Author Archives: Central

አቶ አብዲ ኢሌ “ ኦሮሞዎች ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ ፈረጁ

አቶ አብዲ ኢሌ “ ኦሮሞዎች ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ ፈረጁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ አቶ አብዲ ኢሌ “ ኦሮሞዎች ጠላቶቻችን ናቸው” ሲል በጅጅጋ ከተማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ለተጠሩ ለክልሉ ሽማግሌዎች ተናግረዋል። በከፍተኛ የስሜት መረበሽ ውስጥ ሆነው ንግግር ያደረጉት አቶ አብዲ “ ዶ/ር አብይ እና ሌሎች ወደ ጅግጅጋ መጥተው የነበሩት ኦሮሞዎች ውሸታሞች ናቸው” ብለዋቸዋል። “በእኛ ላይ ስውር ...

Read More »

የወልዋሎ ቡድን ተጫዋቾች ከፈጸሙባቸው ድብደባ ይልቅ የሰደቧቸው ዘር ላይ ያነጣጠረ ስድብ ይበልጥ እንዳመማቸው ኢንተርናሽናል አልቢትር ኢያሱ ፈንቴ ተናገሩ።

የወልዋሎ ቡድን ተጫዋቾች ከፈጸሙባቸው ድብደባ ይልቅ የሰደቧቸው ዘር ላይ ያነጣጠረ ስድብ ይበልጥ እንዳመማቸው ኢንተርናሽናል አልቢትር ኢያሱ ፈንቴ ተናገሩ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ባደረጉት ንግግር ተጫዋቾቹ ሲደበድቧቸው ከአፋቸው ይወጣ የነበረውን ዘር ላይ ያነጣጠር ስድብ ለመግለጽ እንደማይፈልጉ በመጥቀስ “በምን ቋንቋ መናገር እንደምችል አልገባኝም። በእግርኳስ ቋንቋ ላውራ ብል ...

Read More »

በሃረር የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ

በሃረር የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በከተማው የሚታየው የኑሮ ውድነት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ህዝቡ ህይወቱን ለመምራት ተቸግሯል። ሰሞኑን ስንዴ ጠፋ በሚል አንድ ብር ይሸጥ የነበረው ዳቦ፣ መቶ በመቶ ጨምሮ 2 ብር መግባቱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የዳቦው መጠንም በከፍተኛ ሁኔታ ማነሱን ይናገራሉ። አብዛኛው የመንግስት ሰራተኞችም ሆኑ አንስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በየቀኑ የሚንረውን ...

Read More »

የዚምባቡዌ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በመጪው ምርጫ ካሸነፉ ቻይናውያን ባለሀብቶችን ከሀገራቸው ጠራርገው እንደሚያስወጡ አስታወቁ።

የዚምባቡዌ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በመጪው ምርጫ ካሸነፉ ቻይናውያን ባለሀብቶችን ከሀገራቸው ጠራርገው እንደሚያስወጡ አስታወቁ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) በመጪው ሐምሌ በዚምባቡዌ በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግምት ከተሰጣቸው ዋነኛ ተፎካካሪዎች መካከል አንዱ- የዋኘኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የዲሞክራቲክ ለውጥ ንቅናቄ መሪ ናቸው። ሚስተር ኔልሰን ቻሚሳ ለምርጫው እያደረጉት ባለው ቅስቀሳ “በምርጫው ካሸነፍን ሁሉንም የቻይና ኩባንያዎች እናባርራቸዋን”ማለታቸውን አንድ የዚምባቡዌ የግል ድረ ገጽን ዋቢ ...

