Author Archives: Central

የአቅም ችግር ታይቶባቸዋል የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው ነው ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2009) በጥልቅ ተሃድሶው የአቅም ችግር ታይቶባቸው የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑን ተነገረ። የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከብዓዴን የድርጅቱ የጽህፈት ቤት ሃላፊና አማራውን በመዝለፍ የሚታወቁት አቶ አለምነህ መኮንን ተከተዋል። የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በመጭው ሰኞ ይጀምራል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአቅም ችግር ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል። በሁለተኘው ዙር ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የነጻነት ታጋዮች የሚፈጽሙት ጥቃት ቀጥሎአል

ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 አባላት የሆኑ ታጋዮች በደምቢያ ወረዳ ሰረባ መስኖ አጠገብ ሌሊት ላይ ጥቃት ፈጽመው፣ 2 ገልባጭ መኪኖችና አንድ እስካቫተር መኪና የተቃጠሉ ሲሆን፣ በታጋዮች እና ድርጅቱን በሚጠብቁት መካከል ለ30 ደቂቃ ያክል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንና አንድ ወታደር መገደሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል። ኢሳት ወደ አካባቢው ነዋሪዎች ስልክ በመደወል በመኪኖች ላይ ከፍተኛ ...

Read More »

በአለፉት 6 ወራት ብቻ 325 ሰዎች እስር ቤት ህይወታቸው አልፏል

ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2009 ዓ.ም የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 325 በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። አሃዙ በቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት የጋዩት እና በጥይት የተገደሉን እንዲሁም በብርሸለቆ እና በሰባት አሚት እስር ቤት በግፍ የተገደሉ እስረኞችን ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ አሃዙ በየቀበሌው ያሉትን ጊዚያዊ እስር ቤቶችን መረጃ አላካተተም። ከ325 ሟች እስረኞች መካከል 49 ኙ ...

Read More »

የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከሽፏል ተባለ

ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመንና በበርካታ የሶሻሊስት አገሮች ሲሰራበት የነበረው የመንግስት ሰራተኛውን በአንድ ለአምስት አደራጅቶ የመቆጣጠርና የመምራት አሰራር መክሸፉን አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ አመራር አካዳሚ በተደረገ ስብሰባ ላይ የአካዳሚው ዳይሬክተር፣ የመንግስት ሠራተኛው የአንድ ለአምስትን ስብሰባን “መቼ ነው አላቆኝ የማየው?” በማለት በምሬት እስከ መግለጽ ደርሷል ብለዋል፡፡የዚህ ዓይነት ጥላቻ ...

Read More »

የስነዜጋ እና የስነምግባር ትምህርት ውጤት አላመጣም ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2009) በትምህርት ተቋማት የስነዜጋና የስነምግባር ግምባታና ዴሞክራሲያዊነት ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ ሰሞኑን በተካሄደው መድረክ ላይ እንደተገለጸው በት/ቤቶች የሚሰጠው ይኸው የሲቪክ ትምህርት ውድቀት ገጥሞታል። በአቶ አባይ ጸሃዬ የሚመራው የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ የአመራር ድክመት በዋና መንስዔነት ተቀምጦ ለአመታት ሲሰጥ የቆየው ትምህርት ውጤት አላመጣም ተብሏል። በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ኢህአዴግ ፖለቲካዊ አቋሞችን በሚያንጸባርቅ መልኩ ተዘጋጅቶ ከአንደኛ ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ለአለም አቀፍ ዕርዳታ ድጋፍ ለማስቀረት አዲስ እቅድ መንደፉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በየአመቱ ለአለም አቀፍ ዕርዳታ የሚሰጠውን 12 ቢሊዮን ፖውንድ ድጋፍ ለማስቀረት አዲስ እቅድ መንደፉ ተገለጸ። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ፓርቲያቸው በቀጣዩ ወር በሚካሄደው የምርጫ ሂደት ሃሳቡን ያሳውቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሪታኒያው ዘጋርዲያን ጋዜጣ ሃሙስ ዘግቧል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ደሃ ሃገራት ብሪታኒያ ለአለም አቀፍ እርዳታ ከምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነው መቆየታቸው ታውቋል። ይሁንና ብሪታኒያ ለተለያዩ ...

Read More »

የድርቅ አደጋ ለመከላከል ከሚያስፈልገው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መካከል 23 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሚያስፈልገው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መካከል 23 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ተገለጸ። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ ድርቁ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የከፋ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት እና አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች አስታውቀዋል። ባለፈው አመት በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ተመሳሳይ የድርቅ አደጋ ከመንግስትና ከአለም አቀፉ ...

Read More »

በአቶ ዓባይ ጸሃዬ የቀረበውና አስፈጻሚ አካላት ከህግ በላይ ሆነዋል የሚለውን ጥናት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይማሪያም ደሳለኝ አጣጣሉት

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በአቶ ዓባይ ጸሃዬ የቀረበውና አስፈጻሚው አካላት ከህግ በላይ ሆነዋል የሚለውን ጥናት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይማሪያም ደሳለኝ አጣጣሉት። አቶ ሃይለማሪያም ከተመረጡ የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በቅርቡ በአቶ አባይ ጸሃዬ እና በተወሰኑ የመንግስት ተጠሪዎች የቀረበውን ጥናት አላውቀውም፥ ትክክለኛ ግምገማም አይደለም ሲሉ ውድቅ አድርገውታል። ይህን የሚያመለክተው የአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መግለጫ በኢትዮጵያ ...

Read More »

በአማራ ክልል ብቻ ከ66 ሺ በላይ ዜጎች በማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ

ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እንዳስታወቀው በክልሉ 66 ሽህ 102 ዜጎች በፍርድ እና ያለፍርድ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። በክልሉ የእስረኛው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ በመሄዱ የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡበት ጠይቋል። እስረኞቹን ለማስተናገድ የተበጀተው በጀት ማለቁንም ኮሚሽኑ አስታውቋል። እስረኞቹ በአማካኝ ከ5 እስከ 10 ዓመታት በፍርድ ወይም ያለፍርድ በእስር እንደሚማቅቁ የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ክልሉ ...

Read More »

የተቅማጥ (አተት በሽታ) በመላ አገሪቱ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል

ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ከሚታየው ድርቅና የንጽህና ጉድለት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ከፍተኛ ስጋር ፈጥሯል። በአዲስ አበባ የበሽታው ስርጭት እየቀነሰ ነው ቢባልም፣ በዚህ ሳምንት ብቻ 25 በሽተኞች ህክምና ማግኘታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአማራ ክልል በ21 ወረዳዎች ፣ በትግራይ 5 ወረዳዎች ፣ በኦሮሚያ 16 ወረዳዎች ...

Read More »