(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) ሕጻናትን ጨምሮ 8 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ መጠለያ ካምፕ ጋምቤላ ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። ሬዲዮ ታማዙጅ የተባለ ጣቢያ ከሱዳን እንደዘገበው ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ የሙርሌ ጎሳ አባላት የሆኑ ሱዳናውያን ዲማ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። የካምፑ የስራ ሃላፊ አንድሪው ካካ እንዳረጋገጡትም ከትላንት በስትያ ታህሳስ 17 ለሊት ላይ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ተኩስ ተከፍቶ 8ቱ ሰዎች ተገድለዋል። ከስምንቱ የሙርሊ ...
Read More »Author Archives: Central
የሀውቲ አማጽያን ላይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 68 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) በሳውዲ የሚመራው ጥምር ጦር በየመን የሀውቲ አማጽያን ላይ በፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 68 ሰላማዊ ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ መገደላቸው ታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጎ አድራጎት አስተባባሪ እንደሚሉት ማክሰኞ ዕለት በተከታታይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት በአንድ የገበያ ቦታ ላይ በተፈጸመው የመጀመሪያ ጥቃት 54 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በሁለተኛው ጥቃት ደግሞ 14 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የተባበሩት መንግስታት የበጎ አድራጎት ማስተባበሪያ ሃላፊ ...
Read More »ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ስራዎቹን አስመራ ላይ ማቅረብ እፈልጋለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በኤርትራ መዲና አስመራ የሙዚቃ ስራዎቹን ማቅረብ እንደሚፈልግ ገለጸ። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤ ኤፍ ፒ ቃለመጠይቅ የሰጠው ቴዲ አፍሮ በአስመራ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚፈልግ አስታውቋል። በሌላ በኩል ለመጪው የኢትዮጵያ የገና በዓል በአዲስ አበባ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ የአገዛዙን ፈቃድ በመጠበቅ ላይ መሆኑንም ኤ ኤፍ ፒ በዘገባው አመልክቷል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ...
Read More »የማላዊ ባለስልጣናት ስምምነቱን አጣጣሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) በኢትዮጵያ አየር መንገድና በማላዊ አየር መንገድ መካከል የተፈጸመው የንግድ ሽርክና እርባና የሌለውና የማይጠቅም ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ስምምነቱን አጣጣሉ። የማላዊ መንግስት ባለስልጣናትና የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ሁለቱ አየር መንገዶች የሽርክና ስምምነት ከመረመሩ በኋላ ጉዳዩ አዋጭ እንዳልሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ አቻው ጋር ባካሄደው የንግድ ሽርክና ስምምነት 49 በመቶ ድርሻ በመያዝ የትርፍ ተከፋይ ለመሆን ነው። የ51 በመቶ ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል ባላስልጣናት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠየቁ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) አቶ በቀለ ገርባ ለምስክርነት የጠሯቸው የኦሮሚያ ክልል ባላስልጣናት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ጥያቄውን ያቀረቡት በድርጅታቸው ኦህዴድ በኩል መሆኑ ታውቋል። በሚሰጣቸው ተለዋጭ ቀጠሮም በችሎት ቀርበው ምስክርነት እንደሚሰጡም ለፍርድ ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል። ከኦህዴድ ጽሕፈት ቤት ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 18/2010 በተጻፈው ደብዳቤ እንደተመለከተው አቶ በቀለ ገርባ በምስክርነት የጠሯቸው የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ...
Read More »ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ የተከሰተው የህዝብ ፍጅት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ የተከሰተው የህዝብ ፍጅት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። መለዮ ለባሽም መሳሪያውን ከሕዝብ ላይ እንዲያነሳ የጠየቀው ቅዱስ ሲኖዶስ የሀገሪቱን ቀውስ ለመፍታት የአደራ መንግስትም እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል። በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ “በሀገር ውስጥና በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን ለምትወዱ ወገኖቻችን” በሚል ርዕስ ጥሪውን አቅርቧል። ሲኖዶሱ ...
Read More »አብያተ ክርስቲያናት ስደተኞችን በማስጠለል ላይ ናቸው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በአሜሪካ የሚገኙ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ስደተኞችን በማስጠለል ላይ መሆናቸው ታወቀ። አብያተክርስቲያናቱ ስደተኞቹን እያስጠለሉ ያሉት የትራምፕ አስተዳደር ሕገወጥ የሚላቸውን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ስራ በማጠናከሩ ነው። ቢያንስ 32 የሚሆኑ አብያተክርስቲያናት በራቸውን ለስደተኞች ክፍት በማድረግ ስደተኞቹን ከመባረር በመታደግ ላይ ናቸው። የአሜሪካ የስደተኞችና ጉምሩክ ሕግ አስከባሪ መስሪያ ቤት ፖሊሲ በአብያተክርስቲያናት ፣በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሕክምና ተቋማት ፍተሻ ማካሄድን አይፈቅድም። በመሆኑም የመኖሪያ ...
Read More »አቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ አህመድ ፍርድ ቤት ቀርበው ሊመሰክሩ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ አህመድ ፍርድ ቤት ቀርበው ሊመሰክሩ እንደሚችሉ ተገለፀ። ባለስልጣናቱን በአካል አግኝቼ አነጋግሬያቸዋለሁ ያሉት የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሌሎችም በችሎት ተገኝተው ሊመሰክሩ እንደሚችሉ ገልጸውላቸዋል። በሌላ በኩል የበቀለ ገርባ የመከላከያ ምስክር የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ በከባድ ወንጀል የተከሰሱ ናቸው በሚል ማረሚያ ቤቱ ችሎት አላቀርብም ማለቱ ...
Read More »በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ በመካሄድ ላይ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ለማስታወስ በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። በቲውተርና በፌስቡክ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ሆነዋል። በየእስር ቤቱ በስቃይ ላይ የሚገኙትንና በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ፎቶግራፎች በመለጠፍና ስቃያቸውን በመዘርዘር ትኩረት እንዲያገኝ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ዘመቻውን የሚያስተባብሩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦች እንደሆኑም ታውቋል። ዛሬ ፌስቡኩ በኢትዮጵያውያን አንድ ...
Read More »የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተለየ ክትትልና ወከባ እየተፈጸመ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመጽ ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተለየ ክትትልና ወከባ እየተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ። በየመኝታ ክፍሉ ደህንነቶች እየገቡ ተማሪዎችን እንደሚያስፈራሩም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሰኞ ከዩኒቨርስቲው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎችም የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም። ኢሳት ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ሰኞ ታቅዶ የነበረውና የተወሰኑ ተማሪዎች መታሰራቸውን ተከትሎ በግቢው ውስጥ ብዛት ያለው ሲቪል ...
Read More »