተገለጸ። በኦሮሚያ ክልል የቢሾፍቱ አስተዳደርን ጠቅሶ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት የአህያ እርድ ቄራው መዘጋቱን አረጋግጧል። የአህያ ስጋ ቄራው በመንግስት ፈቃድ ተሰጥቶት በቀን 2መቶ አህዮችን በማረድ ስጋውን እና ቆዳውን ወደ ቻይና መላክ ጀመሮ ነበር። ጉዳዩ ከተሰማ በኋላ የአህያ ቄራው ከህዝቡ ሃይማኖት እና ...

Read More »

ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደምትገኝ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት መካከል ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደምትገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ይፋ አደረገ። የ2016 አም አመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው ድርጅቱ ኢትዮጵያ ከ189 ሃገራት በሰው ሃብት ልማቱ በ174ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧንና የያዘችው ደረጃም በአህጉሪቱ ዝቅተኛው መሆኑን አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ጥናቱን ካካሄደባቸው 189 ሃገራት መካከል 41ዱ ...

Read More »

የስቅለት በዓል በመላ ኢትዮጵያ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተከበረ

  ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) የዘንድሮው የእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተከበረ። ይኸው የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በስግደት እንዲሁም በልዩ የጾም ስነ-ስርዓት ተከብሮ መዋሉን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። አርብ መከበር የጀመረው የስቅለት በዓል ምሽቱን በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በሚካሄዱ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚቀጥል ሲሆን፣ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽን 50 ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ በምትገኘው የብርቆድ ከተማ በመዛመት ላይ ባለ የኮሌራ በሽታ ወረርሽን 50 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በአካባቢው በመንግስት የተጣለው የንግድና የሰዎች ዝውውር እገዳ የበሽታው ስርጭት ወደ ከፋ ደረጅ እንዲሸጋገር ማድረጉን መቀመጫውን በቤልጅየም ብራሰልስ ከተማ ያደረገውና Unrepresented Nations and People’s Organization (UNDO) የተሰኘው አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል። በዚሁ ...

Read More »

ቤት ለመግዛት አስፈላጊውን ክፍያ የፈጸሙ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቤታቸውን ለመረከብ ሲሄዱ ወደሆቴልነት ተቀይሮ እንደጠበቃቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት ለመግዛት ክፍያን ከፈጸሙ በኋላ ቤቱን ለመረከብ ሲሄዱ ሆቴል ሆኖ እንደጠበቃቸው ተዘገበ። ድርጊቱን የፈጸመው ኬርያ የተባለው ሪል ስቴት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢያመራም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይበልጥ አስገራሚ መሆኑ ተመክቷል። የማምኮ ወረቀት ፋብሪካ ሃላፊ በሆኑ በሼክ መሃመድ  አላሙዲ አጎት በአቶ መርዱፍ የተቋቋመው ኬሪያ  ሪል  ስቴት፣ ከሰባት አመት ...

Read More »

የስቅለት በዓል በመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የስቀለት በዓልን አክብረው ውለዋል። በኢትዮጵያ የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በስግደት እና ጸሎት አሳልፈዋል። በዚህ አመት የአመት በአል ገበያ የዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ወኪላችን ገልጿል። በተለይም በእርድ በሬ፣ ዶሮና ሽንኩርት ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።በደቡብ እና ኦሮምያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ዘይትና ስኳር ሙሉ በሙሉ ከገበያ ...

Read More »