Read More »

ኢራን የ6 ቢሊየን ዶላር ካሳ ትክፈል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) በአሜሪካ ከ17 አመታት በፊት በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች ኢራን የ6 ቢሊየን ዶላር ካሳ እንድትከፍል አንድ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ዳኛ ትዕዛዝ ሰጡ። የምርመራ ውጤቶች ግን ኢራን በሽብር ጥቃቱ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎ የሚያሳይ ነገር አልተገኘም በሚል ትችት በመቅረብ ላይ ነው። የኒዮርክ የደቡብ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ጆርጅ ዳኒልስ ትዕዛዙን የሰጡት ትላንት መሆኑ ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የእስር ማዘዣ ተቆርጦብኝ ነበር አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ከመመረጣቸው አምስት ቀን ቀደም ብሎ የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸው እንደነበር ገለጹ። ዶክተር አብይ አህመድ ይህንን የገለጹት ለሃይማኖት አባቶች፣ለአባገዳዎች፣ለሀገር ሽማግሌዎች፣ለሃይማኖት አባቶች፣ለኪነጥበብ ባለሙያዎችና ለአትሌቶች በተዘጋጀ መድረክ ላይ መሆኑም ተመልክቷል። ትላንት ምሽት በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው ስነ ስርአት ላይ እሳቸውንና አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ በአምስት የኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ ተቆርጦ ነበር ማለታቸውን በስብሰባው ላይ ...

Read More »

የአብይ አህመድን ስልጣን ለማዳከም የተለያዩ እቅዶችን መንደፋቸው ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) የሕወሃት መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ስልጣን ለማዳከም የተለያዩ እቅዶችን መንደፋቸው ተገለጸ። ሰሞኑን በትግራይ በተካሄደውና በመከላከያ ውስጥ ያሉ ነባር የሕወሃት የሰራዊት አባላት በተሳተፉበት  ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያን እንዳይቆጣጠሩና በክልሎች የሚኖራቸውን ስልጣን የሚገድቡ የተለያዩ ርምጃዎች ተወስደዋል። ከመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች የተገኙበትና በአቶ አባይ ጸሀዬና በአቶ በረከት ስምኦን የተመራው ስብሰባ የትግራይ ተወላጆች ከስልጣን ተገፍተዋል የሚል ...

Read More »

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት በአዲስ እየተዋቀረ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት በአዲስ መልክ እየተዋቀረ መሆኑ ተነገረ። በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት አሁንም ሕወሃቶች የተለያዩ መምሪያዎችን ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ሲል የውስጥ ደህንነት የነበረው መምሪያ በ3 ተከፍሎ አዲስ ተሿሚዎች መመደባቸው ተነግሯል። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተለያዩ መምሪያዎች የተዋቀረ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚሁ መምሪያዎች መካከል በዋናነት የሚታወቀው የውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ከ3 እንዲከፈል መደረጉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ...

Read More »

ከትግራይ ክልል ውጪ በርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል ተቋርጦ እንደነበር ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ምክንያት ከትግራይ ክልል ውጪ በርካታ ከተሞች በጨለማ ተውጠው እንደነበር ተገለጸ። በግልገል ጊቤ ግድብ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ በተፈጠረ ችግር የኢትዮጵያ ከተሞች በጨለማ መዋጣቸው ብዙዎችን ግራ አጋብቶ እንደነበር ተገልጿል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ችግሩ ተፈቶ መብራት መለቀቁን ቢገልጽም የተወሰኑ ከተሞች ግን አሁንም በጨለማ እንደተዋጡ መሆናቸው ታውቋል። በግልገል ጊቤ የሃይል ማመንጫ የተፈጠረው ...

Read More »

በሻኪሶ የተነሳው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2010) ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በሻኪሶ ለተጨማሪ 10 አመታት ኮንትራቱ መታደሱን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ተገለጸ። በምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞን በበርካታ ከተሞችና የገጠር መንደሮች የተነሳው ተቃውሞ ኮንትራቱ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ነው ተብሏል። መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞውን እያሰማ ያለው የጉጂ ህዝብ በአስቸኳይ ሜድሮክ አካባቢውን ለቆ ካልወጣ ርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ኮንትራቱ ሊታደስ የነበረው ከሶስት ...

Read More »