(ኢሳት ዜና ሐምሌ 7/2009) በአዲስ አበባ በቡልጋሪያ ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው ብርሃን የኢትዮጵያ የባህል መአከል በህገወጥ መንገድ እየፈረሰ መሆኑ ተነግሯል። ማዕከሉ እንዲፈርስ የተፈለገው ከቦሌ ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስደው መንገድ መተላለፊያ በመሆኑ ነው ተብሏል ። መንገዱ ከተጀመረ ሁለት አመት ቢሆነውም የኢትዮጵያ የባህል ማዕከል ጉዳዩ ሳይነገራቸው ከአጥር ግቢው 5 ሜትር ያህል ፈርሶ እንዳገኙትና በህገወጥ መንገድ አፍራሽ ግብረሀይል እንደተላከባቸው ገልጸዋል። ማዕከሉ በ960 ስኩየር ሜትር ...
Read More »Author Archives: Central
የኦሮሚያ ነጋዴዎች ከሚያነሱት ጥያቄ ዘጠና በመቶው ከግንዛቤ እጥረት ጋር የተያያዘ ነው ተባለ።
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 7/2009) በኦሮሚያ ከቀን ገቢ ግምት ጋር ተያይዞ ነጋዴዎች ከሚያነሱት ጥያቄ ዘጠና በመቶው ከግንዛቤ እጥረት የተያያዘ መሆኑን የክልሉ ገቢዎች ዋና ዴሬክተር ገለፁ። የክልሉ ገቢዎች ዋና ዴሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ እንደገለፁት ከጥያቄዎቹ መካከል ሊታይ የሚገባው 10 በመቶ ብቻ ነው። የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ በጽ/ቤታቸው ለመንግስት፣ የድርጅትና የግል የሚዲያ ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኦሮሚያ የግብር ...
Read More »ግብጽ የህዳሴው ግድብ በውሃ መሞላት አልተጀመረም አለች
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 7/2009)በኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ እየተባለ የሚጠራው የኣባይ ግድብ መጋቢት 24/2003 ላይ የመሰረት ድንጋዩ ሲጣል 6 ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይልን ማመንጨት አላማው አድርጎ ነው። ከግድቡ ግንባታ መጀመር ጋር ተያይዞ ፍትሃዊ የሆነ የውሃ ክፍፍል ላይኖር ይችላል የሚለው ጥያቄ ደግሞ ከጎረቤት ሀገራት በተደጋጋሚ ይነሳ የነበረ ቅሬታ ነው። የኢትዮጵያ መንግስትም የግድቡ ግንባታ ማንንም የማይጎዳና ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግበት ሁኔታ መኖሩን በጥናት ...
Read More »የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት ኣቶ አማረ አረጋዊ የህይወት ዘመን እውቅና ተሸለሙ።
(ኢሳት ዜና- ሀምሌ 7/2009) የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል ከዋቢ የግል አሳታሚዎች ማህበር ጋር በመተባበር ለአቶ ክፍሌ ወዳጆ እና ለአቶ አማረ አረጋዊ የሕይወት ዘመን እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ኣቶ ክፍሌ ወዳጆ ሕገመንግስቱ ሲረቀቅ የሚዲያ ነጻነት በሀገሪቱ እንዲከበር ሚና ተጫውተዋል በሚል ከአቶ አማረ ጋር እውቅና ተስጥቷቸዋል። በእውቅና አሰጣጡ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተአማኒና ተፅዕኖ ፈጣሪ መገናኛ ብዙሃንን ለመገንባት ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ...
Read More »ከግብር ጋር በተያያዘ ነጋዴዎች የሚያሰሙት ተቃውሞ ቀጥሎአል
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ነጋዴዎች ተቃውሞቸውን በስብሰባ ቦታዎች ከመግልጽ አልፈው ወደ አደባባይ በመውጣት በማሰማት ላይ መሆናቸውን ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በአምቦ ትናንት ሃሙስ በተነሳው ተቃውሞ መኪኖች የተቃጠሉና የተሰባበሩ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ ደግሞ ከ3 ቀናት በፊት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በፈዲስ፣ ጭሮ ( አሰበ ተፈሪ)፣ ...
