(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) የፊታችን ሐሙስ የተጠራው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ ተራዘመ። የምክር ቤቱ ስብሰባ የኢሕአዴግን ሊቀመንበር ለመምረጥና ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን ግለሰብ ለመወሰን እንደነበርም ለመረዳት ተችሏል። በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በተለይም በሕወሃትና በኦሕዴድ መካከል ያለው ፍጥጫ ለስብሰባው መራዘም ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረም ታምኖበታል። ከእያንዳንዱ አባል ፓርቲ 45 በአጠቃላይ 180 አባላት ያሉት የኢሕአዴግ ምክር ቤት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ምትክ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርን ...
Read More »Author Archives: Central
በነቀምት ውጥረቱ ተባብሷል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) በነቀምት ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬ ጠዋት አንድ ወጣት በአልሞ ተኳሽ ወታደር መገደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂን በመጣስ ተቃውሞ እያደረጉ ባሉ የነቀምት ነዋሪዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የአገዛዙ ወታደሮች ከ20 በላይ ሰዎች ማቁሰላቸውም ታውቋል። ቤት ለቤት አፈሳ የተጀመረ መሆኑኑም ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ አመራሮች በወለጋ ደጋፊዎቻቸውን ለማግኘት ቀጠሮ የያዙት ከአስቸኳይ አዋጁ ይፋ መሆን ቀደም ብሎ ...
Read More »በነቀምቴ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አንድ ሰው ሲሞት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል
በነቀምቴ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አንድ ሰው ሲሞት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል (ኢሳት ዜና የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ከነቀምቴ ህዝብ ጋር ለመገናኛት ያደረጉት ሙከራ አዋጁ አይፈቅድም በሚል ሰበብ በወታደሮች እንዲገታ ከተደረገ በሁዋላ፣ ህዝቡ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን፣ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 1 ሰው መገደሉንና 7 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የኦሮምያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ...
Read More »የደህንነት አባላት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ዘረፋ እየፈጸሙ ነው። በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች የንብረት ዘረፋውም ተባብሶ ቀጥሏል
የደህንነት አባላት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ዘረፋ እየፈጸሙ ነው በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች የንብረት ዘረፋውም ተባብሶ ቀጥሏል (ኢሳት ዜና የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) በመዲናዋ አዲስ አበባ እና አዋሳኝ ከተሞች በቀንና በጨለማ ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያ እየተፈጸመ ሲሆን የደህንነት አባላት እንዲሆኑ ራሳቸውን የሚገልጹ ሰዎች የዘረፋው ዋነኛ ተዋናዮች ሆነዋል። ዝርፊያው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሱሉልታ፣ ሰበታ፣ ፉሪ፣ ቡራዩና በቅራቢያው በሚገኙ ...
Read More »ከአርባ ምንጭ ከተማ በሽብር ክስ ተከሰው ሰሞኑን የተለቀቁ የከተማዋ ወጣቶች አሁንም በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻልንም አሉ
ከአርባ ምንጭ ከተማ በሽብር ክስ ተከሰው ሰሞኑን የተለቀቁ የከተማዋ ወጣቶች አሁንም በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻልንም አሉ (ኢሳት ዜና የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸው በአርባምንጭ ከተማ የሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በማእከላዊ እስር ቤት፣ በሸዋ ሮቢት፣ በቂሊንጦና ዝዋይ እስር ቤቶች ውስጥ ሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ በእስር ሲንገላቱ የቆዩት ወጣቶች፣ ከእስር ከተፈቱም በሁዋላ እንግልቱ እንዳልቀረላቸው ይናገራሉ። እጃቸው በተያዘበት ወቅት ”ከመቼ ...
Read More »የነቀምት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
የነቀምት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በኦሮምያ ክልል በወለጋ ነቀምት ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በአካባቢያቸው የተሰማሩት ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ በአጠቀላይ አገዛዙን የሚያወግዙ መፍክሮች ተሰምተዋል። የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ የተኮሱ ሲሆን፣ ጉዳት መድረሱና አለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ከህዝቡ ...
Read More »የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህልውና አደጋ ውስጥ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህልውና አደጋ ውስጥ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ሜቴክና ባለለስልጣናት በባንኩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ህዝቡ በጊዜ ገንዘቡን እንዲያወጣ ባለሙያዎች መክረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባልተጠኑ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የሜቴክ ወታደራዊ ጄኔራሎችና ባለስልጣናት በፈጸሙት ዘረፋ የህልውና አደጋ እንደተረጋገጠበት ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች ገልጸዋል። ሙሉውን ዘገባ በድረገጻችን ላይ እንድትከታተሉት በአክብሮት እንገልጻለን
Read More »የባህርዳር ከነማና የደሴ ከነማ ደጋፊዎች ተቃውሞአቸውን አሰሙ
የባህርዳር ከነማና የደሴ ከነማ ደጋፊዎች ተቃውሞአቸውን አሰሙ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ የባህር ዳር ከነማ እና ደሴ ከነማ የእግር ኳስ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተመልካቾች አገዛዙን የሚያወግዙ መፈክሮችን አሰምተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 10 “ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ማዕከላት ከስፖርት ተግባር ውጪ የሆኑ ሁከቶችና ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ ነው” ቢልም ተመልካቾች፣ ተቃውሞአቸውን ከመግለጽ ወደ ሁዋላ አላሉም። ተመልካቾች “ ...
Read More »አቶ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ውስጥ ህይወታቸው አለፈ
አቶ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ውስጥ ህይወታቸው አለፈ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ እስከዳር ይርጋ ክስ መዝገብ በ”በሽብር” ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህመም እንደሞተ የተገለጸ ቢሆንም፣ ታላቅ ወንድሙ ግን ሟቹ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለበት ገልጿል። ታላቅ ወንድሙ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ ሟቹ ከሶስት ቀናት በፊት ...
Read More »የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል አስመልክቶ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቁ
የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል አስመልክቶ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቁ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ይዞታችን አይነካ ማለታቸውን ተከትሎ ከዋልድባ ገዳም ተይዘው በማእከላዊና በተለያዩ እስር ቤቶች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የቆዩት መነኮሳት የደረሰባቸውን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በደብዳቤ አሳውቀዋል። በጻፉት ደብዳቤ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰቶች በዝርዝር አቅርበዋል። መነኩሳቱ በጻፉት ደብዳቤ እንደገለጹት ...
Read More »