ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በመጋቢት ወር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ እንዳይቆረጥባቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ደሞዛቸው ሳይቆረጥባቸው የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን የአመቱን የስራ ማጠናቀቂያ ተከትሎ መምህራን ስለሚበታተኑ ተቃውሞ አያነሱም በሚል ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ 30 በመቶ እንደሚቆረጥባቸው ወረዳው መናገሩን ተከትሎ መምህራን ...
Read More »Author Archives: Central
የቂሊንጦ እስረኞች የግዳጅ የጉልበት ስራ እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቂሊንጦ እስር ቤት የግዳጅ የጉልበት ስራ እያሰራቸው መሆኑን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት እነ ጌታሁን በየነ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ እስረኞቹ ፣ 200 ኪሎ ግራም ቆሻሻና የ125 እስረኞች የሚቀርብን ወጥ ሁለት ሰዎች ብቻ እንዲሸከሙ እንደሚገደዱና ይህም ...
Read More »የማላዊ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ ወደ አገሬ ገብተዋል ባላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የገንዘብ ቅጣት ፈረደ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብታችኋል በተባሉ 27 ስደተኞች ላይ እያንዳንዳቸው 20 ሽህ የማላዊ ክዋቻ እንዲከፍሉ ሲል የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በየነ። ከተፈረደባቸው ስደተኞች ውስጥ ከአንዱ በስተቀር የተቀሩት ሃያስድስቱም በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ናቸው። ስደተኞች ማክሰኞ እለት በሕገወጥ መንገድ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው ሲጓዋዙ ይጠቀሙበት ከነበረው ተሽከርካሪ ...
Read More »በሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ በጸና ታመዋል
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሙስና ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፋንታ በጸና መታመማቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ጥቅምት ወር፣ 2006 ዓም በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ፣ በተከሰሱበት ወንጀል እንዲከላከሉ ባለፈው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱ ይታወቃል። አቶ መላኩ ምንም አይነት ...
Read More »መንግስት ከፋ ዞን ቲፒ ወህኒ ቤትን በመስበር እስረኞችን ያስመለጡት ታጣቂዎችን በሽምግልና ካስገባ በኋላ ማሰሩ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) በደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን የቴፒ ወህኒ ቤትን በመስበር እስረኞችን ያስመለጡትን ታጣቂዎች መንግስት በሽምግልና ካስገባቸው በኋላ ወደ ወህኒ እንደወረዳቸው የአካባቢው ምንጮች ገለጹ። በከተማው ነዋሪ ላይ የሚፈጸመው ግፍና በደል መጠናከሩንም እነዚሁ ምንጮች አስታውቀዋል። ከሁለት አመት በፊት ሃሙስ ግንቦት 27/2007 ሌሊት በቴፒ ከተማ ወህኒ ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከመቶ በላይ እስረኞችን በማስፈታትና መሳሪያ በመንጠቅ ተመልሰው ጫካ የገቡት ታጣቂዎች ...
Read More »የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የብሉምበርግ የዜና ወኪልን ዘገባ በኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊው በኩል አጣጣለ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የብሉምበርግ የዜና ወኪል በሲምንቶ ምርት ላይ በኦሮሚያ ተሰማርቶ የነበረው ዳንጎቴ ሲምንቶ ፋብሪካ ከአስተዳደሩ እየደረሰበት ባለው ጫና ምክንያት ፋብሪካውን ዘግቶ ሊወጣ እንደሚችል ዘግቦ ነበር። የጽ/ቤት ሃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት አስተያየት “የብሉምበርግ የዜና ወኪል የሰራው ዘገባ መሰረታዊ የጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር ያልተከተለ የክልሉን መንግስት መልካም ስም ለማጉደፍ ሆን ተብሎ የተሰራ ተራ ፕሮፖጋንዳ ነው” በማለት አጣጥለውታል። አቶ አዲሱ አያይዘው ...
Read More »የአጋዚ ክ/ጦር በሰሜን ጎንደር መሳሪያ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ ግጭት አስከተለ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የአጋዚ ክፍለጦር አባላት በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ መሳሪያ ለማስፈታት ያደረጉት ሙከራ ወታደራዊ ግጭት አስከተለ። የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ሃሙስ ሰኔ 22/2009 በተካሄደ ግጭት 7 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ሶስት መቁሰላቸው ተመልክቷል። በነጻነት ሃይሎች በኩል ስለደረሰው ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም። ሐሙስ ሊነጋጋ ሲል በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የተንቀሳቀሱት የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ስለዘመቻው በቂ መረጃ በነበራቸው የነጻነት ...
Read More »የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የመቀሌ አቻው ለጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባለመገኘቱ ፎርፌ እንዲሰጠው ጥያቄ አቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለተመሳሳይ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመቀሌ አቻው ውድድር ሜዳ ላይ ባለመገኘቱ ፎርፌ እንዲሰጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጠየቀ። ክለቡ ከዚህ ቀደም በመቀሌ ከተማ ከዚሁ ቡድን ጋር በነበረው ጨዋታ በተፈጠረ ግጭት ውድድሩ ከተቋረጠ በኋላ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥፋተኛ ተብሎ ተጫዋቾቹና ቡድን መሪዎቹ በገንዘብ መቀጣታቸው ይታወቃል ። የባህር ዳር ከተማ ...
Read More »የአሜሪካው ጠ/ፍርድቤት የ6 እስልምና ዕምነት ተከታይ ሃገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክለውን ህግ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ ሰጠ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የአሜሪካው ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰኞ በወሰነው መሰረት በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዩች ካሉባቸው ስድስት አገሮች የሚመጡ ጎብኝዎች እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከሰኔ 29/2017 ምሽጥ 8 ሰአት ጀምሮ ወደ አገሪቱ መግባት እንደማይችሉ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አስታወቀ። ጎብኚዎቹ አሜሪካ የሚኖሩ የቅርብ ዘመድ ከሌላቸው ወይንም በአሜሪካ ከሚገኝ ድርጅት እና የትምህርት ተቋም ጋር የስራ ስምምነት ከሌላቸው ወደ ሃገሪቱ መግባት አይችሉም። የውጪ ጉዳይ ...
Read More »ለስራ ወደሩማንያ ከሄዱት የንግድ ም/ቤት አባላት ሰባቱ አለመመለሳቸው ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) ለስራ ከሃገር ከወጡ የንግድ ም/ቤት ልኡካን አባላት ሰባቱ ምስራቅ አውሮፓ ሩማንያ ውስጥ መቅረታቸው ተዘገበ። በግንቦት ወር ከ27 የንግድ ም/ቤት ልኡካን ጋር ወደ ቡካሬስት ሩማንያ የተጓዙት ሰባቱ ግለሰቦች ስለቀሩበት ምክንያት የተገለጸ ነገር ባይኖርም ከመካከላቸው አራቱ ወደ ጎረቤት ሃገር ሃንጋሪ ሲሻገሩ ድንበር አካባቢ መያዛቸው ተነግሯል። በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዝዳንት በአቶ ኤልያስ ገነቱ የተሰራውና ባለፈው ...
Read More »