Author Archives: Central

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መታቀዱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) ሰነድ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ በፈቃደኝነትም ሆነ በማስገደድ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የአውሮፓ ሕብረትና የኢትዮጵያ አገዛዝ መስማማታቸውን አፈትልኮ የወጣ አንድ ሰነድ አመለከተ። በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ስደተኞችን ከአውሮፓ ወደ ሀገራቸው በግዳጅ ለመመለስ ሙሉ ትብብር ያደርጋል። ስደተኞቹ ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ ፓስፖርት ባይዙ እንኳን የደህንነት መስሪያ ቤቱ ማንነታቸውን ካረጋገጠ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የጉዞ ሰነድ ...

Read More »

አቶ አባይ ወልዱን ከክልል ፕሬዝዳንትነት የማንሳት ጉዳይ ተቃውሞ ገጠመው

(ኢሳት ዜና –ሕዳር 28/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አባይ ወልዱን ከትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትነት ለማንሳት የሚደረገው ሙከራ ተቃውሞ እንደገጠመው ምንጮች ገለጹ። ለተቃውሞ ምክንያት የሆነውም የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከልጣናቸው ሳይወርዱ አቶ አባይ ወልዱ መነሳት የለባቸውም በሚል እንደሆነም ታውቋል። በዚህ ሳቢያ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በቅድሚያ ለማውረድ በሕወሃት ጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ብአዴን ...

Read More »

በአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊላክ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ በማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ የልዑካን ቡድንን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ መዘጋጀቱ ታወቀ። ተቋሙ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልከው በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኢኮኖሚው ሁኔታ እያሳሰበው በመምጣቱ መሆኑ ታውቋል። የሀገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ምንዛሪ ወደ 700 ሚሊየን ዶላር የወረደ ሲሆን በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት በጅቡቲ የተከማቹ እቃዎችን ማንሳት እንዳልተቻለም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በወጭ ንግድ ...

Read More »

አሜሪካ ለኢየሩሳሌም እውቅና ሰጠች

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን እውቅና ሰጡ ። ይህን ተከትሎም የአረብ ሀገራት መሪዎች የፕሬዝዳንት ትራምፕን ርምጃ ሲያወግዙ የካቶሊካውያኑ ሊቀጳጳስ ኢየሩሳሌም የሁሉም ነች በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በጉዳዩ ላይ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት እንደሚያነጋግሩ አስታውቀዋል። አሜሪካ ቴል አቪቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዛወር መወሰኗንም ሆነ ለኢየሩሳሌም ዋና ከተማ የሰጡትን እውቅና የፍልስጤማውያኑ ፕሬዝዳንት ...

Read More »

ነባርና ታሪካዊ አካባቢዎችን ማፍረስ ተጀመረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነባርና ታሪካዊ አካባቢዎችን ማፍረስ ጀመረ። ገዳም ሰፈርና ጌጃ ሰፈርን ጨምሮ አምስት ነባር ሰፈሮች ሙሉ ለሙሉ ይፈርሳሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 ከያዘው ከ40 ቢሊየን ብር አመታዊ በጀት ውስጥ 30 ቢሊየን ብሩን ከማዘጋጃ ቤትና ግብር ነክ ገቢዎችን ከሕብረተሰቡ በቀጥታ የሚሰበስበው መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ገቢ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻውን የያዘው ነባር መሬቶችን በማስለቀቅ መሬቱን በመሸጥ የሚያገኘው ...

Read More »

ሕወሃት የተቋማትን ኮምፒዩተሮች ይሰልላል

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የሕወሃት የስለላ ተቋማት አንድ በእስራኤል የሚገኝ ድርጅት የሚያቀርበውን የስለላ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን፣አንድ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪንና የአንድ ጠበቃን ኮምፒዩተሮች ሲሰልል እንደነበር ሲትዝን ላብ የተባለው ተቋም አጋለጠ። በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ፣በግለሰቦችና ሌሎች ድርጅቶች ላይም የስለላ ተግባር መፈጸሙ ተጋልጧል። በሲትዝን ላብ የሚገኝ አንድ ግለሰብም የጥቃቱ ሰለባ መሆኑ ታውቋል። ሲትዝን ላብ እንደ ሕወሃት ያሉ አምባገነን ...

Read More »

እስረኞች ከፍተኛ ማሰቃየት እየተፈጸመባቸው ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) በፖለቲካ ምክንያት ታስረው በወህኒ ቤት የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ማሰቃየት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። ከጊዜያዊ ህመም እስከ ዘላቂ የአካል ጉዳት የደረሰ ቅጣት እንደሚፈጸምባቸውም እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የሚፈጸሙና አሰቃቂ የሚባሉት ድርጊቶች ችሎት ፊት ሲቀርቡ ምናልባትም የህግ ባለሙያዎች መቀለጃ ወይንም የበለጠ ቅጣትን ማክበጃ ተደርገው ይወሰዳሉ። እንዲህ አይነቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚፈጸመው ደግሞ ምንም አይነት ወንጀል በሌለባቸው፣ወንጀል ሰርተው ...

Read More »

አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ ተቃጠለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) በሰሜን ጎንደር አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ ተቃጠለ። በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር አካባቢ ኳቤር ሎምዬ ቀበሌ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ዛሬ ጠዋት የተቃጠለ ሲሆን፣  አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ለጥቃቱ ሃልፊነቱን ወስዷል። ነዳጁ ለአጋዚ ጦር የታሰበ በመሆኑ ርምጃውን መውሰዱን ንቅናቄው አስታውቋል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነዳጅ የጫነ ቦቴ መቃጠሉን አረጋግጠው ቦቴው የጋየው ከዘራፊዎች ጋር በተደረገ ...

Read More »

በ8 ሀገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ ሕግ ጸደቀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ሕግ አጸደቀ። ውሳኔው ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ሲታወቅ በሁለት ግዛቶች የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ለመቀልበስ ክርክር በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ባለፈው መስከረም ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበውን የጉዞ እገዳ ሕግ ሙሉ ለሙሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሲያጸድቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ...

Read More »

የኢሳት 7ኛ አመት በቦስተንና ሂውስተን ተከበረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010)  የኢሳት 7ኛ አመት በቦስተንና ሂውስተን ከተማ በድምቀት ተከበረ። የበአሉ ተሳታፊዎች ኢሳት የሚያደርገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያለማቋረጥ ድጋፋችንን እናደርጋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 2/2017 በሰሜን አሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት ቦስተን ከተማና ቴክሳስ ግዛት ሂውስተን ከተማ የኢሳት 7ኛ አመት በርካታ የኢሳት ደጋፊዎች በተገኙበት ተከብሯል። ለኢሳት ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በእለቱ ተካሂዷል። በቴክሳስ ሂውስተን በተካሄደው ዝግጅት ላይ ላለፉት ...

Read More »