በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ የደህንነት ተቋማቱን ማስጨነቁን ምንጮች ገለጹ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ለ7 ቀናት በወልቂጤና ሌሎችም የጉራጌ ከተሞች የተካሄደው የስራ ማቆም አድማና የአደባባይ ላይ ተቃውሞ ለአገዛዙ የደህንነት አባላት ፈተና ሆኖ መሰንበቱን ምንጮች ገለጹ። ተቃውሞውን ለማስቆም የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የነበሩ የደህንነት አባላት፣ የተጠቀሙባቸው ዘዴዎች ሁሉ ባለመስራታቸውና አድማው አዲስ አበባ ባሉ የጉራጌ ተወላጆች ዘንድም ተግባራዊ ሊሆን ...
Read More »Author Archives: Central
የክልል መንግስታት በጸጥታ ጉዳይ መግለጫ እንዳይሰጡ ታገዱ
የክልል መንግስታት በጸጥታ ጉዳይ መግለጫ እንዳይሰጡ ታገዱ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የአዋጁን ተግባራዊነት ከሚከታተለው እዝ ውጭ ማንኛውም የክልል ባለስልጣን በክልሉ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይችል አግዷል። ከዚህ ቀደም የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የኮሚኔከሽን ሃላፊዎች እንዲሁም የዞን የጸጥታ ባለስልጣናት ሳይቀሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሚወስዱት እርምጃ ላይ መግለጫዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል። የኦሮምያ ክልል ...
Read More »አራት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላትና በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው የታሰሩ ሁለት ኮሎኔሎች ተፈቱ
አራት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላትና በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው የታሰሩ ሁለት ኮሎኔሎች ተፈቱ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ በማዋቀር፣ የማንነት መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩት አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ ጌታቸው አደመ እና አቶ ተሻገር ወልደሚካኤል ዛሬ ክሳቸው ተቋርጦ ተፈትተዋል። ሰሞኑን በጎንደር እስር ቤት የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ...
Read More »ሁለት የእርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2010) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት የዕርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ። የፈረንሣይ መንግሥታዊ ያለሆነ ተቋም ሃይድሮሊክ ሣን ፍሮንቴይር ባልደረባ የነበሩት ሀለቱ ግለሠቦች የተገደሉት ባለፈው ቅጻሜ መሆኑ ታውቋል። የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም። በምሥራቃዊ የኮንጎ ኪቩ በተባለው ግዛት የተገደሉት ሁለቱ የዕርዳታ ድርጅት ሰራተኞች በስምና በዜግነት አለመገለፃቸውን ከቢቢሲ ዘገባ መረዳት ተችሏል፡፡ በከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ በምትገኘው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተገደሉት ...
Read More »እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ አሁንም አልተፈቱም
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2010) ክሳቸው ተቋርጦ እንዲሁም በፕሬዝዳንቱ ይቅርታ ይፈታሉ ከተባሉ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው ዮናታን ተስፋዬ አሁንም አለመፈታታቸው ታወቀ። በክስ መቋረጥም ሆነ በይቅርታ ስማቸው ያልተጠቀሰው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌንና የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ መቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ መድረክ ዘመቻ ጀምረዋል። ከጎንደሩ ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ ከታሰሩት ...
Read More »የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን መሸጋገር አይደለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2010) የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን አገዛዝ መሸጋገር አለመሆኑን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት የምንታገልለት ለውጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። በለውጡ ሂደት ስልጣን ሃላፊነት በሌላቸው እጅ እንዳይገባ በከፍተኛ የሃላፊነትና የአጣዳፊነት ሁኔታ መታገል አለብን ሲሉም ገልጸዋል። ፕሮፈሰር ብርሃኑ ...
Read More »በወልቂጤ የተጠራው አድማ ለሰባተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜና–የካቲት 13/2010) በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የተጠራው አድማ ለሰባተኛ ቀን መቀጠሉ ተገለጸ። የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑ ሁለት ሰዎች አድማውን አስተባብራችኋል ተብለው ታስረዋል። በእንድብርና በአገና የፌደራል ፖሊስ የሃይል ርምጃ እየተጠቀመ ነው። የጉራጌ ወጣቶች ጥሪ አድረግዋል። በወልቂጤ የተጀመረው አድማ ሳምንቱን ደፍኗል። ዛሬም ወደ እንቅስቃሴ አልገባችም። ባለፉት ሁለት ቀናት አንዳንድ የንግድ ቦታዎች ተከፍተው የነበረ ቢሆንም ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን የደረሰን ...
Read More »የስራ ማቆምና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2010) በአማራ ክልል የተጠራው የስራ ማቆምና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። በመጀመሪያው ቀን አድማ ያልተሳተፉ ከተሞች ዛሬ ተቀላቅለዋል። ጎንደር በተጠናከረ መልኩ የአድማውን እንቅስቃሴ እያደረገች ነው። በባህርዳር በአብዛኛው ሱቆችና መደብሮች ተዘግተዋል። ባህርዳር ከትላንት ይልቅ ዛሬ አድማ ላይ ጠንክራ ብቅ ብላለች። በአገዛዙ ታጣቂዎች ወከባ ከፍተው የነበሩ አንዳንድ የንግድ ቦታዎች ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ አድማውን መቀላቀላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ...
Read More »በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ ለ6ኛ ቀን ቀጥሎአል
በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ ለ6ኛ ቀን ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በወልቂጤ፣ በጉብሬ፣ በአገናና በሌሎችም አካባቢዎች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ ለስድሰተኛ ቀን መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የስራ ማቆም አድማው ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የተወሰኑ ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ይታወሳል። ተቃውሞው አድማሱን በማስፋት ወደ እዣ፣ ቺሃ፣ እምድብር፣ እነሞር እና ኢነር ወረዳ የጉመር ወረዳን መቀላቀላቸውን ወኪላችን ገልጿል። ...
Read More »በጎንደርና ባህርዳር የስራ ማቆም አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል
በጎንደርና ባህርዳር የስራ ማቆም አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በአማራ ክልል የተጠራው የስራ ማቆም አድማ በጎንደር ከተማ ለሁለተኛ ቀን በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል። በከተማው ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴውም ሆነ የተሽከርካሪ አገልገሎት የለም። የአገዛዙ ካድሬዎች የንግድ ድርጅቶችን ለማስከፈት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክልታል። በባህርዳር ትናንት የተጀመረውን አድማ ተከትሎ የአገዛዙ ባለስልጣናትና ሰራተኞች የንግድ ድርጅት ባለቤቶችን ...
Read More »