Read More »በቆላ ድባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ተሰማርተው በህዝቡ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወኪላችን እንደዘገበው ባለፉት ሁለት ቀናት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በቆላ ድባና በገጠር አካባቢዎች በሰማራት በህዝቡ ላይ ድብደባ ከመፈጸም ጀምሮ አንዳንዶችን ይዘው በማሰር ላይ ናቸው። ባለፈው አመት የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሳይቋረጥ ከቀጠለባቸው የሰሜን ጎንደር ከተሞች መካከል ቆላ ድባ አንዷ ስትሆን፣ በአካባቢው የሚካሄደውን የትጥቅ ትግል ተከትሎ አካባቢው አመቱን ሙሉ በውጥረት ...
Read More »በሶማሌ ክልል በዶሎ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በርሃብ ምክንያት 68 ሕጻናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው የርሃብ አደጋ ወደ አስጊ ደረጃ መሸጋገሩን እና በርሃብ ምክንያት ባለፈው ወር በሶማሌ ክልል በዶሎ ዞን 68 ታዳጊ ሕጻናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። በክልሉ ከድርቁ በተጨማሪ ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋዎች በመከሰታቸው የረድኤት ሥራውን ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል። በድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን በቀጠናው ላለፉት 12 ዓመታት በረድኤት አገልግሎት ሥራ ...
Read More »የአሜሪካና የሶማሊያ ወታደሮች በአልሸባብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገለጹ
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሃሙስ ጠዋት የአሜሪካና የሶማሊያ ጦር ሃይል በደቡብ ሶማሊያን በአልሸባብ ተይዞ በነበረ ቦታ ላይ በሰነዘሩት ድንገተኛ ጥቃት ብዙ የአልሸባብ ወታደሮችን ገድለዋል። የሶማሊ ኮማንዶዎች ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር በመሆን በሁለት ሄሊኮፕተሮች ተጉዘው ኩንያ ባሮ የሚባለውን የአልሸባብ እስር ቤት የሚገኝበትን ቦታ በመውረር በፈጸሙት ድንገተኛ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እስረኞች ተለቀዋል። ...
Read More »ጣና ሃይቅ በቆሻሻ ፍሳሽ እየተበከለ ነው
(ኢሳት ዜና-ሐምሌ 6/)2009 በአለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ የአለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የጣና ሃይቅ በእምቦጭ አረም መስፋፋት ምክንያት የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል።ከዚህ ባልተናነሰ ግን በባህር ዳር ከተማና በሃይቁ ዙሪያ የሚገኙ የአገልግሎትና መንግስታዊ ተቋማት ወደ ሃይቁ የሚለቁት ፍሳሽ ችግሩን እንዳባባሰው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከአማራ ክልል ምክር ቤት ህንጻ ፣ ከመስተዳድሩ የዘርፉ ቢሮዎች ፣ከ3 ሺ በላይ ታሳሪዎችን ከሚይዘው ወህኒ ቤት ፣ ፖሊ ቴክኒክን ...
Read More »የኢትዮጵያ የወርቅ ምርትና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ በእጅጉ በማሽቆልቆል ላይ መሆኑ ተነገረ::
(ኢሳት ዜና -ሐምሌ 6/2009) ኢትዮጵያ ከወጭ ንግድ ጋ በተያያዘ ከፍተኛ ገቢ ከምታገኝባቸው ዘርፎች አንዱ የወርቅ ንግዷ ነው። ከዘርፉ በአመት 350 ሚሊየን ዶላር ገቢም ታስገባለች። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2015 ባለው ጊዜ ብቻ 1 ነጠብ 9 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝታለች ብሏል ፎሩቹን ጋዜጣ በእትሙ። ይሄ ገቢ ሲታይ ግን ባለፉት አምስት አመታት ብቻ ከ19 በመቶ ወደ 10 በመቶ አሽቆልቁሏል። የማእድን፣ የነዳጅና ...
Read More »