Author Archives: Central

ኢርማ አውሎ ንፋስ ፍጥነቱን ቀንሶ ወደ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ ማምራቱ ተነገረ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 1/2010) በአሜሪካ የፍሎሪዳ ግዛትን የመታው ኢርማ አውሎ ንፋስ ፍጥነቱን ቀንሶ ወደ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ ማምራቱ ተነገረ። አውሎ ንፋሱ ከ3 እስከ 4 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎችን ከኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ውጪ አድርጓቸዋል። በአሁኑ ጊዜ 75 ማይል ወይም 150 ኪሎ ሜትር በሰአት እየተምዘገዘገ ያለው ኢርማ አውሎ ንፋስ ፍጥነቱን ቀንሶ አቅጣጫውን መቀየሩን በፍሎሪዳ ታምፓ የባህር ዳርቻ ከተማ የሚኖረው ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ለኢሳት ገልጿል። ...

Read More »

አሪክ የተባለው የናይጄሪያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከሰሰ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 1/2010) አሪክ የተባለው የናይጄሪያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳሳተ መግለጫ ደርሰብኝ ላለው ጉዳት 56 ሚሊየን ዶላር ይከፈለኝ ሲል በፍርድ ቤት ክስ አቀረበ። አየር መንገዱ ለናይጄሪያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባቀረበው የጉዳት ካሳ ክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴርና የናይጄሪያ አቃቢ ህግ ተጠያቂ እንደሆኑ አመልክቷል። 20 አንቀጾች ባለው የክስ አቤቱታ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የፌዴራሉ የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የአሪክ አየር ...

Read More »

የኢትዮጵያ አዲስ አመት በኢትዮጵያና በተለያዩ የአለም ክፍሎች በድምቀት ተከበረ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 1/2010)የኢትዮጵያ አዲስ አመት በኢትዮጵያና በተለያዩ የአለም ክፍሎች በድምቀት ተከበረ። አዲሱ አመት በልዩ ልዩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርአት ደምቆ መዋሉ የታወቀ ሲሆን በተለይ በዋዜማው የሙዚቃ ዝግጅቶች በልዩ ልዩ መድረኮች ለሕዝብ ቀርበዋል። በቅርቡ አዲሱን የሙዚቃ አልበሙን ለማስመረቅና ከማር እስከ ጧፍ በሚል የተቀነባበረውን ክሊፑን ለመልቀቅ በሒልተን ሆቴል የተጠራው ፕሮግራም በመንግስት የተሰረዘበት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ለአዲሱ አመት ከማር እስከ ጧፍ የሚለውን የሙዚቃ ክሊፕ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የመከራ ዘመን እንዲያበቃ፣ፍቅርና አንድነት እንዲታወጅ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 1/2010)የኢትዮጵያ የመከራ ዘመን እንዲያበቃ፣ፍቅርና አንድነት እንዲታወጅ በውጭ የሚኖሩ አባቶች ጥሪ አቀረቡ። የኢትዮጵያን አዲስ አመት 2010 በማስመልከት በሐገር ቤትና ከሐገር ውጭ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ሰባኪያን የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ እንዲሁም የፈርስት ሒጅራ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ሐጂ ነጂብ መሀመድና የፈርስት ሒጅራ ፋውንዴሽን ኢማም ሼህ ካሊድ ኡመር ፣የአዲስ ኪዳን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ...

Read More »

የሜክሲኮ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ በርእደ መሬት ተመታ

(ኢሳት ዜና –ጳጉሜ 3/2009) የሜክሲኮ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ በሪክተር ስኬል 8 ነጥብ 2 በተመዘገበ ርእደ መሬት ተመታች። በሀገሪቱ የመቶ አመት ታሪክ ውስጥ በከባድነት በተመዘገበው በዚህ ርእደ መሬት እስካሁን 33 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የአደጋ ጊዜ ኤጀንሲ ሃሪኬን ኢርማ ፍሎሪዳን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጉረቤት አካባቢዎችንም ሊያጠፋ ይችላል ሲል ማስጠንቀቂያውን ሰጥቷል። የሜክሲኮን ደቡባዊ የባህር ዳርቻን የመታው ርእደ መሬት በመቶ አመት ...

