ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው መነኮሳቱ በጎንደር ከተማ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ተብለው ይፈለጉ ለነበሩ ግለሰቦች ከለላ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት የሽብርተኝነት ክስ ተከፍቶባቸዋል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ሰኔ 20/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ...
Read More »Author Archives: Central
የትምህርት ሚኒስትሩን የዝርፊያ ሰንሰለት የሚያሳዩ ተጨማሪ መረጃዎች እየመጡ ነው
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አሁን ትምህርት ሚኒስቴርን የሚመሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሙስና መዘፈቃቸውን በተመለከተ ኢሳት መረጃዎችን ማውጣቱን ተከትሎ፣ የክልሉ ነዋሪዎች በተለይ የአቶ ሽፈራውን የሙስና ሰንሰለት የሚያሳዩ መረጃዎችን እየላኩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው የአቶ ሽፈራው የሙስና ሰንሰለት እስከ ወረዳ የተዘረጋ ነው ይላሉ። ...
Read More »ወደ ማላዊ ሲገቡ የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር ቆራርጠው በማላዊ የድንበር ከተማ ካሮንጋ በኩል በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በድንበር ፖሊስ መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎችን ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ከቺቲፓ ወደ ካሮንጋ አውራጃ የሚወስደውን M1 አውራ ጎዳና ይዘው ሲጓዙ ነበር። የድንበር ፖሊሶችን መምጣት በማየት መንገዳቸውን ቀይረው በካሮንጋ አየር ...
Read More »ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ክልል ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥2009) ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ ኣዋጅ በሚንስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተሰማ። በቀጣዩ ሳምንት ፓርላማ ቀርቦ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል። ከሳምንት በፊት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ያሳለፈው ይህ ረቂቅ ኣዋጅ አዲስ አበባ የሚባለው የከተማው ስያሜ በነበረበት እንዲቀጥል ፊንፊኔ የሚለውም መጠሪያ በተጨማሪነት እንዲያገለግል ወስኗል። በሚኒስትሮች ም/ቤት ማክሰኞ እለት የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር በአዲስ ...
Read More »በቢሊዮን የሚቆጠር ብር የወጣባቸውና 25ሺ ያህል እስረኞችን የሚይዙ አዳዲስ ወህኒ ቤቶች በአራት ክልሎች ተገነቡ
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥2009) በቢሊዮን ብሮች ወጪ 25 ሺህ ያህል እስረኞችን የሚይዙ ወህኒ ቤቶች በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በዝዋይና በሸዋሮቢት መገንባታቸው ታወቀ። አዲስ ፎርቹን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው የአዲስ አበባ እስር ቤት 900 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሲሆን በአንድ ጊዜ 6 ሺህ እስረኞችን የመያዝ አቅም አለው። በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አባሳሙኤል ወንዝ አቅራቢያ በ5ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ የተዘረጋው ...
Read More »ቻይና በወንጀል የሚፈለጉ ቻይናውያን ለመቀበልና ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያንን አሳልፋ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አጸደቀች
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥2009) ቻይና በወንጀል የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ለመስጠት እንዲሁም በወንጀል የምትፈልጋቸውን ቻይናውያንና ሌሎችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል የተደረሰውን ስምምነት አጸደቀች። የቻይና ዜና አገልግሎት ዥንዋ እንደዘገበው የቻይና ብሄራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ ማክሰኞ ሰኔ 20/2009 ባካሄደው ስብሰባ ኢትዮጵያና አርጀንቲና በወንጀል የሚፈልጓቸውን ግለሰቦች አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት መሰረት ቻይና በወንጀል የምትፈልጋቸውን ግለሰቦች አርጀንቲናም ሆኑ ኢትዮጵያ ለቻይና አሳልፈው የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት የሙስና ሰንሰለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች ...
Read More »የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮማንደሮችን ስራ መልቀቅ በተመለከተ ለኢሳት ዘገባ መልስ ሰጠ
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ መልሱን የሰጠው ኢሳት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና የምዕራብ ጎጃም ዞን የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ኮማንደር በላይ ካሴ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በማስመልከት ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ማህበራዊ ሚዲያ አራማጆች የአማራ ክልል ኪሚሽን ስራ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና ኮማንደር በላይ ...
Read More »በማእከላዊ ዜጎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ሸራተን እየተባለ በሚጠራው የእስር ቤቱ ክፍል የሚገኝ ዘርኣይ አዝመራው የሚባል ከደባርቅ አካባቢ የመጣ ወጣት አባትህ ሸፍቷል በሚል በአሌክትሪክ “ ሾክ” ስለተደረገ ሰውነቱ እንደሚንቀጠቅ፣ በራሱ መሄድ ባለመቻሉም በድጋፍ እንደሚጓዝ ታውቋል። ሌሎችም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ተይዘው የመጡ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ለአካል ጉዳት ተደርገዋል። አእምሮን በሚጎዳ ...
Read More »አንድ ሺህ 438ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በመላው አለም ተከበረ
ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) በአዲ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር በተገኙበት ዩ ኤስ አሜሪካ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ስነ-ስርዓት መከበሩን ዜናው ያስረዳል። የፈርስት ሂጂራ ፋውንዴሽን ኢማም ሼህ ካሊድ ኡመር እና የፋውንዴሽኑ ፕሬዝዳንት ሃጂነጂብ መሃመድ በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ቨርጂኒያ ግዛት በተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ሙስሊሙ ማህበረሰብ በብዛት መገኘቱም ታውቋል። በከፍተኛ ...
Read More »