Author Archives: Central

የአቶ አለምነው መኮንን የግል አጃቢ በሆቴል ውስጥ መገደላቸው ታወቀ

ሰኔ 14 ፥ 2009 የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣንና የብአዴን ፅ/ቤት ሃላፊ የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ ሆቴል ውስጥ መገደላቸው ታወቀ። በሌላ ሰው ሥም በተያዘ ሆቴል ውስጥ አጃቢው መገደላቸውና ሆቴሉን የያዘው ሰው አለመታወቁ አነጋጋሪ ሆኗል። ግድያውንም ተከትሎ በብአዴን አመራር በተለይም በአቶ ዓለምነው መኮንን ዘንድ ሥጋት መፈጠሩ ተመልክቷል። የኣቶ ዓለምነው መኮንን አጃቢ አቶ አንዋር መሐመድ የተገደለው ሰኞ ሰኔ 12/ 2009 በባህርዳር ቀበሌ ...

Read More »

የቀን ገቢ ግምት በማስላት በነጋዴዎች ላይ የሚጣለው ግብር ከፍተኛ ተቃውሞ አስከተለ

ሰኔ 14 ፥ 2009 የቀን ገቢ ግምትን በማስላት በነጋዴዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተቃውሞና ውጥረት ማስከተሉን የኢሣት ምንጮች ከአዲስ አበባ ገለፁ። በተለይ በዋናው የገበያ ማዕከል መርካቶ ነጋዴዎች እየተዋከቡ ሲሆን እርምጃው ነባር ነጋዴዎችን እየገፋ እዚህ መድረሱንም መረዳት ተችሏል። ድንገት በገበያ ሥፍራዎች የሚሰማሩትና በኢሕአዴግ የተለያዩ መዋቅር የተሰለፉት የቀን ግምት ገማቾች ግዢ ፈፅመው የሚሄዱ ሸማቾችን ጭምር በማዋከብ ላይ መሆናቸውን የሚገልፁት የኢሣት ምንጮች ፌደራል ፖሊስም ...

Read More »

በትግራይና በአማራ ክልሎች የእግር ኳስ ቡድኖች ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች ተሰረዙ

ሰኔ 14 ፥ 2009 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አማካኝነት በባህርዳር ከነማና በሽሬ እንደስላሴ ቡድን እንዲሁም በመቀሌ ከነማና በአማራ ውሃ ሥራዎች መካከል በባህርዳር ሊካሄድ የታቀደው ጨዋታ ላልታወቀ ጊዜ መራዘሙን ፌደሬሽን አስታወቀ። በባህርዳር ከተማ የሚገኙ የአማራ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ቢሮዎች ጨዋታው ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር መጠየቃቸውንም ማክሰኞ ፌደሬሽኑ ሰኔ 13/ 2009 በፃፈው ደብዳቤ አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ...

Read More »

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የገንዘብ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ

ሰኔ 14 ፥ 2009 መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የገንዘብ እጥረት እንደገጠመውና በጀት እንዳልመደበ ተገለጠ። የከተማ ቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስትሩ ለፓርላማው እንዳስታወቁት፣ መንግስት በገጠመው የገንዘብ ችግር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን መቀጠል አልቻለም። የ1997 ዓም ሀገራዊ ምርጫ በተቃረበበት ወቅት የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላለፉት 13 ያህል ዓመታት ቢቀጥልም መንግስት በ2ኛው የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን 750 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ቢያቅድም በገጠመው የፋይናንስ ...

Read More »

የአቶ አለምነው መኮንን የግል አጃቢ መገደል በካድሬዎች ላይ ሽብር ፈጥሯል

ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ስራውን በፈቃዱ ለቋል በአማራ ክልል ህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠሉትና የህወሃት ቀኝ እጅ ተድርገው የሚቆጠሩት የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ የሆነው አንዋር ሙሃመድ የተባለው ግለሰብ፣ ባህርዳርቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ውስጥ በጥይት ተመትቶ ተገድሎ ከተገኘ በሁዋላ፣ የብአዴን ካድሬዎችና የአቶ ዓለምነው የቅርብ ወዳጆች ሽብር ውስጥ መግባታቸውን ...

