Author Archives: Central

ሁሉን አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ ምክር ለመመስረት ስምምነት መደረጉን በሲያትል በተካሄደው ጉባዔ ተመለከተ

ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን በማስተባበር ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ ምክር ቤት ለመመስረት ስምምነት መደረጉን በሲያትል የተካሄደው ጉባዔ የአቋም መግለጫ አመለከተ። በአቋም መግለጫው እንደተመለከተው በኢትዮጵያ የተካሄውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የበለጠ ማጠናከር ያልተቻለው ጠንካራ የተቃዋሚ ሃይሎች ህብረት ባለመኖሩ ነው።  ስለሆነም፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሽግግርነት ሁሉን አሳታፊ ብሄራዊ ምክር ...

Read More »

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ዱባይ አሸሽተዋል የተባሉ አንድ የውጭ ዜጋ በ25 አመት እስራት እንዲቀጡ ወሰነ

ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩትን 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ዱባይ አሸሽተዋል ከተባሉ ሁለት ተከሳሾች መካከል ትውልደ ግብጻዊና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ማክሰኞ ወሰነ። ሁለተኛ ተከሳሽና በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ ሆነው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ ደግሞ የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የፍርድ ...

Read More »

ሰመጉ “በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ” ዜጎች በእስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን ስቃይ ይፋ አደረገ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብአዊ መብት ጉባኤ በ142ኛ ልዩ መግለጫው ላይ እንደጠቀሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም 29 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከ22 ሺ በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የሆኑ የቅጣት እርምጃዎች በእስረኞች ላይ እንደሚፈጸሙ ገልጿል። ሰመጉ ወታደራዊ ካምፖች ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች እስርቤት ሆነው ማገልገላቸውን ገልጾ፣ በተለይ በወታደራዊ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በአንድ የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ልዩ ስሙ ጎርጎራ ክፍል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ግንቦት21 ቀን 2009 ዓም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በአንድ የህወሃት የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል። በደንቢያ ወረዳ የህወሃት ሰላይ በመሆን በአካባቢው ህዝብ ላይ ለሚደርሰው ግድያ ፣ አፈናና እስር ዋና ተጠያቂ ነው ባለው ...

Read More »

የሱዳን ገበሬዎች ከኢትዮጵያ ተቆርሶ የሚሰጣቸው መሬት አነስተኛ ነው በማለት አማረሩ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ከ12 ዓመታት በፊት የተጀመረው ድርድር ተግባራዊነት እውን ሊሆን ጫፍ መድረሱን ተከትሎ የሱዳን የመገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ገበሬዎቹ የሚሰጠን መሬት ትንሽ ነው በማለት እያማረሩ መሆኑን የሱዳን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። በገዳሪፍ አካባቢ የሚኖሩ የሱዳን ገበሬዎች በቅርቡ የግዛቱ አስተዳዳሪ የሆኑት ...

Read More »

ለኢትዮጵያ ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሽልማት ተበረከተላቸው

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) ለኢትዮጵያ ሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ 8 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ሃገር ባደረገ ተቋም ሽልማት ተበረከተላቸው። ማህበረ ጊወራን ዘረ ኢትዮጵያ ወይም /ሲድ/ የተባለው ይኸው ተቋም ላለፉት 25 አመታት ለሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን በመሸለም ይታወቃል። በሜሪላንድ ግዛት ኮሌጅ ፓርክ ዕሁድ ግንቦት 20/2019 ከተሸለሙት ስምንቱ ታዋቂ ኢትዮጵያውን መካከል አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን እና የትዝታው ንጉስ መሃመድ አህመድ ይገኙበታል። ...

Read More »

በህይወት መኖራቸው ያልታወቁት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ተወሰነ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ያልታወቀ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ወሰነ። ለበርካታ አመታት በፍትህ ስርዓት ውስጥ ያገለገሉት አቶ ልዑል ላለፉት ስምንት ወራት ውስጥ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የመስሪያ ቤታቸው ባልደርቦች ዳኛው ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ ለፓርላማው የቀረበን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ ለቀቁ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) በቅርቡ የብድር መጠኑ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ለ10 አመታት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸው ታውቋል። ሃላፊው ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ቢረጋገጥም ምክንያቱ ግን በኮርፖሬሽኑም ሆነ በዶ/ር ጌታቸው አልተገለጸም። መንግስታዊ ተቋም በሃገሪቱ ሰፊ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ባቀደ ጊዜ ዶ/ር ጌታቸው ፕሮጄክቶችን በመቆጣጠርና ...

Read More »

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ከእገታ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ። ስሙ ይፋ ባልተደረገው ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ላይ እገታውን ፈጽመዋል የተባሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ኒውስ 24 የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። ሶስቱ ግለሰቦች ኢትዮጵያዊ ነጋዴውን ከጆሃንስበርግ ከተማ በቅርቡ ርቀት ላይ ከሚገኘው የኦ አር ታምቦ (O R Tambo) አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የንግድ ...

Read More »

በሳውዲ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አልታወቀም

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) በሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ከ700 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አለመታወቁ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ ያለፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 40ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመውጫ ቪዛ አግኝተዋል ቢልም፣ ሌሎች ከ700 ሺ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ ...

Read More »