(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) ነባር አመራሮችን ጨምሮ የድርጅቱን ሕልውና እየገመገመ ያለው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በተንጠባጠበ ሁኔታ ሲካሄድ ቆይቶ መቋረጡ ታወቀ። በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው 22 አባላት ሕወሃት ባስቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት በጥልቅ ተሃድሶው አፈጻጸም ላይ ውይይት ቢጀምሩም በወልዲያና በቆቦ የተፈጸመው ጅምላ ግድያ በመካከላቸው መከፋፈልን ፈጥሯል። የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቶ አዲሱ ለገሰና በአቶ በረከት ስምኦን አቅጣጫ ሰጭነት ለክልልና ለተወካዮች ምክር ቤት የማሟያ ምርጫ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለውን ግድያ የሃይማኖት ተቋማት አወገዙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በወልዲያና በቆቦ በኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለውን ግድያ በማውገዝ የሃይማኖት ተቋማት መግለጫ አወጡ። በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየአብያተክርስቲያናቱ ለሟቾች ጸሎተ ፍትሃት እንዲደረግ ወስኗል። ለመከላከያ ሰራዊቱም ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የወሎ ሕዝብ እየከፈለ ላለው መሽዋዕትነት አክብሮቱን ገልጿል። አለም አቀፍ የክርስቲያን ኢትዮጵያውያን እህቶች ህብረትም ንጹሃንን የገደሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲል ባወጣው መግለጫ ...
Read More »የቃና ዘገሊላ በአል ላይ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገኝ ከስምምነት ተደርሶ ነበር
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በወልዲያ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በአል ላይ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገኝ ከተስማማን በኋላ ሰራዊቱ በበአሉ ስፍራ መገኘቱ ለግጭቱ መከሰት ምክንያት መሆኑን ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ ገለጹ። ሆን ተብሎ የታቀደ ይመስላል ሲሉም ሲሉም ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። የሰሜን ወሎና ከሚሴ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ ከግድያው ባሻገር ለንብረት ውድመቱም ምክንያት የሆነው የመከላከያ ሰራዊቱ መግባት እንደሆነ መናገራቸውን ሃራ ተዋህዶ ዘግቧል። ...
Read More »በቆቦ ህዝባዊ አመጹ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በሰሜን ወሎ ቆቦ የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉ ተገለጸ። የአጋዚ ወታደሮች ከተማዋን በማጥለቅለቅ ህዝቡ ላይ ጥቃቱን አጠናክረው ቀጥለዋል። የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ወድመዋል። ዛሬም በቆቦ ሰማይ ሄሊኮፕተር ሲመላለስ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ። በሆስፒታል አድራሻቸው ያልታወቀ አስከሬኖች እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። በቆቦ አቅራቢያ በምትገኘው ሮቢትም የህዝብ አመጽ መነሳቱ ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊትን ግስጋሴ ለመግታት መንገዶች ተዘግተዋል። ህዝቡ በመንግስት ተቋማትና በአገዛዙ ደጋፊና ...
Read More »ነብይ ነኝ ባዩ ናይጄሪያዊ በቁጥጥር ስር ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) ነብይ ነኝ ባዩ ናይጄሪያዊ አደንዛዥ እጽ ሲያዘዋውር በቁጥጥር ስር መዋሉን የዛምቢያ ፖሊስ ገለጸ። የ42 አመቱ ናይጄሪያዊ አይዛክ ጁልየስ አማታ በዛምቢያ ርዕሰ መዲና ሉሳካ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ መሆኑ ታውቋል። 26 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እጽ እንደተገኘበትም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። ሉሳካ ኬኔት ካውንዳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው አይዛክ ኦማታ ወደ እስር ቤት መወሰዱም ታውቋል። በእጽ አዘዋዋሪነትም እንደሚከሰስ ...
Read More »ጊዜያዊ የትምህርት ማቋረጥ የጠየቁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ አይመለሱም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጊዜያዊ የትምህርት ማቋረጥ(ዊዝድሮዋል) የጠየቁ ተማሪዎች የመልሶ ቅበላ እንደማይፈቀድላቸው የመንግስት ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ ዊዝድሮዋል መሙላት ቴክኒካል ጉዳይ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። የመንግስት ቃል አቀባዩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ በጽሕፈት ቤታቸው ለመንግስት፣ለፓርቲና ለግል መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጊዜያዊ ትምህርት ማቋረጥ(ዊዝድሮዋል) መሙላት አይችሉም ሲሉ ተደምጠዋል። ቃል አቀባዩ በ2010 ጊዜያዊ ማቋረጥን መሙላት ...
Read More »የኦሮሞ ሕዝብ ለምን ተበደለ ተብሎ መዘገቡ ትክክል አይደል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ለምን ተበደለ፣ጥቅምስ ለምን ቀረበት በሚል ኦቢኤን ቴሌቪዥን መዘገቡ አግባብ አይደለም ሲሉ የብሮድካስት ባለስልጣን አቶ ዘርአይ አስገዶም ገለጹ። አቶ ዘርአይ የክልልና የግል መገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች በተገኙበት መድረክ እንዳሉት ቴዲ አፍሮ ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ ሲያውለበልብ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በፌስቡክ ገጻቸው ድጋፍ ሰጥተዋልም ብለዋል። የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ ኦቢኤን በድምጻዊ አጫሉ ሁንዴሳ በኩል ወጣቶች ቤተመንግስት እንዲገቡ ...
Read More »ሰላም ባስ የጎዞ መስመሩን ለሁለተኛ ጊዜ ቀየረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በወልዲያ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ የቀየረውን የጎዞ መስመር በአፋር ክልል በገጠመው የጸጥታ ችግር እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለመቀየር መገደዱን አስታወቀ። በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ ግዴታ ስለሆነበት የታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ጥር 15/2010 “ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን” በሚል ያወጣው ማስታወቂያ ከአዲስ አበባ መቀሌና ...
Read More »በቆቦ ህዝባዊው ተቃውሞ ተባብሶ ቀጠለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) በሰሜን ወሎ ቆቦ ትላንት የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ዛሬ ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ። የአጋዚ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ 9 ሰዎች መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አንድ የአጋዚ ወታደርም መገደሉ ታውቋል። ህዝቡ ራሱን ለመከላከል ከዘመተበት የህወሃት ጦር ጋር መጋጠሙ ይነገራል። ከህወሃትና ብአዴን ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ንብረቶች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ፍርድ ቤት፣ 4 ቀበሌዎች መቃጠላቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ለኢሳት ...
Read More »በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከ7 በላይ ተማሪዎች መጎዳታቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) በደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ ግጭት ከ7 በላይ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግጭቱ ብሔርን መሰረት አድርጎ መቀስቀሱን ዘገባዎች አመልክተዋል። ዩኒቨርስቲው ግጭቱን ለማርገብና ለመቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ማቋቋሙ ታውቋል። በሆሳዕና ከተማ ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ብሔርን መሰረት ያደረገ ግጭት በመፈጠሩ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እስከመውጣት ደርሰዋል። የችግሩ መንስኤ በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የተነሳ ነው ቢባልም ቀደም ብሎም ፖለቲካዊ ...
Read More »