“ከልባችን ይቅር ተባብለን በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንሻገር” ሲሉ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መንግስታዊ ስልጣኑን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውን ከልባቸው ይቅር ተባብለው፣ የትናንትናውን ምዕራፍ ዘግተው በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ አገራዊ ጉዞ እንዲሸጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ይህን እውን ለማድረግ አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቢናገሩም፣ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ አፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ የአስቸኳይ አዋጁ እንዲነሳ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ ጠየቀ
በኢትዮጵያ አፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ የአስቸኳይ አዋጁ እንዲነሳ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ ጠየቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዶ/ር ዓብይ አህመድን መመረጥ አስመልክቶ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪክ ኤምባሲ በመግለጫው እንዳለው መንግስታቸው የአዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር መሾም በበጎ ጎኑ እንደሚያየውና ከዶ/ር አብይና የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የጋራ ግንኙነት እንደሚቀጥል ገልጿል። በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማሪያም ...
Read More »የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት ጀመሩ
የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት ጀመሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደሮች ከግቢያቸው እንዲወጡና ያነሱዋቸው የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በመጠየቅ ትምህርታቸውን ለመጀመር ፈቃደኛ ያልሆኑት የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ዛሬ ትምህርት ካልጀመሩ ከግቢው ለቀው እንዲወጡና ዩኒቨርስቲውም እንደሚዘጋ በወታደራዉ አዛዦች የተነገራቸው ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ ትዕዛዙን ባለመቀበል እስከ ጠዋት ድረስ ትምህርት አልጀመሩም ነበር። ይሁን እንጅ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ተማሪዎች ትምህርት መጀመራቸውን የገለጸው ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አሁንም በችግር ላይ ናቸው
በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አሁንም በችግር ላይ ናቸው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንት በፊት ያልተፈቀደ ስብሰባ እና አርማ የሌለውን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ተጠቅማችሁዋል በሚል በእስር ላይ የሚገኙት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሁንም ያሉበት ሁኔታ አለመሻሻሉ ታውቋል። አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝና ሌሎችም ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የታሰሩበት ሁኔታ እጅግ መጥፎ የሚባል መሆኑ መዘገቡ ይታወቃል። በአገራቸው ጉዳይ ...
Read More »በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ
በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ በወታደራዊ እዙ ቢታዘዙም፣ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ሳይመጡ ትምህርት አንጀምርም በማለታቸው ከየክፍላቸው እየተወሰዱ መታሰራቸውን የአካባቢው ወኪላችን ገልጿል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ግቢውን ተቆጣጥረው ተማሪዎችን ከክፍላቸው እያወጡ ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ከሳምንት በፊት ተማሪዎች ምዝገባውን ካካሄዱ በሁዋላ ፣ ከፋሲካ በሁዋላ እንገናኝ በማለት ብዙዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው ነበር። በግቢው ...
Read More »በአርባምንጭ በቅርቡ ከተፈቱት የህሊና እስረኞች መካከል የተወሰኑት ተመልሰው መታሰራቸውና ሌሎችም ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው
በአርባምንጭ በቅርቡ ከተፈቱት የህሊና እስረኞች መካከል የተወሰኑት ተመልሰው መታሰራቸውና ሌሎችም ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የሽብርተኝነት ወንጀሎች ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎየተፈቱ ቢሆንም፣ በአካባቢያቸው የሚገኙ የወታደራዊ እዙ ወኪሎች ነን የሚሉ እና የወረዳው ባለስልጣናት እየዛቱባቸው መሆኑ ታውቋል። በእነ ሉሉ መሰለ መዝገብ ተከሶ በቅርቡ ከእስር የተፈታው መርደኪዮስ ሽብሩ መልሶ ...
Read More »በአስከፊ እስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሞ ሆስፒታል ገባ
በአስከፊ እስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሞ ሆስፒታል ገባ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በደረሰበት ህመም ምክንያት ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል። ጋዜጠኛ ተመስገን የጀርባና የወገብ ህመም እንደሚያሰቃየው ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረ ሲሆን፣ ሌሊቱን በእጅጉ ታሞ ማደሩን አብረውት ከታሰሩት ከእነ አቶ አንዱአለም አራጌ መስማቱን ገልጿል። ባለፈው ...
Read More »አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሥር ለሰደደው የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ ይገባቸዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሥር ለሰደደው የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ ይገባቸዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) አዲሱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አብይ አህመድ በመላው አገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋውንና ሥር የሰደደውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ለመፍታት ከሁሉም ነገሮች ቅድሚያ ሊሰጡት ይገባል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል። የጠቅላይ ሚንስትሩን መመረጥ አስመልክቶ የድርጅቱ ...
Read More »በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀሌ ከተማ መሃከል ሊደረግ የነበረው ጫወታ በኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ ተቋረጠ
በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀሌ ከተማ መሃከል ሊደረግ የነበረው ጫወታ በኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ ተቋረጠ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በትናንትናው እለት በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲግራት ከተማ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀሌ ከተማ መሃከል ሊካሄድ የነበረው ጫወታ በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ ተቋርጧል። ጫወታው ዛሬ እንዲደገም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር ውሳኔ ቢያሳልፍም ኮማንድ ፖስቱ ጫወታው እንዳይካሄድ ማገዱን ሪፖርተር ...
Read More »የቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ስልጣን ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010) የቦትስዋናው ፕሬዝዳንት አያን ከሃን ስልጣን መልቀቃቸው ተሰማ። የሁለት ዙር ስልጣናቸውን ሊያጠናቅቁ ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ፕሬዝዳንት አያን ካሃን መንበረ ስልጣኑን ቀድመው መልቀቅ የፈለጉት ለሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት በማሰብ ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ በሚገኙት 57 ግዛቶችም በመዘዋወር ስንብት አድርገዋል። ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ በሀገሪቱ በሚገኙ 57 ግዛቶች የስንብት ጉብኝት ያደረጉት የቦትስዋናው ፕሬዝዳንት አያን ከሃን የስልጣን ዘመናቸውን ለመጨረስ 18 ወራት እንደሚቀራቸው ነው ...
Read More »