Read More »

ብአዴን የአማራ ግጨው ሁለት መንደሮችን ለትግራይ አስረክቦ በራሱ ግዛት ያለን የእርሻ መሬት ቦታ አገኘሁ ማለቱ ታሪካዊ ስህተት መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 3/2009)የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ የአማራ ግጨው ሁለት መንደሮችን ለትግራይ አስረክቦ በራሱ ግዛት ያለን የእርሻ መሬት ቦታ አገኘሁ ማለቱ ታሪካዊ ስህተት መሆኑን በአካባቢው የመሬት አስተዳደር ባለስልጣን የነበሩ ሰው ገለጹ። በአማራና በትግራይ ክልሎች ርእሰ መስተዳድሮች ስምምነት ለትግራይ የተሰጡት የግጨውና የጎቤ መንደሮች ከዚህ ቀደም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካኝነት በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ የአካባቢው ሕዝብ አማራ ነን በማለቱ ውሳኔ አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ...

Read More »

በእሬቻ በአል በግፍ ለተገደሉት ሰዎች በአገዛዙ የቆመው የሰማእታት ሀውልት እንዲነሳ ኦፌኮ ጠየቀ

(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 3/2009) በእሬቻ በአል በግፍ ለተገደሉት ሰዎች በአገዛዙ የቆመው የሰማእታት ሀውልት እንዲነሳ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ጠየቀ። ኦፌኮ የእሬቻ በአል መቃረብን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሰማእታት ሀውልት ችግሩን ባደረሱትና ተጠያቂ ሊሆኑ በሚገባቸው አካላት መገንባቱ ከመሰረቱ ትክክል አይደለም። ከመንግስት የሚጠበቀው የሟቾችን ማንነት በገለልተኛ አካል ይፋ ማድረግና የደም ካሳ ወይም ጉማ መክፈል እንዲሁም ገዳዮቹን ለፍርድ ማቅረብ ነው ብሏል።ኦፌኮ በመግለጫው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ መግለጫ ...

Read More »

የኦብነግ አመራር አባልን የሶማሊያ መንግስት አሳልፎ መስጠቱ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 3/2009) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/አመራር አባል አብዲካሪን ሼህ ሙሴን የሶማሊያ መንግስት አሳልፎ መስጠቱ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ሲል አፍሪካ ራይትስ ሞኒተር አወገዘ። በጄኔቫ አውሮፓ የሚገኘው አፍሪካ ራይትስ ሞኒተር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኦብነጉ መሪ ያለፍላጎታቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1954 የወጣውን የተባበሩት መንግስታት ስምምነት የሚጣረስ ነው። አፍሪካን ራይትስ ሞኒተር በመግለጫው እንዳመለከተው የኢትዮጵያው አገዛዝ የሰዎች ...

Read More »

ኦህዴድ የውስጠ ድርጅት ቀውስ ውስጥ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009) በዘርፈ ብዙ ግጭቶችና ህዝብ ተቃውሞ እየታመሰ ያለው ኦህዴድ የውስጠ ድርጅት ቀውስ ውስጥ መሆኑ ተገለጸ። ባለፉት ተከታታይ ወራት የስርአት ለውጥ በሚጠይቁ ዜጎች ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠመው የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ከድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ጀምሮ የ18 ከፍተኛ ባለስልጣናትና ካድሬዎች ለውጥ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወሃት ወታደራዊ አዛዦች በሚመራው የሱማሌ ልዩ ፖሊስና በኦሮሚያ ህዝብ መካከል እየተካሄደ ...

Read More »

ህዝቡ ስለወልቃይት ማንነት የተጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ተደረገ

(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009)በግጨው የድንበር ወሰን ላይ ከስምምነት ደርሰናል በሚል በብአዴንና ህውሀት መሪዎች በተሰጠው መግለጫ ህዝቡ ሳይዘናጋ ስለወልቃይት ማንነት የተጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ተደረገ። ልሳነ ግፉአን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ማህበረሰብ ለኢሳት እንደገለጸው የትግራይ ገዢ ቡድን አሸናፊ ሆኖ የወጣበትን ስምምነት የአማራውም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል። ትላንት የሁለቱ ድርጅቶች መሪዎች አጨቃጭቆናል ባሉት የግጨው የወሰን ጉዳይ ላይ ስምምነት መድረሳቸውን ያስታወቁ ሲሆን ...

Read More »