Author Archives: Central

አንድ የማዕድን ኩባንያ ለወርቅ ፍለጋ በተሰጠው መሬት ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ዝግጅት ጀመረ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ የማዕድን ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል ለወርቅ ፍለጋ በተሰጠው መሬት ላይ የሚኖሩ በርካታ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ከፊ ሚነራል የሚል መጠርያ ያለው ይኸው አለም አቀፍ ኩባንያ ከአንድ አመት በፊት ከመንግስት ጋር በደረሰው ስምምነት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር በምትገኘው የቱሉ ቃቢ አካባቢ የወርቅ ማውጫ ሰፊ ይዞታ ለ20 ...

Read More »

በሆለታ ከተማ ከገበሬዎች ለወሰደው የአበባ እርሻ መሬት ኪራይ ክፍያ ያልፈጸመ የህንድ ኩባንያ መሬቱን እንዲያስረክብ ተወሰነ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤት በሆለታ ከተማ ከገበሬዎች ለወሰደው የአበባ እርሻ መሬት መክፈል የሚጠበቅበትን የኪራይ ክፍያ ያልፈጸመ አንድ የህንድ ኩባንያ መሬቱን እንዲያስረክብ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ በቅርቡ የሰጠውን ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ኢትዮጵያን ሚዶውስ የተሰኘው ኩባንያ ከ13 አርሶ አደሮች በኪራይ የወሰደውን 108 ሄክታር መሬት መመለሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁንና የኩባንያውን ባለድርሻዎች ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ...

Read More »

አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) የሶማሌው ታጣቂ ሃይል አሸባብ በማዕከላዊ  ሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። ይኸው ጥቃት በሂራን ግዛት ስር በምትገኘውና ከበለደወይን ከተማ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የቡርዳር ከተማ መፈጸሙን ጋሮዌ ኦንላይን የተሰኘ የመገናኛ ተቋም የአይን እማኞች ዋቢ በማድረግ በዘገባው አመልክቷል። በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል ስር በሚያገለግሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ...

Read More »

ግንባታቸው የተስተጓጎለው ፋብሪካዎች ወደ ግንባታ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከህንድ ባለስልጣናት ጋር ምክክር እያካሄዱ መሆኑ ታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች የተመራ የልዑካን ቡድን ግንባታቸው ተስተጓጎሎ የሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ግንባታ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከህንድ ባለስልጣናት ጋር በሃገሪቱ ምክክር እያካሄዱ መሆኑ ታወቀ። የህንድ መንግስት ኮርፖሬሽኑ ሊያካሄዳቸው ላቀዳቸው 10 የስኳር ፋብሪካዎች ማስጀመሪያ ከአራት አመት በፊት የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። የህንድ መንግስት ለፋብሪካዎቹ ግንባታ ካቀረበው ብድር በተጨማሪ በርካታ ሰራተኞች በፕሮጄክቶቹ እንዲሰማሩ ...

Read More »

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ አገዳ ምርት እጥረት ወደ ስራ አለመግባቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) ከሁለት አመት በፊት ስኳርን ለውጭ ገበያ ያቀርባል ተብሎ የነበረውና ግንባታው በቅርቡ የተጠናቀቀው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ አገዳ ምርት እጥረት ወደ ስራ አለመግባቱ ተገለጸ። ይኸው ከህንድ መንግስት በተገኘ ብድርና ከሃገር ውስጥ የመንግስት በጀት የተቋቋመው የስኳር ፋብሪካ ኣጋጥሞታል የተባለው የምርት አቅርቦት እስከቀጣዩ አራት አመት ድረስ የሚዘልቅ መሆኑም ታውቋል። የፋብሪካውን ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርትን ለፓርላማ ያቀረበው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ...

Read More »

በአርባምንጭ ገዢው ፓርቲ የሚያሰማው የቦንድ ግዢ ቅስቀሳ ሰሚ አላገኘም

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የአባይ ግድብ ዋንጫ ወደ ከተማው ይመጣል በሚል ህዝቡ ዋንጫውን እንዲቀበል የገንዘብ መዋጮና የቦንድ ግዢ እንዲፈጽም ቢጠየቅም፣ ከህዝቡ የተገኘው ምላሽ ዝቅተኛ ነው። ነጋዴዎች እስከ 20 ሺ ብር፣ በአነስተኛ ስራ የሚተዳደሩት ደግሞ እስከ 150 ብር እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ ነዋሪዎች ግን መክፈል ካለብን በፈቃዳችን እንከፍላለን እንጅ ልንገደድ አይገባም በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ...

Read More »

ጄ/ል ገብሬ አዲሱን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ነቀፉ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ራሳቸውን የምስራቅ አፍሪካ አገራት ሕብረት -ኢጋድ የሶማሊያ ተወካይ አድርገው የሚቆጥሩት የቀድሞው በኢትዮጵያ የሶማሊያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገብሬ ዲላ ፣ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በሶማሊያ ለተሰማሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት አክብሮት አላሳዩም በሚል ነቅፈዋቸዋል። ብ/ ጄኔራል ገብሬ በኦፊሻል የትዊተር ገጻቸው ላይ በጻፉት አጭር መልእክት ላይ እንዳሉት ”ፕሬዚዳንቱ ...

Read More »

የሰብአዊ ኮሚሽን ሪፖርትን ተከትሎ አመጽ ይነሳል በሚል በኦሮምያ የፌደራል ፖሊሶች ተሰማሩ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀደሞው ምርጫ ቦርድ ም/ል ሰብሳቢ በህወሃቱ አባል ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው ራሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብሎ የሚጠራው ድርጀት ከፍተኛ አመጽ ተነስቶባቸው በነበሩ የኦሮምያ ከተሞች 495 ሲቪል ዜጎች መገደላቸውን ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቀሴ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል በሚል በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በደንብ የታጠቁ ወታደሮች የአመጹ ...

Read More »

የሶማሊ ልዩ የሚሊሺያ አባላት የደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ። ታጣቂዎቹ ትእዛዝ ለመቀበል ፈቀዳኛ አለመሆናቸውንም አስታውቀዋል

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከ200 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆችን በመግደላቸው እየተወነጀሉ ያሉት በአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ አባላት ፣የደረሰባቸውን ጥቃት ተከትሎ፣ የጉዳት ካሳና ደሞዝ ካልተጨመራቸው ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ለመዝመት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ አካባቢው በቅርቡ የተጓዙት አዲስ የተሾሙት የደህንነት አባል መከላከያው የልዩ ሃይሉን ቦታ ...

Read More »

በደቡብ ጎንደር ዞን ዜጎች በብዛት እየታሰሩ ነው

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ ወዲህ በተለያዩ ሰበቦች በርካታ ዜጎች እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። የማሰር ዘመቻው ወደ ካህናቱም ወርዶ በትናንትናው እለት በአንዳቤት ወረዳ በርካታ ካህናት ቤተክርስቲያን ማስተዳደር አልቻላችሁም ተብለው ታስረዋል። የደቡብ ጎንደር ሃገረ ሰብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት መላከ ሰላም አባ ሃይለየሱስ ቢያድግልኝ መታሰራቸውንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የእርሳቸው መታሰር የአካባቢውን ...

Read More »