Read More »

በኦህዴድ ውስጥ የእርስ በርስ መጠላለፍና መወነጃጀል ተፈጥሯል

በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሓት ታማኞች ጓዶቻቸውን እያሳደዱና እያሰሩ ነው። ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ ውሰጥ ያሉ ታማኝ የህወሓት አገልጋዮቸ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የራስ መተማመንንበማዳበር ላይ ያሉትን የኦህዴድ አመራር አባላትን ማደን ጀምረዋል። የህወኃት ተላላኪዎቹ-ጓደኞቻቸውን ኦህዴድ ውስጥ ሆነው ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። ባለፉት 2 ቀናት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ 3 የዞን አመራሮች የታሰሩ ሲሆን፤ አምስት ...

Read More »

የደደቢት ተጨዋቾች በክፍያ ምክንያት ከክለቡ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። የባህር ዳር ስፓርት ደጋፊዎች ተቃውሞ አሰሙ።

ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ዋነኛ ተፎካካሪ እየሆነ የመጣውና ለየሊጉን ዋንጫ እስከማንሳት የደረሰው የትግራዩ ደደቢት እግር ኳስ ክለብበዘንድሮ አመት የውድድር ዘመን ለተጨዋቾቹ ደሞዝ ባለመክፈሉ በክለቡ ውስጥ ውዝግብ ተፈጥሯል። ክለቡ የአምስት ወር ደሞዝ አልከፈለንም በማለት የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋቾች የሆኑት አይናለም ኃይሌ ፣ አስራት መገርሳ ፣ ሳምሶን ጥላሁን ፣ አክሊሉ አየነው ...

Read More »

ከ470 ብር ሺህ በላይ አጭበርብራ የታሰረች ግለሰብ በትዕዛዝ ተፈትታ ደህንነት ሥራ ላይ ተመደበች

ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በመረጃ ሠራተኝነት ስትሰራ የነበረችው እና “ቦታ አሰጣችኋለሁ” በማለት ከባህር ዳር ነጋዴወችና ከተለያዩ ግለሰቦች ከ470.00ሺህ ብር በላይ ገንዘብ በመቀበል ክስ ተምስርቶባት ታስራ የነበረች ሴት በትዕዛዝ ተፈትታ አሁንም በደህንነትና ስለላ ሥራ መሰማራቷ ተጠቆመ። በፈጸመችው የማጭበርበር ወንጀል ተይዛ በሙስና ተከሳ ከ 5 ወር በላይ በእስር ያሳለፈችው የትግራይ ተወላጇ ሰላም ...

Read More »

የፌዴራል አቃቤ ህግ ዶ/ር መረራ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ባለመቀበል ለፍ/ቤት አቤቱታ አቀረበ

ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አቃቢያን ሕግ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እንደማይቀበሉት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።  የፌደራል አቃቤ ሕጎች ማክሰኞ ሰኔ 13/ 2009 ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የተቃውሞ አቤቱታ ዶ/ር መረራ ጉዲና ክሳቸው ከኢሳትና ኦኤምኤን ተለይቶ የሽብር ክሳቸው በሌላ መታየቱን እንደማይቀበሉ ገልፀዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በአቃቤ ሕግ የቀረበውን በርካታ ክሶች ከሽብርተኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር ...

Read More »

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 80 ዓመታት ከግማሽ በላይ የቡና ምርቷን ልታጣ እንደምትችል አንድ ጥናት አመለከተ

ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በቀጣዬቹ 80 ዓመታት ኢትዮጵያ ከ60 በመቶ በላይ የቡና ምርቷን ልታጣ እንደምትችል አንድ ጥናት አመለከተ። ኔቸር ፕላንትስ የተሰኘ የሳይንስ መፅሄት ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ከፍተኛ ወደሆኑ መልከአምድሮች ምርታቸውን ካላበቀሉ 60 በመቶ የቡና ምርት ሊጠፋ ይችላል። በጥናቱ እንደተገለፀው የአካባቢ የአየር ንብረት ተፅዕኖ የሙቀት መጨመር አነስተኛ ...

Read More »