ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮግራም በከተማ ኗሪ የሆኑ ‹‹በሚቀጥሉት 10 አመታት ከአጠቃላይ ድህነት ወለል በታች ያሉ 90 በመቶ የሚሆኑ ስራ አጦችን እንዲሁም ለማህበራዊ ኑሮ ችግርና ጠንቅ የተጋለጡ ዜጎች ወደ ስራ እንዲሰማሩና 10 በመቶ የሚሆኑት የመስራት አቅም የሌላቸው የማህበራዊ ጠንቅ ሰለባዎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኙ›› የሚል አላማ ይዞ በ2005 ...
Read More »Author Archives: Central
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እና 10 የመልሶ ማልማት ‹‹መሰረት ድንጋይ ›› ሳይቀመጥ ቀረ
ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኝ 10 ሺህ ካሬ/አንድ ሄክታር/ ለሆቴል ግንባታ በካሬ 650 ሺህ ብር ሊዝ የገዙት የኳታሩ ባለሃብት ፣ አገዛዙ ቦታው ላይ የሰፈሩትን ነዋሪዎች በሙሉ አንስቶ ቦታውን አጽድቶ መጨረሱን በመግለጽ የመሰረት ድንጋይ እንዲያስቀምጡ ቢጋብዝም፣ ባለሃብቱ ግን ‹‹ህዝብ ተፈናቅሎ እያለቀሰ ባለበት ሰአት የመሰረት ድንጋይ አላስቀምጥም›› ማለታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የገዢው ፓርቲ ...
Read More »በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የቦንብ ፍንዳታን ባስተናገደችው ጎንደር፣ ማክሰኞ ምሽት 2 ሰአት አካባቢ ታክሲ ማዞሪያ በጌምድር ሆቴል አካባቢ ቦንብ መፈንዳቱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የሚገለጹት እማኞች፣ በፍንዳታው ወቅት ከፍተኛ ድምጽ ከመሰማቱ ጋር ተያይዞ በአካባቢ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር ብለዋል። የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከ15 ...
Read More »በእስር ቤት ለወራት ታስረው የሚገኙ የነጻነት ታጋዮች ለችግር ታድርገዋል
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና የእስረኞችን ሁኔታ የሚከታተሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ለመብታቸው በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ገብተው ሲታገሉ የነበሩ፣ በግላቸው በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋልጡ እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርተው ለአገራቸው የሚችሉትን መስዋትነት በመክፈል ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ከሚደርስባቸው ስቃይ በተጨማሪ፣ መሰረታዊ የሚባሉትን ልብስ እና ጫማዎችን ለመቀየር አልቻሉም። ከአማራ ...
Read More »አቶ መኳንንት ካሳሁን በማእከላዊ ድብደባው እንዲቆምለት ፍርድ ቤቱን ጠየቀ
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ብስራት አቢ እና ደቡብ ወሎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ መኳንንት ካሳሁን ከደሴ ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ከአንድ ወር ከ5 ቀን በኋላ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። አቶ መኳንንት ካሳሁን ሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ክቡር ፍርድ ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የመወያያ መድረክ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሰብዓዊ መብቶች አካባቢ ላይ ልዩ የመወያያ መድረክ እንዲያዘጋጅ አሜሪካ ጠየቀች። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለበርካታ ሃገራት አለመረጋጋት ምክንያት እየሆኑ መምጣቱን የገለጸችው አሜሪካ፣ ምክር ቤቱ የሰብዓዊ መብት መከበር ግጭትን ለመከላከልና ለአለም ሰላምና ደህንነት ያለው ሚና ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስባለች። በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ኒኪ ሃሊ ቀጣዩ የአለም ቀውስና አለመረጋጋት የሰብዓዊ ...
Read More »በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአመቱ የመደቡትን በጀት የኮሌራ ወረርሽንን ለመከላከል እንዲያውሉት ተጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) በሶማሌ ክልል በእርዳታ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለተለያዩ የሰብዓዊ ዕርዳታ ስራ የያዙትን በጀት እየተባባሰ ላለው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ መከላከያ እንዲያዞሩ ተጠየቁ። በሃገሪቱ መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት ዘንድ የሚካሄዱ የዕርዳታ ስራዎችን የሚያስተባብረው Ethiopian Humanitarian Fund በክልሉ በመዛመት ላይ ያለው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ዕልባት ባለማግኘቱ ምክንያት ድርጅቶቹ በበጀታቸው ላይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቋል። በሰባት ...
Read More »የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደርቦች ከ380 ሺ ብር በላይ ከተጠርጣሪ ወስደዋል ተብለው ክስ ተመሰረተባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሁለት ባልደርቦች ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተሰማሩ ጊዜ ከ380 ሺ ብር በላይ ከተጠርጣሪ ወስደዋል ተብለው ክስ ተመሰረተባቸው። አቶ ባህሩ አዱኛና አቶ ደራ ደስታ የተባሉ የደህንነት ሰራተኞቹ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ ነዋሪ የሆኑትን አቶ ኡመር አብዶ የተባሉ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተሰማሩ ጊዜ 418 ሺ 500 ...
Read More »ወደ አራት ሚሊዮን አካባቢ የሚሆኑ የሞባይል ስልኮች አገልግሎት እንዳይሰጡ ሊደረግ መሆኑ ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በተጠቃሚ እጆች የሚገኙ ወደ አራት ሚሊዮን አካባቢ የእጅ ስልኮች (ሞባይሎች) አገልግሎት እንዳይሰጡ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ። የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከወራት በፊት በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ አዲስ የመመዝገቢያ ስርዓት ተግባራዊ እንዲደረግ መመሪያ አውጥቶ የነበር ሲሆን፣ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ ሞባይሎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ በዚሁ መመሪያ ተደንግጓል። አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግና ...
Read More »ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለውጭ ጋዜጠኞች ሊሰጡ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰረዘ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ረቡዕ በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለውጭና ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች ሊሰጡ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰረዘ። ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ግን መግለጫ መስጠታቸው ተዘግቧል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለተጋበዙ ጋዜጠኞች ባሰራጨው አስቸኳይ መልዕክት የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም እንዳማይካሄድ አስታውቋል። ይሁንና ጽ/ቤቱ መግለጫው በሌላ ጊዜ እንደሚካሄድ ቢገልፅም የረቡዕ ፕሮግራም በምን ምክንያት ሊሰረዝ እንዳቻለ ...
Read More »