Author Archives: Central

ልጃቸው ፍትህ እንዲሰጠው ኢትዮጵያዊቷ እናት ጥሪ አቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010) በሳዑዲ አረቢያ ለ12 ዓመታት በስቃይ ሆስፒታል የሚገኘው ልጃቸው ፍትህ እንዲሰጠው ኢትዮጵያዊቷ እናት የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ። ወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚል ሁሴን በህክምና ባለሙያዎች በተፈፀመ ስህተት መንቃት ሳይችል የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የቀረው ልጃቸውን ይዘው ወደ ሀገር ቤት ለመግባት የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ጠይቀዋል። ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳላደረገላቸው የገለጹት ወ/ሮ ሃሊማ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው እንዲቆም መጠየቃቸው ታውቋል። ህፃን ...

Read More »

በናይጄሪያ አንድ ከአንድ መቶ በላይ ሴት ተማሪዎች ታገቱ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010) እስላማዊ ታጣቂዎች በናይጄሪያ አንድ ት/ቤት በመውረር ከአንድ መቶ በላይ ሴት ተማሪዎችን  አግተው ወሰዱ።የተማሪዎቹ ወላጆች የናይጄሪያ መንግስት ልጆቻቸውን በፍጥነት  እንዲያስመልስ ጥሪ አቅረበዋል።ዕገታውን በተመለከተ ሃላፊነት የወሰደ ቡድን ባይኖርም ቦኮሃራም ድርጊቱን ሳይፈጽም አንዳልቀረ ታምኖበታል። እስላማዊ ታጣቂዎች በናይጄሪያ አንድ ት/ቤት በመውረር ከአንድ መቶ በላይ ሴት ተማሪዎችን  አግተው ወሰዱ፥የተማሪዎቹ ወላጆች የናይጄሪያ መንግስት ልጆቻቸውን በፍጥነት  እንዲያስመልስ ጥሪ አቅረበዋል።ዕገታውን በተመለከተ ሃላፊነት የወሰደ ቡድን ባይኖርም ...

Read More »

የፖለቲካ እስረኛው በእስር ቤት እንዳለ ሕይወቱ አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010) የፖለቲካ እስረኛው ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ በእስር ቤት እንዳለ ሕይወቱ ማለፉ ተነገረ። በሽብር ወንጀል ተከሶ የአራት አመት እስር ፍርደኛ የነበረው ገበየሁ ፈንታሁን እስርቤት ውስጥ በሕመም ምክንያት መሞቱ ታውቋል። እስረኛው ገበየሁ ፈንታሁን ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ እንደነበርና በቆይታውም ድብደባ ይፈጸምበት እንደነበር ከሐገር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ክሳቸው ተቋርጦ ሊፈቱ ነው የተባሉት የዋልድባ መነኮሳት ምስክር ሊሰማባቸው በፍርድ ...

Read More »

የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ሲራጅ ፈጌሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010) የደቡብ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢሕዴን/ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምትክ አቶ ሲራጅ ፈጌሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው እየሰሩ ያሉትን አቶ ደሴ ዳልኬን ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል። የደኢሕዴን ምርጫ ከዚህ ቀደም ይፋ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ዜናው እንዲነሳ ተደርጎ ማስተባበያ ተሰጥቶበት እንደነበር ይታወሳል። የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 21 ቀናት ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ ...

Read More »

በነቀምቴ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2010) በነቀምቴ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ለሰዓታት ታግተው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተከትሎ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ የአገዛዙ ታጣቂዎች ህዝቡ ላይ ሲተኩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል። ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልወጣም። ደጋፊዎቻቸውን ለማግኘት ወደ ወለጋ ያመሩት የኦፌክ አመራሮች አስቸኳይ አዋጁን የሚጥስ ተግባር ነው በሚል በፌደራል ፖሊስ ጉዛቸውን እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። በደምቢዶሎ በሳምንቱ መጨረሻ በአገዛዙ ታጣቂዎች በተወሰደ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በጦር ወንጀለኝነት ሊከሰሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 16/2010) አርባ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በጦር ወንጀለኝነትና በሰብአዊ መብት ጥሰት በግል ሊጠየቁ እንደሚችል አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ይፋ አደረገ። ቢቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ሱዳን አስገድዶ መድፈር፣የአካል መጉደል፣ስቃይና እንግልት እንዲሁም ከመኖሪያ አካባቢ መፈናቀል በሰፊው ሲፈጸም ነበር ብሏል። ሪፖርቱ እጅግ አሰቃቂ ነበር ካለው ድርጊት ውስጥ ሕጻናት እናቶቻቸው ሲደፈሩ እንዲመለከቱ ይደረግ ነበር፣ወንዶች ጭምር የአስገድዶ መድፈር ...

Read More »

ብአዴን አቶ ደመቀንና አቶ ገዱን በስልጣን ላይ ለማቆየት ወሰነ

ብአዴን አቶ ደመቀንና አቶ ገዱን በስልጣን ላይ ለማቆየት ወሰነ (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በዝግ ስብሰባ ለሳምንታት ሲገማገም የሰነበተው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ አቶ ደመቀ መኮንን የድርጅቱ ሊ/መንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊ/መንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፏል። አቶ ገዱ በሌሎች ሰዎች እንደሚተኩ አስቀድሞ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን ድርጅቱ በእርሳቸው መሪነት መቀጠሉን መርጧል። አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን ...

Read More »

በምዕራብ ዕዝ በመከላከያ አባላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ወታደሮች መቁሰላቸው ታወቀ

በምዕራብ ዕዝ በመከላከያ አባላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ወታደሮች መቁሰላቸው ታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከ10 ቀናት በፊት በባህርዳር ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ ምድብ ውስጥ ወታደሮች ከብሄር ጋር በተያያዘ እርስ በርስ በመታኮሳቸው፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በወቅቱ ሌሊቱን የተኩስ ድምጽ ሲሰሙ ያደሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በሁኔታው ተደናግጠው ነበር። የክልሉ የኢሳት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተለያዩ የአምራች እንዱስትሪ ባለቤቶች ሲናገሩ ሲናገሩ ቢቆዩም፣ ችግሩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም። በአሁኑ ሰዓት የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚጠበቀው ወረፋ ከአመት በላይ መሆኑን የሚናገሩት ባለሀብቶች፣ ያም ሆኖ በቂ ዶላር ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ይላሉ። ...

Read More »

በሽር ማክታልን ከእስር ለማስለቀቅ ዘመቻ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 16/2010) በአሸባሪነት ተወንጅሎ እድሜ ልክ የተፈረደበትንና የካናዳ ዜግነት ያለውን ኢትዮጵያዊ በሽር ማክታልን ከእስር ለማስለቀቅ ዘመቻ ተጀመረ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር አባል ነው በሚል ከኬንያ በሃይል ተገዶ ወደ ኢትዮጵያ የተወሰደውና በአሸባሪነት የተወነጀለው በሽር ማክታል ከታሰረ 11 አመታት ተቆጥረዋል። የ49 አመት እድሜ ያለው በሽር ከእስር እንዲለቀቅ ካናዳውያን ዘመዶቹና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች ዘመቻ ጀምረዋል። የካናዳ ዜግነት ያለው ...

Read More »