(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) በ110 የጭነት መኪናዎች ተጭኖ ወደ ኬንያ ሊገባ የነበረው 44 ሺ ኩንታል ስኳር ከ2 ወራት የሞያሌ ቆይታ በኋላ ለብልሽት ተዳርጎ ወደ ወንጂ በመመለስ ላይ መሆኑ ተነገረ። እስካሁን 44 የጭነት መኪናዎች ስኳሩን እንደጫኑ ናዝሬት ገብተዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ስኳሩን ዱባይ ለሚገኘው አግሪ ኮሞዲቲ የተባለ ኩባንያ የሸጠው በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የስኳር እጥረት ባለበት ሁኔታ ነው። ስኳሩን ኬንያ ለማድረስ ተዋውሎ ሞያሌ ...
Read More »Author Archives: Central
የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም 15 በመቶ እንዲቀንስ ተወሰነ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም 15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰኑ ከነገ ጥቅምት 1/2010 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለጸ። በዚህም አንድ የአሜሪካን ዶላር በ27 የኢትዮጵያ ብር እንደሚመነዘር ተመልክቷል። የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መስከረም 29/2010 ሲጀምር ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መወሰኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም ኤክስፖርትን ለማበረታታት ታልሞ መሆኑን በንግግራቸው ቢጠቅሱም ርምጃው ግን የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል ...
Read More »ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ ይደረጋል አሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ እንደሚደረግ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ የሚደረገው ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ነው ብለዋል። መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደገጠመውም ፕሬዝዳንቱ በይፋ ተናግረዋል። እንደ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ገለጻ በኢትዮጵያ ላለፉት 3 አመታት በነበረው የውጭ ምርቶች መላክ መዳከምና ከዚህ ጋር ...
Read More »በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው ታገደ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው መታገዱ ተሰማ። የአባይ ዋንጫ በዙር ጭኮ ወረዳ መግባቱን ተከትሎ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ከደመወዙ ከ300 ብር ጀምሮ እንዲያዋጣ መመሪያ ተወስኖበታል። የሴክተር መስሪያ ቤቶች ያለፈቃዳቸው እንደተስማሙ ተደርጎ የተቆረጠባቸው ሲሆን መምህራን ተቃውሞ በማንሳታቸው የመስከረም ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው አራት ቀናት መቆጠሩን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መምህራኑ ደሞዛችን ካልተከፈለን አንሰራም በማለት ዛሬ ስራ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የፌደራል መንግስት የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው በሚል ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በኦሮሚያ ጥቃት ላይ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር የተደረገ የጋራ መግለጫ በሚል ያወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚቃረን ነው። እናም የሚመለከተው አካል ይህንኑ ...
Read More »አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የአፈጉባኤነት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመተው መልቀቂያ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸውን ምንጮች ገለጹ። ዛሬ በፓርላማ በመደበኛ ስራቸው ላይ የታዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውንም ትላንት አረጋግጠዋል። ላለፉት አስር አመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤነት የቆዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከኦሮሚያና ከሶማሌው አዋሳኝ ድንበር ግጭት ጋር በተያያዘ የጸጥታ ሃይሉ ሚና እንዳላስደሰታቸውና ስልጣን ለመልቀቅም ምክንያት እንደሆናቸው አዲስ ስታንዳርድ ...
Read More »ታዋቂው የባህል ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010)ታዋቂው የባህል ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ ከዚህ አለም በሞት የተለየው በደረሰበት የመኪና አደጋ ነው። ሀብተሚካኤል ደምሴ በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢ ከሚያሽከረክረው መኪናው ወርዶ መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገጭቶ ሕይወቱ አልፏል። አደጋው የደረሰበት ዛሬ ሰኞ ከረፋዱ 4 ሰአት አካባቢ ነው። ከዚህ አለም ...
Read More »በኢትዮጵያ የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010)በኢትዮጵያ ባለፉት 26 አመታት የተተገበረው የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ታዋቂው የአለም አቀፍ መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ዘገበ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የብሔር ግጭት የዳሰሰው ዘኢኮኖሚስት የክልል መንግስታት በፌደራል መንግስት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቢሆንም ከእጅ እያመለጡ ናቸው ብሏል። እናም የሕዝቡን አንድነት በማዳከም የጎሳ ፖለቲካን ሲያራምድ የቆየው የኢትዮጵያው አገዛዝ የማይወጣው ችግር ውስጥ እያስገባው መሆኑን ዘ ኢኮኖሚስት በሀተታው ዘርዝሯል። ...
Read More »አንድ ጄኔራል የህወሃት አገዛዝን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አንድ ጄኔራል ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ የተባሉ ከፍተኛ መኮንን ናቸው። ከወር በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዘጋጅነት በዋሽንግተን በተካሄደ ጸረ አይ ሲስ አለም አቀፍ ዘመቻ ላይ ከተገኙ የኢትዮጵያ ልኡካን አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ ...
Read More »የኒዩክለር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አለም አቀፍ ዘመቻ የተባለው ድርጅት የ2017 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፈ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) የኒዩክለር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አለም አቀፍ ዘመቻ የተባለ ድርጅት የዘንድሮውን የ2017 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፈ። በምህጻረ ቃል ኢካን ተብሎ የሚታወቀው አለም አቀፍ ተቋም የዘንድሮው የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆነው የኒዩክለር አደጋ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ለአለም አደጋ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ነው። እናም ተቋሙ የጸረ ኒዩክለር ስምምነት እንዲኖር ላደረገው ጥረት ሽልማቱን ማግኘቱ ታውቋል። የኖቤል ሽልማቱን ያገኘው ተቋም በአውስትራሊያ ተመስርቶ በአሁኑ ...
Read More »