ሰኔ 28/2009 በወላይታ ሲዳማ ዞን የተነሳው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ወደ ግጭት እንዳያመራ መንግስት እጁን ከጉዳዩ እንዲሰብስብና በሃገር ሽማግሌዎች እንዲፈታ ጥሪ ቀረበ ። በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር በውዝግቡ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የወላይታ ህዝብ የሲዳማን ህዝብ ጨምሮ ከሁለቱ ጎረቤቶቹ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖርን በማስታወስ አሁን የገጠመንም ችግር ከሲዳማ ህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲፈታው ያለውን እምነት ገልጿል ። የውዝግቡ መነሻ የሆነውንና አሁን ...
Read More »Author Archives: Central
በአማራ ክልል ስራቸውን የሚለቁ አመራሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው
ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የበላይነት በሚዘወረው ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ስራቸውን የሚለቁ የፖሊስ አዛዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ፣ እስካሁን ባለው መረጃ ከ21 በላይ ኮማንደሮች ስራቸውን ለቀዋል። ትናንት በነበረው ግምገማ በባህርዳር የጣና ክ/ከተማ ሃላፊ ኮ/ር በላይ ደምሴ ፣ የህዳር 11 ክ/ከተማ ሃላፊ ኮማንደር አልምነው አደመ፣ የበላይ ዘለቀ ክፍለከተማ ...
Read More »የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር መምህራኑን ለማስፈራራት እየሞከረ ነው
ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወረዳው መምህራን እንደሚሉት ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ ያለፈቃዳቸው 30 በመቶ ተቆርጦ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሊሰጥባቸው መሆኑን በመቃወም ፊርማቸውን አሰባስበው ካስገቡ በሁዋላ ፣ ሚስጢራችንን “ለጸረ ሰላም ሃይሎች አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል” በሚል ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው። መምህራኑ ማስፈራሪያውን ወደ ጎን በማለት አሁንም በአቋማቸው በመጽናት ጥያቄያችን ይመለስልን በማለት እየተጠየቁ ነው። በመጋቢት ወር መምህራኑ ...
Read More »በሃረር በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ በመደረጉ ህዝቡ ሲጉላላ ዋለ
ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ዛሬ ረቡዕ በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና አቶ አባይ ጸሃየ የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዘጋታቸው ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ሲንገላታ ውሎአል። መረጃዎቸ እንደሚያሳዩት አጠቃላይ የዝግጅቱን ሃላፊነት የወሰዱት ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ናቸው። አጠቃላይ ዝግጅቱ ለአንድ ...
Read More »የእንግሊዝ ፖሊስ በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ ክስ መሰረተ
ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ታደሰ ክስ የተሰመረተባቸው በጥር ወር ኤርትራ ቆይተው ወደ እንግሊዝ ሲገቡ፣ አየር ማረፊያ ላይ በተደረገው ፍተሻ አንዳንድ ጽሁፎችን ከዌብ ሳይት ላይ ወስደው ኮምፒተሮቻቸው ላይ አውርደውና ቦርሳቸው ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው ነው። ጽሁፎቹ በእንግሊዝ ፖሊሶች በጥርጣሬ መታየታቸውን ተከትሎ፣ ክስ እንደተመሰረተባቸው ታውቋል። ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲሞክራሲና የፍትህ ትግል ውስጥ በአርበኞች ...
Read More »ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ።
ኢሳት ሰኔ 27/2009 ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ። የኢሳት ዋና ዳይሬክተር አበበ ገላው ጉዳዩን በማስመልከት ለኢሳት በሰጠው መግለጫ አንዳስገነዘበው ህወሃት መራሹ መንግስት በከባድ ፈተና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ከመቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድቦ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ገልጿል። የህውሃት/ ...
Read More »241ኛው የአሜሪካ የነጻነት ቀን በዛሬው እለት ተከብሮ ዋለ
ኢሳት ሰኔ 27/2009 አስራ ሶስት የአሜሪካ ግዛቶች ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ ወጥተው ዩናይት ስቴት ኦፍ አሜሪካን የመሰረቱበት 241ኛው የአሜሪካ የነጻነት ቀን ማክሰኞ እለት በመላው አገሪቱ ተከብሮ ውሏል። እ.ኤ.አ በ July 4, 1776 የ13 ግዛቶች ተወካዮች በፔንሲልቬንያ ተሰባስበው ነበር። ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ መውጣታቸውንና እራሳቸውን የቻሉ ሉአላዊ ግዛቶች መሆናቸውንና በዚሁም ቀን ዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ መመስረቷን አወጁ። ዲክላሬሽን ኦፍ ኢንዲፔንደንስ የተሰኘውንም የአሜሪካን ነጻነት ...
Read More »ለቤት ግንባታ በአለም አቀፍ ጨረታ የተመዘገቡ የውጭ አገር ኩባንያዎች ወደ ስራ አለመግባታቸው ተገለጸ
ኢሳት ሰኔ 27/2009 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለቤት ግንባታ ባወጣው አለም አቀፍ ጨረታ 28 የሚጠጉ ደረጃ አንድ የውጭ ኮንትራክተሮች ተወዳድረው የተመረጡ ቢሆንም አንዳቸውም ወደ ስራ መግባት እንዳልቻሉ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ከዛሬ ሁለት አመት በፊት የኮንስትራክሽን ሚኒስትሩና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ በሰጡት የጋራ መግለጫ የውጭ ኮንትራክተሮችን በመኖሪያ ግንባታ ዘርፍ ለማሳተፍ ቅድመ-ዝግጅቱ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው በጥቂት ቀናት ወደ ...
Read More »የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ
ኢሳት ሰኔ 27/2009 የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ። 29ኛውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እየተካፈሉ ያሉት የሱማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ በቲውተር ገጻቸው የመረጃውን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል። የሱማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ሰኞ እለት እንደገለጹት ከሆነ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገባችው ስምምነት መሰረት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ተረክባለች። እስከ ኣስር አመት እና ከዚያ በላይ መታሰራቸው የተገለጸው እስረኞች በምን ...
Read More »የኪነጥበብ ሙያተኞች በሽብርተኝነት ተከሰሱ
ኢሳት ሰኔ 27/2009 ሰኔ 23 ቀን 2009 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት 5 አርቲስቶችን እና ተባባሪዎች ያላቸውን የሽብርና የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ሴና ሰለሞን፣ ኢፋ ገመቹ፣ ሃይሉ ነጮ፣ አሊያድ በቀለ እና ኤልያስ ክፍሉ የተባሉ አርቲስቶችና በግል ስራ እንደሚተዳደሩ የተገለጹ ቀነኒ ታምሩ እና ሞይቡሊ ምስጋኑ የቀረበባቸው ክስ ሁከትና አመጽ የሚያነሳሱ ዜናዎችን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተው በድምጽ በመቅረጽ ማሰራጨታቸው፤ ...
Read More »